Osho

Osho

Share

Welcome to
Chandra Mohan Jain, Bhagwan Shree Rajneesh, Osho

Telegram: Contact @EthioOsho 03/11/2022

“የፈጣሪ ያለህ … ጭራሽ #ፍልስፍና የምትማረው የፈላስፎችን መንገድ ለመዋጋት ነው? እንዲህ አይነት ነገር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ የምትል ከሆነ ብር የሚልክልህን ፈልግ” አሉኝ፤

እኔም ተዉት አልኳቸው !!!

ከማትሪክ ውጤት በኋላ መላው ቤተሰቤ ተበጠበጠ … ምክንያቱም አንዱ ዶክተር እንድሆን ይፈልጋል፣ አንዱ ሳይንቲስት እንድሆን ይፈልጋል፣ ሌላው መሐንዲስ እንድሆን ይሻል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሙያዎች ሕንድ ውስጥ በጣም የሚያስከብሩ፣ ‘የሚያበሉ’ የሚባሉ ሙያዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሙያዎች ውስጥ ከገባህ #ሃብታም፣ ዝነኛ፣ የተከበርክ ትሆናለህ ነው የሚሉት፡፡

እኔ ግን “የማጠናው ፍልስፍና ነው…” ስላቸው ሁሉም ጮሁ፡፡

“አብደሃል ? የማይሆን ነገር ነው የምታወራው !! ማንም ሰው ሞኝ ካልሆነ በስተቀር ፍልስፍና ላጥና አይልም፡፡ ፍልስፍና ተምረህ ምን ለመሆን ነው ? ስድስት ዓመት ሙሉ ዋጋ የሌለው ነገር እየተማርክ ጊዜህን በከንቱ ልታጠፋ ነው ማለት ነው፡፡ ፍልስፍና እማራለሁ ብለህ ከንቱ ሆነህ እንዳትቀር፡፡ ተራ ሥራ እንኳ አታገኝም…”

እናም ትክክል ናቸው፡፡

ሕንድ ውስጥ ተራ ለሚባል ሥራ፣ የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ወረቀት ብቻ ለሚጠይቅ የፖስታ አመላላሽነት ሥራ፣ በፍልስፍና የማስተርስ ዲግሪህን፣ ከዩኒቨርሲቲው አንደኛ የወጣህበትን የወርቅ ሜዳሊያህን ብታቀርብ፣ ማንም እሺ ብሎ የሚቀጥርህ የለም፡፡ አዎ … በነዚህ ባቀርብካቸው ነገሮች ሳቢያ እምቢ ትባላለህ !!! ያቀረብካቸው ነገሮች የብቃት ማረጋገጫ ሳይሆኑ #አደገኛ ሰው ነህ ማለት ነው !!! ‘ሆ … ለፖስታ አመላላሽነት ፈላስፋ ቀጥረን ደግሞ እንቃጠል እንዴ…’ ነው የሚሉት !!!

“እድሜ ልክህን ችግር ውስጥ ነው የምትገባው - ብታስብበት ይሻላል” አሉኝ…

“ፈፅሞ #አላስብበትም፡፡ ደግሞ ታውቁኛላችሁ፡፡ እኔ በቀጥታ ነው የማየው፡፡ ምርጫ የሚሉት ነገር እዚህ ውስጥ አይገባም፡፡ ምን ማጥናት እንዳለብኝ እኔው ራሴ ነኝ የማውቀው፡፡

የትኛው ሙያ ያዋጣል አያዋጣም የእኔ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለማኝ ብሆን እንኳ ፍልስፍና ማጥናቴን አልተውም” ስላቸው፣

ምን እንደሚሉ ግራ ገባቸው፡፡

“ቆይ ግን” አሉኝ፣ “ለመሆኑ ለምንድነው ፍልስፍና ለመማር የፈለግከው ?”
“ምክንያቱም መላው ሕይወቴን ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ፡፡ ስለዚህም ስለእነሱ ሁሉንም ነገር ማወቅ እፈልጋለሁ”

“የፈጣሪ ያለህ…” አሉ፣ “ይሄ ነው ምክንያትህ ? በቃ ? አንድ ሰው የፈላስፎችን ሐሳብ ለመዋጋት በሚል ፍልስፍና እንደሚያጠና አናውቅም ነበር !!! ይሄ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ነገር ነው”

“እስከዛሬ ካልሰማችሁት እንግዲህ አሁን ከእኔ ስሙታ … ከፈላስፎች ጋር ፍልሚያ እገጥማለሁ - እድሜ ልኬን፡፡ ለዚህ ደግሞ ፍልስፍና ማጥናት አለብኝ፡፡ የፍልስፍና #የክርክር ስልቶች በጣም ነው የሚጥሙኝ፡፡ ስለዚህም የእያንዳንዱን ፍልስፍና የክርክር ነጥቦች በጥልቀት መመርመር እፈልጋለሁ፡፡

