Ethio Press

Ethio Press

Share

Official FaceBook page of Ethio Press

07/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና) በሰላም አደረሳችሁ እያልን፤ በዓሉ በሰላም፣ በጤና እና በደስታ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ለክልላችን ሕዝብና ለባለድርሻ አካላት በሙሉ ቢሯችን ምስጋናውን ያቀርባል።

የዘንድሮው የገና በዓል በክልላችን በሰላም መጠናቀቁ ለልማት ሥራዎቻችን ትልቅ ስንቅ ነው። በበዓሉ ወቅት ማህበረሰቡ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን (ሥጋ፣ ወተት፣ ቅቤና እንቁላል) በአግባቡና በጤናማ ሁኔታ እንዲጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጥ እና የክትትል ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

በበዓሉ የታየውን ከፍተኛ የፍላጎት መጠን ለማሟላት አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ የእንስሳት ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።

በበዓላት ወቅት የሚታየውን የፍጆታ ፍላጎት ተከትሎ በሽታዎች እንዳይስፋፉ የክትባትና የቁጥጥር ሥራዎችን በስፋት እያከናወንን።

አምራቾች ምርታቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማድረስ የሚችሉበትን ዘመናዊ የገበያ ትስስር በመፍጠር። የተገኘው ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የክልላችንን የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁላችሁም የድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልን!
ጋሻው መጨ( ዶር)
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

06/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል "እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!"

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ በዓል ይሁንላችሁ ። ይህ በዓል ተስፋ የምንሰንቅበት፣ መተጋገዝና መረዳዳትን የምናጠናክርበት ወቅት ነው። በተለይም በክልላችን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ለስርአተ ምግብ፣ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራና ተጠቃሚነት በአጠቃላይ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት ውስጥ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት የማይተካ ሚና አለው።

የተከበራችሁ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት፤ ባለፈው የሥራ ዘመን በክልላችን የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፣ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ ፣ በዝርያ ማሻሻል ፣ በመኖ ልማት አጠቃቀም እንዲሁም የዓሳ ሃብት ልማትን ለማስፋፋት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሰርተናል። ይህ በዓል ያለፉ ስኬቶቻችንን እያደነቅን ያሉብንን ፈተናዎች በጋራ ለመወጣት ቃል የምንገባበት ሊሆን ይገባል።

ውድ የክልላችን ህዝቦች ፣ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የታመሙትን በመጠየቅና ያለንን በማካፈል ሊሆን ይገባል።

ሰላማችንን በመጠበቅና ለልማት ስራዎቻችን ቅድሚያ በመስጠት ክልላችንን ወደተሻለ ከፍታ ለማውጣት ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ ጥሬዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!

ጋሻው ሙጨ (ዶር)
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

Photos from Ethio Press's post 02/04/2024

"አማራ ክልል በርካታ የልማት ጥያቄዎች የሚነሳበት ክልል ነው። ይህንን የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ ኢኮኖሚያችን በሚያመነጨው ልክ ተመጣጣኝ ገቢ መሰብሰብ ይጠበቅብናል።

የአማራ ክልል በቆዳ ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት ታላቅ የሚባል ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦም በእጅጉ ሰፊ ነው። ሁኖም ግን ክልሉ በሚያመነጨዉ ሃብት ልክ ገቢ በአግባቡ እየተሰበሰበ አለመሆኑ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት እያቀጨጨው ይገኛል።

ስለሆነም ከላይ እስከ ታች ያለው የክልሉ አመራር ለበጀት ምደባ የሚጓጓውን ያክል ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብና ገቢን በማስተዳደር የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመፍታት መሥራት ይጠበቅበታል።

ከደሃ ሕዝብ የመልማት ጥያቄ ላይ ቁመው ግብር የሚሰውሩ፣ ግብር ለሚሰውሩ ወገኖች የሚተባበሩ፣ ግብር ከፋዮችን ዘመናዊ በሆነ ጥራት ያለው አገልግሎት የማያስተናግዱ አካላት እየሠሩት ያለው ሥራ የሕዝብ ጠላትነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ይህንን አይነት ሕገወጥነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማረም የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ማዘመን ከሁላችንም ይጠበቃል።

በክልላችን ውስጥ የሚገኙ የውሃ፣ የትምህርት ቤት፣ የመድኀኒት አቅርቦት፣ የመስኖ፣ የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ሁሉ ከግብር ከፋዩ ሕዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚሠሩ መሆናቸውን የማይረዳ የክልላችን ነዋሪ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።

ስለሆነም ይህንን እያወቁ የሕዝብን ሃብት የሚመዘብሩ ሙሰኞች፣ ግብር የሚሰውሩ የሕዝብ ጠላቶችም ሆነ ሃቀኛውን ግብር ከፋይ ምቹና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዳያገኝ የሚያደርጉ አሠራሮች ሁሉ ተያይዘን እንድንወድቅ የሚያደርጉ በመሆናቸው መስተካከል የሚገባቸው ናቸው።

በዚህ ወቅት ከሕዝብ ጎን በመቆም ከድሃ ሕዝብ ላይ ግብር በመሰወር አንከብርም፤ ታማኝነታችን በሰላምና በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራ ጊዜም ሕያው ነው ነብላችሁ በሃቀኝነት የጸናችሁ ታማኝ ግብር ከፋዮች ክብር ይገባችኋል።"

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ "ግብር ለሀገር ክብር" በሚል መሪ መልእክት ምስጉን ግብር ከፋዮችንና ታታሪ ሠራተኞችን ለማበረታታት ባዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደz

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa