Fikiru Kumera

Fikiru Kumera

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fikiru Kumera, Health/Beauty, Addis ababa, Ababa.

Photos from Fikiru Kumera's post 06/04/2024

ለውጡ የተጀመረበትን 6ኛ ዓመት ለማሰብ እና የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

ለውጡ የተጀመረበትን 6ኛ ዓመት ለማሰብ እና የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ “ለሀገራችን ብልፅግና በኅብረት እንቆማለን!” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ በርካታ የመዲናዋ እና የአጎራባች አካባቢዎች ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ሰልፈኞቹ ለውጡን እና የለውጡን አመራር የሚደግፉ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

ከመፈክሮቹ መካከል፣ ድሎችን በማዝለቅ እና ጉደለቶችን በማረም ለውጡን እናስቀጥላለን!” “ለሀገራችን ብልፅግና በኅብረት እንቆማለን!”፣ “መንግሥት አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ማራኪ ከተማ ለማድረግ የሚሠራውን ሥራ ከልብ እንደግፋለን!” የሚሉ ይገኙበታል።

እንዲሁም፣ “አዲስ አበባችን በመሪዎቿ እና በሕዝቡ ትብብር ወደ ተሟላ ብልፅግና የምትሸ ጋገርበት ጊዜ አጭር ነው!” “የፅንፈኝነት እና የአክራሪነት አስተሳሰብ እና ተግባርን በፅናት እንታገላለን!” “ጠንካራ ኢትዮጵያ በኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ ትገነባለች!” የሚሉ መፈክሮችንም እያሰሙ ነው።

Photos from Fikiru Kumera's post 21/03/2024

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ
*****************
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በመደበኛ አጭር የትምህርት መርሐግብሮች ያሰለጠናቸውን ጀነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች አስመረቀ።

የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ፤ ኮሌጁ በመደበኛ አጭር ኮርስ ስልጠና ጄነራል መኮንኖች እና ከፍተኛ መኮንኖችን አሰልጥኖ በዛሬው እለት አስመርቋል።

በዛሬው ዕለት የተከናወነው ጄነራል መኮንኖችና ከፍተኛ መኮንኖች ምረቃም ኮሌጁ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ተመራቂዎች በቆይታቸው ባገኙት ዕውቀት ሌሎች መኮንኖችን ለማፍራት መትጋትና የዕለት ተዕለት ስራዎቻቸውን በብቃት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ዲማ ነገዎ ተገኝተዋል።

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Photos from Fikiru Kumera's post 13/03/2024

የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር በኢትዮጵያ የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድና የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሚስተርስ ፍሎሪ ቤርፕ ንጋሩኮ በዓለም ባንክ የሚደገፈውን የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድና የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራሞች ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው በመመልከት ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስተር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ፣በበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹን ጨምሮ በርከታ ባለስልጣናት የተሳተፉ ሲሆን

ለወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ በመሰልጠን ላይ ያሉ ወጣቶችን ፣ በወረዳ 14 አስተዳደር በሚገኘው ህዳሴ ጤና ጣቢያ ውስጥ በልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች የተሰራውን የከተማ ግብርና ስራ ተመልክተዋል።

የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ እንግዶችን ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ በከተማ አቀፍ ደረጃ እየተሰሩ ባሉ ተግባራት ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ሚስተርስ ፍሎርቤርፕ ንጋሩኮ በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድና የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት እየተከናወነበት ያለው አግባብ በእጅጉ የሚበረታታ መሆኑንና ኢትዮጵያም ተግባሩን ተቀብላ በርካታ ስራ እየሰራች መሆኑን ጠቁመው ፕሮግራሙን ለማጠናከር ለሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ቃል ገብተዋል፡፡

ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
መጋቢት 04/2016 ዓ.ም

Photos from Fikiru Kumera's post 05/03/2024

በዓድዋ ድል መታሰቢያ እና አራዳ ህንጻ መሃል ያለው እንደ አዲስ የተገነባው መንገድ ከዛሬ ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት
ስለተደረገ አሽከርካሪዎች መንገዱን መጠቀም እንደምትችሉ እናሳውቃለን::

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Addis Ababa
Ababa