EthioPulse

EthioPulse

Share

Breaking and Current Ethiopian news, jobs vacancy, current affairs

Photos from EthioPulse's post 26/08/2025

🚨🇺🇸🇻🇪 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት የጦር መርከቦች ወደ ደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ቬንዝዌላ እንዲጓዙ ማዘዛቸው ተመላከተ።

ፕሬዝዳንቱ በቬንዝዌላ ያለውን ከፍተኛ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ለመግታት በማለም ይህንን ውሳኔ መወሰናቸውም ተገልጿል።

አሜሪካ የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮን በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር የምትከሳቸው ሲሆን መሪውን ለመያዝ ለሚያግዛት እሰጣለሁ ያለችውን በዕጥፍ አሳድጋ 50 ሚሊዮን ዶላር ማድረጓ ይታወሳል።

ሶስቱ የአሜሪካ የጦር መርከቦች 4 ሺህ 500 የአሜሪካ ወታደሮችን ይዘው ወደ ቬንዝዌላ ዳርቻ እየተጓዙ መሆኑንና በሚመጣው እሁድ እንደሚደርሱ ስማቸው ያልተጠቀሰ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለስልጣናት መግለፃቸውን ሮይተርስ ዘግበዋል።

የጦር መርከቦቹ ጉዞ በቬንዝዌላ ያሉ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኖች በአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ስጋትነት ላይ ምላሽ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

የቬንዝዌላው ፕሬዝዳንት ማዱሮ ለአሜሪካ ስጋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሚሊሻዎችን በበሀገሪቱ እንደሚያሰማሩ አስታውቀዋል።
ምንጭ [ሮይተርስ] ነው

25/08/2025

ቡርኪናፋሶ በጌትስ ፋውንዴሽን ድጋፍ የሚደረግለት የወባ ፕሮጀክት እንዲቆም አዘዘች።

በቢሊየነሩ ቢል ጌትስ እና ባለቤቱ ሜሊንዳ ጌትስ የተመሰረተው ጌትስ ፋውንዴሽን በቡርኪናፋሶ ወባ ላይ ትኩረት ያደረገ ስራን ይደግፍ የነበረ ቢሆንም ከመንግስት ስራውን እንዲያቆም ተነግሮታል።

ፕሮጀክቱ'Target Malaria' የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን የወባ በሽታን ለማጥፋት የዘረ መል ለውጥ የተደረገባቸውን የወባ ትንኞች መልቀት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲባል ሁሉንም ተግባራቱን እንዲያቆም ታዟል።

በተጨማሪ ወባን ለማጥፋት የሚለቃቸውን የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞችን እንዲያጠፋም ታዟል።

የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች በቡርኪናፋሶ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2019 ሲለቀቁ በዚህ ወርም ዳግም ተለቀው ነበር።

እነዚህ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች ጋር በተያያዘ ግን ሌሎች ጉዳቶችን ያስከትላሉ በሚል ውዝግቦች ነበሩ።

ቡርኪናፋሶ በአፍሪካ በወባ በሽታ በብዛት የሚጠቁባት ዜጎች ካሉባቸው ሃገራት አንዷ ስትሆን 24 ሚሊየን ዜጎች ያሏት ሃገር በ2023 በበሽታው 8 ሚሊየን ሰዎች ተይዘው ከ16 ሺህ በላይ ሰዎችም ህይወታቸውን አጥተው ነበር ተብሏል።

ከ2022 ጀምሮ በኢብራሂም ትራኦሬ ወታደራዊ መንግስት የምትተዳደረው ቡርኪናፋሶ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት እየሻከረ ሲሆን በዚህ አመት በሰኔ እና ሐምሌ ወር ብቻ 21 የአለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ተቋማትን ፈቃድም ነጥቃለች ተብሏል።

የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የወባ ትንኞች እንዴት የወባ በሽታን ለማጥፋት እንደሚረዱ እና ስለሚያስከትሉት አሉታዊ ተፅዕኖ ከእዚህ እና ከእዚህ ማንበብ ትችላላችሁ።

Source: AFP

Want your business to be the top-listed Media Company in Adama?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Adama
0000