ጠልቄ ማየት እሻለሁ፡፡ ዋንኛ ዓላማዬ ግን ፈላስፎችን መፋለም ነው፡፡ ምክንያቱም ከልምዴ እንዳየሁት አንድም የበራለት (Enlightened) ፈላስፋ የለም፡፡ እንዲሁ ነው በቃላት የሚጫወቱት፤ በአመክንዮ ጅምናስቲክ የሚተጣጠፉት፡፡ መቼም ከአንጎላቸው በላይ ወጥተው አያውቁም፡፡ በአንጎላቸው ትልልቅ ሥራዎች ሰርተዋል - ግን አእምሮ ብቻ ሆነው ቀርተዋል”

ነገር ግን … ያው … እብድ ብጤ መሆኔን ስለሚያውቁ፣ “ለነገሩ እንደዚህ አይነት ነገር እንደምታደርግ የሚጠበቅ ነው” አሉ፡፡

ቢሆንም የቻሉትን ያህል ሞከሩ፡፡

“ጊዜ አለ … እስቲ አስብበት … ዩኒቨርሲቲዎቹ እስኪከፈቱ አንድ ወር ያህል ጊዜ ስላለ አስብበት” አሉኝ፡፡

“አንድ ወርም፣ አንድ ዓመትም፣ አንድ ሕይወትም ለውጥ የለውም - ምክንያቱም እኔ አልመርጥም፡፡ ይህ የእኔ ምርጫ አልባው ኃላፊነቴ (choiceless responsibility) ነው”

ከአጎቶቼ አንዱ እንዲህ አለ [የዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ነው]፣ “ከእሱ ጋር መነጋገር በጣም ከባድ ነው፡፡ ምንም ትርጉም ያላቸው የማይመስሉ ቃላት ነው የሚጠቀመው፡፡ ምርጫ አልባነት … ኃላፊነት … ንቃተ ሕሊና - እነዚህን ነገሮች ከሕይወት ጋር ምን ያገናኛቸዋል ? እንዴ … ገንዘብ ያስፈልግሃል፣ ቤት ያስፈልግሃል - #ቤተሰብ መስርተህ ቤተሰብህን መደገፍ አለብህ”
“ቤተሰብ አልመሰርትም፤ ቤትም አይኖረኝም፣ ማንንም አልደግፍም” አልኩት፡፡

እናም ማንንም አልደግፍም፤ ቤትም አልሰራሁም፡፡ የዓለማችን የመጨረሻው ደሃ ሰው ማለት እኔ ነኝ፡፡

ዶክተር፣ ኢንጂነር ወይም ሳይንቲስት ሊያደርጉኝ ሞክረው ስላልተሳካላቸው በጣም ተናደዱ፡፡

እናም ሊያስፈራሩኝ ሞከሩ፤ “ፍልስፍና የምታጠና ከሆነ ገንዘብ አንልክልህም” አሉኝ፡፡
“እንዲህ ማለትም አይጠበቅባችሁም፡፡ እኔም ራሴ አልቀበላችሁም፡፡ #ምክንያቱም የምማረው ራሴ የመረጥኩትን አይደለ ? ስለዚህ ራሴው እወጣዋለሁ፡፡ እናንተ ተማር ያላችሁኝን አልመረጥኩም፡፡ ስለዚህ ከእናንተ ገንዘብ መቀበል የማይታሰብ ነው፡፡ ለምን ብዬ ነው ገንዘብ ከእናንተ የምቀበለው ? ለምን ብዬ ? ብትሰጡኝም አልቀበልም” ስላቸው፣
ክው አሉ…

እንዴት ብሎ ይችለዋል ብለው ነበር - እኔ ግን ቻልኩት፡፡ ለሊት ጋዜጣ ላይ አዘጋጅ ሆኜ እሰራለሁ፡፡ ቀን ዩኒቨርሲቲ እማራለሁ፡፡ በዚህ መሃል ባገኘሁት አጋጣሚ እተኛለሁ፡፡
በስተመጨረሻ #ጥፋተኝነት ተሰማቸው፡፡ አባቴ፣ “እባክህን ይቅርታ አድርግልንና የላክንልህን ገንዘብ ተቀበል” እያለ ይፅፍልኛል፡፡

በፖስታ ቤት የሚልኩልኝን የገንዘብ ማዘዣ መልሼ እልክላቸዋል፡፡ አንድ ቀን አባቴ ዩኒቨርሲቲ ድረስ መጥቶ፣ “ይቅርታ አታደርግልንም ? እባክህን ሁሉን ነገር እርሳው” አለኝ፡፡

