InfoHub
Your daily source for what's happening now. The Pulse delivers breaking news and top stories to keep you informed. Stay ahead.
18/05/2026
ጎበዟ ተማሪ 15,000 ብር መክፈል አቅቷት እራ-ሷን አጠ-ፋች የሚል ዜና መስማት እንዴት ያ-ማል? 😭
ሂንሴኔ ተፈሪ ትባላለች፤ ነዋሪነቷ በነቀምቴ ከተማ ሲሆን፣ በ'ኒው ጀነሬሽን' ኮሌጅ የቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing) የ4ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች።
በቅርብ የሚያውቋት ጓደኞቿና መምህራኖቿ እንደሚመሰክሩት፣ ሂንሴኔ በትምህርቷ እጅግ ጎበዝ፣ ታጋሽ እና በከፍተኛ ውጤቷ ሌሎች ጭምር የሚቀኑባት ድንቅ ተስፋ የነበረች ወጣት ነበረች።
ሆኖም ግን፣ ይህቺ በነገይቱ ሀገር ላይ ትልቅ እምነት ተጥሎባት የነበረች ባለ ብሩህ አእምሮ ተማሪ፣ ዛሬ በገጠማት ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ምክንያት ህይወቷን በገዛ እጇ እንድ-ታጠፋ ያደረጋት ልብ ሰ-ባሪ ታሪክ ተሰምቷል።
የዚህ አ-ሳዛኝ ጉዳይ መነሻ ደግሞ ለትምህርት ቤት መክፈል የነበረባት አስራ አምስት ሺህ (15,000) ብር ክፍያ በመቅረቱ ምክንያት ነው።
በወቅታዊው አሰራር መሰረት፣ የቀረባትን የትምህርት ክፍያ ካላጠናቀቀች ብሄራዊ የ'Exit Exam' ፈተናን መፈተን እንደማትችል ተነግሯት ነበር። ይህንን ተከትሎ፣ የረጅም ዓመታት ልፋቷ ከንቱ ሆኖ መቅረቱ እና አብረዋት የለፉ ጓደኞቿ ተፈትነው ወደ ስራ አለም ሲቀላቀሉ እሷ ግን በገንዘብ እጥረት ምክንያት ወደ ኋላ መቅረቷ፣ ውስጧን በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥና በጭንቀት እንዲሞላው አድርጎታል። ይህ የማህበራዊና የስነ-ልቦና ጫናም
በመጨረሻ ለዚህ አስከፊ ውሳኔ እንድትደርስ አድርጓታል።
ይህም መንግስትም ሆነ ስለወጣቱ ግድ የሚለው ሁሉ ሊሰራበት የሚገባ ሁላችንም አጥብቀን ልንፀልይበት የሚገባ ጉዳይ ነው!
ለቤተሰቦቿ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ተመኘሁ!
09/05/2026
ማንቼስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን አሸነፈ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ36ኛ ሳምንት መርሐግብር ማንቼስተር ሲቲ ብሬንትፎርድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኢትሃድ በተደረገው ጨዋታ የውሃ ሰማያዊዎቹን ግቦች ዶኩ፣ ሀላንድ እና ማርሙሽ በ2ኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ነጥቡን 74 በማድረስ ከመሪው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ማጥበብ ችሏል፡፡
ቀደም ሲል በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ከሰንድርላንድ 0 ለ 0፣ ሊቨርፑል ከቼልሲ 1 ለ 1 አቻ ሲለያዩ፥ ብራይተን ወልቭስን 3 ለ 0 እንዲሁም በርንማውዝ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
18/10/2025
🔥25,000 ብር ልንሸልምዎ መተናል 💸💵
🔥በተጠባቂው የእንግሊዝ ፕርሚየር Liverpool ከ Manchester united ይፋለማሉ
ይህን ተጠባቂ ጨዋታ ኮሜንት ሴክሽን ላይ በትክክል ለገመቱ 25 ቤተሰቦቻችን የ1000ብር ሽልማት እንሰጣለን 💵🎁
ተሻላሚ የሚሆኑት ከቴሌግራም እና ከፌስቡክ ተመርጠው ይሆናል👇
ማሳሰቢያ ፦ የኛን የቴሌግራም እና ፌስ ቡክ አካውንት የማይከተል ሰው መልሱን ቢያገኝ እንኳን እንደማይሸለም ከወዲሁ እናሳውቃለን!
መልካም እድል!