WolloPedia
Organic Wollo
01/05/2026
"የተፈጥሮ ድንቅ ውበት - የአልቡኮ ጎሴ ሜዳ!
በደቡብ ወሎ ዞን አልቡኮ ወረዳ የሚገኘው የጎሴ ሜዳ ልዩ የተፈጥሮ ውበት፣ ማራኪ አረንጓዴ ገጽታ እና መንፈስን የሚያድስ አየር ያለው ድንቅ ቦታ ነው።
ተፈጥሮን ለሚወድና አእምሮውን ማዝናናት ለሚፈልግ ሰው ሁሉ ፍጹም ምርጫ ነው። ይህንን ውብ ስፍራ አይታችሁታል? ካልጎበኛችሁት ሊያመልጣችሁ የማይገባ የምድራችን ጸጋ ነው! 🇪🇹
#አልቡኮ #ጎሴሜዳ
05/03/2026
የደሴ ከተማ ዘመን ተሻጋሪ ብርሃናማ ከዋክብት ...⭐️🌟💫
ታይታኒክ በተሰኜው ዝነኛ ፊልም ላይ "ጃክ" የሚባለው ዋና ገፅ ባህሪ እንዲህ የሚል ቃለ ተውኔት አለው "I like the night. Without the dark, we'd never see the stars." በእርግጥም ጨለማ ከሌለ ከዋክብትን በፍፁም አናያቸውም። አስፈሪው ጨለማ አቅም የሚያጣው ውብ እና ብርሃን የሚተፉ ከዋክብት በሰማዩ ላይ ሲፈሱ ብቻ ነው። ልዩነቱ በደሴ ከተማ ሰማዩ ብቻ ሳይሆን ምድሩም በርካታ ከዋክብትን አፍርቷል። እድለኛዋ ደሴ ከተማ በዬዘመናቱ ከሰማይ ብቻ ሳይሆን ከምድርም ከዋክብትን ትታደላለች። ደሴ የማይነጥፍባት የብርሃን ምንጭ ናት። ጊዜ እንደፈቀደ ለዛሬ የአንዱን ብርሃናማ የደሴ ከተማ ኮከብ እንቃኝ።
ወይዘሮ አሰለፈች ካሣ ዘወትር ወደ ደሴ መድኃኒያለም እየሄዱ ልጅ እንዲሰጣቸው በድኃኒያለምን ይለምናሉ። 'ልጅ ከሰጠኸኝ አገልጋይህ ይሆናል" በማለት ተስለውም ነበር። የአቶ ገበየሁ እሰየም ፀሎት ልጅ ነው። እግዚአብሔር ፀሎታቸውን ሰምቶ በ1932ዓ.ም ሜጠሮ በሚባለው ሰፈር ወንድ ልጅ ሰጣቸው። ይህ ልጅ አድጎ ሊቀ ጳጳስ ይሆናል ብሎ ማን አሰበ ? ህፃኑ በቀዝቃዛው የደሴ ሰማይ ከጦሳ ተራራ ስር እየቦረቀ አደገ። እድሜው ለትምህርት ሲደርስ እናቱ ወደተሳለችው ደብር ወደ ደሴ መድኃኔዓለም የኔታ ክፍሌ ( አባ ክፍለ ማርያም) ዘንድ ላከቺው። ፊደል መቁጠር ጀመረ።
ይህ ሰው በሀገር ውስጥ ከ8 ከዳማትና አድባራት በላይ ተዟዙረው የተማሩ፣ በብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ አመካኝነት ወደ ግሪክ ተልከው "በደሴተ ፍጥሞ" ለሁለት ዓመት መንፈሳዊ ትምህርት ተምረው ዲፕሎማ የተመረቁ፣ ከአቴንስ ዩኒቨርስቲ በሥነ መለኮት የማስትሬት ዲግሪ የተቀበሉ፣ ከስዊዘርላንድ ፍሪበሪን ዩኒቨርሲቲ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተመረቁ፣ በኢየሩሳሌም ደብረ ጽዮን የግሪክ መንፈሳዊ ኮሌጅ ውስጥ በመግባት በአረብኛ ቋንቋ ትምህር የተመረቁ፣ አምስት አይነት የውጭ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ... የደሴው ልጅ ብጹዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ናቸው።
አባታችን "የቤተ ክርስቲያን ታሪክ" ተብሎ በታተመው እና ቀድመው ባዘጋጁት መፅሐፍ ላይ ስለ ልጅነታቸው ሲያወሱ "እንደማንኛውም የደሴ ልጅ ቦርከና ዋኝቻለሁ፣ የጦሳን ገደል እሩጨበታለሁ፣ ፈረንጅ አምባ ስራገጥ በመዋሌ በጉማሬ ተገርፊያለሁ (ፈረንጅ አምባ ፒያሳ ነው)፣ አሬራ ሄጄ ሀጋምና ቀጋ ለቅሚያለሁ፣ ስልካምባ ሄጀ በስልክ አውርቻለሁ፣ አልቅሼ ስቂያለሁ ... ብቻ በአጭሩ የደሴ ትዝታ ከልብ በቀላሉ የሚወጣ አይደለም" በማለት ልጅነታቸውን አስታውሰዋል።
የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ በነበራቸው ጊዜ በርካታ ሥራዎችን በመስራት ለትውልድ መሰረት መጣል የቻሉ አባት ናቸው፡፡ የወንጌልና የታሪክ ብርሃንን በተለይ በወጣቱ ሕይወት ላይ የፈነጠቁት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሐምሌ 22/1982 ዓ.ም ወደ መቂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለአገልግሎት ሲሄዱ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በሃምሳ ዓመታቸው ሕይወታቸውን ያጡ እንቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባት እና በደሴ ከተማ ሰማይ ያበሩ ኮከብ ናቸው።
@ሜላት ሰሎሞን የመነን ልጅ
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.