“ይቅር ልል እችላለሁ፡፡ ግን መቼም አልረሳውም” አልኩት፣ “ምክንያቱም በገንዘብ አስገድዳችሁ የማልፈልገውን ትምህርት እንድማር ልታደርጉኝ ሞክራችኋል…” ለእነሱ ገንዘብ ትልቅ ነገር ነው፡፡

“ከእኔ ይልቅ ገንዘባችሁ ነው ያሳሰባችሁ፡፡ እናም አስፈራራችሁኝ፡፡ ከእናንተ ገንዘብ አልፈልግም፡፡ እዛው ያዙት ብራችሁን፡፡ እኔ በደምብ እየኖርኩ ነው”
አባቴ ገንዘቡን የማትቀበለኝ ከሆነ ከዚህ አልሄድም አለ፡፡

በእኔ ምክንያት ማንም ሰው ጥፋተኛነት እንዲሰማው ስለማልፈልግ ገንዘቡን ተቀበልኩት፡፡

Source: Osho
#ኦሾ and please

Telegram: Contact @EthioOsho

25/10/2022

"ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው!"
❤ ❤ ❤
#በፍቅር በተሞላ ልብ መኖር እጅግ አስፈላጊ ነው።የፍቅር አመለካከት ሁላችንም ውስጥ ሊኖር ይገባል።ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው፤በፍቅር ልብ ውስጥ ጥልቅ የደስታ ስሜት ይኖራል።ትንሽ ፍቅር ለሰው ከለገሷችሁ በኃላ የሚሰማችሁ የሀሴት ስሜት አስተውላችሁ ታውቁታላችሁ?
መስፈርት በሌለው ፍቅር(unconditional love) ወስጥ ሆናችሁ የሚኖረውን ሰላም አስተውላችሁ ታውቃላችሁ?
ንፁህ ፍቅር ሊኖር የሚችለው በምክንያቶችና በመሥፈርቶች ካልታጀበ ብቻ ነው፤በሁኔታ የሚወሰን ፍቅር (conditional love) #ፍቅር አይደለም የማታውቁትን ሰው መንገድ ላይ ፊት ለፊት ፈገግታውን ተመልክታችሁ የሚሰማችሁን ደስታ አስተውላችሁታል?
የወደቀን ስታነሱ የደከመን ስትረዱ የታመመን አበባ ስታበረክቱና ስጠይቁ የሚሰማችሁ የደስታ ስሜት ወሰን የለውም፤ ይህን የምታደርጉት አባታችሁ ወይም እናታችሁ ስለሆኑ አይደለም በሰውነት የምታበረክቱት ስጦታ ለእናንተ በተራው ታላቅ ደስታና እርካታና ስለሚያበረክት እንጂ።ለዚህም ነው ሰብአዊነት ሊወለድ የሚችለው ከፍቅር ልብ ነው የምላችሁ።

#ኦሾ

https://t.me/EthioOsho

https://t.me/Ethio_Osho_group
https://t.me/Ethio_Osho_group

24/10/2022

ከጨለማ ባሻገር የብርሃን ፀዳል አለ✨

"እስቲ ትንሽ ስለራሳችን እንማማር ሰዎች ከህይታችሁ ሊወጡ ሲያስብ መጀመሪያ የሚሰማችሁን ነገሮችን እንደገና የናንተን ድክመት ነቅሰው በማውጣት እና አስፍተው በመተንተን ነገሮች ሁሉ ፤ እንዳከተመላቹ ተስፋም እንደሌላቹህ በቀጥታም ይሁን በተለያዩ አጋጣሚዎች ይነግሯቹሀል ። ደስ የማይል ስሜት እንዱሰማቹህ የደርጋሉ ፤ እናንተ ግን ይህን ስሜት በተቃራኒው ማየት አለባችሁ ፤ የሚሰማቹህን ያንን ስሜት አትፍሩት ። የቻላቹሁትን ያህል እዘኑ ። ነገር ግን በውስጥ ህሊናቹህ ነገሮች እንደሚያልፍ የሚነግራቹህን ጥቂት ጥንካሬ በውስጣቹህ ያዙት ። ስሜቱ ተመላልሶ ተመላልሶ ይመጣል ። እናም እራሱን ይገልፅ ዘንድ ፍቀዱለት እንደ ጥንካርያቹህ መጠን ጊዜው አንድ ቀን አንድ ሳምንት አንድ ወር አንድ አመት ሊወስድ ይችላል ፤ ነገር ግን ከሩቅ የብርሃን ፀዳል ሲወጣ ታያላቹህ ። በርግጥ ሁሉም ነገር መጨረሻ ላይ መልካም ይሆናል ። ተዛንፎ የሚቀር ፤ ወድቆ የማይነሳ ሰው ተስፋ የቆረጠ ብቻ ነው ።

#ኦሾ

https://t.me/EthioOsho

https://t.me/Ethio_Osho_group
https://t.me/Ethio_Osho_group

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa