Awusa.com

Awusa.com

Teilen

A resource and advocacy center for the art, history, culture, ethnography and current affairs of Afa

08/05/2026

:- ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ማስጠንቀቂያ ሰጡ!!

በትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ያለው የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ወደ ከረረ ደረጃ መሸጋገሩን ተከትሎ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ የተቃውሞ መግለጫ አወጡ።

ዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም “ተመርጠናል” የሚሉ አካላት በጸጥታ ኃይሎች ታጅበው በጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አዳራሽ ስብሰባ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

ድርጊቱ “የሥልጣን ወረራ” መሆኑን የጠቀሱት ጄነራሉ፣ ለሚከተለው ማንኛውም ዓይነት ቀውስ ተጠያቂው ይህ በጉልበት ሥልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

07/05/2026

የሕወሓት አንጃ የትግራይን ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ከሻዕቢያ ጋር ለማቆላለፍ ወስኗል!

የትግራይን ህዝብ ከሀገሩ የመነጠል ወንጀል! ያረጠው አንጃ የትግራይን ኢኮኖሚ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ከሻዕቢያ ጋር ለማቆላለፍ የወሰነው ውሳኔ የሀገር ክህደት ነው።

ህዝብን ለፖለቲካ ቁማር ማስያዝ ይብቃ! የህዝብን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል የትውልድ ወንጀል ነው! ንቃ የትግራይ ህዝብ!


!
#ሕወሓት
#ትግራይ
#ኢትዮጵያ

04/05/2026

ህወሓት በገዛ ሴራዋ ነበልባል እየተለበለበች ነው!!

የትግራይን ህዝብ ለሦስተኛ ዙር የጦርነት ማገዶ ለማድረግ የቆረጠው ህወሓት፣ ዛሬ በገዛ ወታደራዊ አመራሮቿና በህዝብ ቁጣ ግንብ ስር እየተቀበረች ትገኛለች።

የሰላም ስምምነቱን በመናድ ክልሉን ዳግም ወደ እልቂት ለመውሰድ ያቀደችው ሴራ "ለጦርነት አንሰለፍም" ባሉ የቁርጥ ቀን የጦር መሪዎች አይሆንም ባይነት መክኖ፣ ድርጅቱ በውስጥ ሽኩቻና በመርበድበድ ላይ ይገኛል።

እንደ ብ/ጄነራል ነጋሽ ዳኘው ያሉ ከፍተኛ መኮንኖችን ከሃላፊነት በማንሳትና ለማሰር በማሳደድ የምትፈፅመው የድንባዤ እርምጃ፣ ቡድኑ ከውስጥ እንደ ሰም እየቀለጠ መሆኑንና የህልውናው ጀንበር መጥለቋን የሚያበስር የውርደት አዋጅ ነው።

የትግራይ ወጣት፣ ኤሊቶችና ሰራዊቱ "ለጥፋት ቡድን ማገዶ አንሆንም" በማለት የጀርባ አጥንቷን ስለሰበሩት፣ ያቀደችው ህገ-ወጥ የሹመት ድራማ ሳይጀመር በውርደት ተስተጓጉሏል።

ይህ ከውስጥ የነደደው የፍትህ ነበልባል ድርጅታዊ መዋቅሯን አመድ እያደረገው ሲሆን፣ ህወሓት ከገዛ ሰራዊቷና ከህዝብ ጋር የተጋጨችበት የዘንድሮው ዓመት የጥፋት ታሪኳ ማጠቃለያ መሆኑ የማይቀረ መራር እውነታ ነው።

ዛሬ ትግራይ ውስጥ እየተሰማ ያለው የለውጥ ነጎድጓድ፣ የጦርነት ነጋሪት ለሚጎስሙ ጁንታዎች የመጨረሻው የመቃብር ጥሪና የጥፋት ሴራቸው ማክተሚያ ነው።

Wollen Sie Ihr Service zum Top-Medienfirma in Vienna machen?
Klicken Sie hier, um Ihren Gesponserten Eintrag zu erhalten.

Telefon

Adresse

Vienna