Visit Dire
ድሬ የፍቅር ሀገር
Dire
"ብዙ ሰው ይመሰክርላቸዋል"
24/03/2026
የድሬዳዋ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርማቸውን ለብሰው፣ ፈገግታቸውን አክለው ከምዕመናን ጋር ማዕድ ተጋርተዋል።
የሕዝብ ደህንነትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ በደስታም ሆነ በችግር ጊዜ ከማኅበረሰቡ ጎን መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል።
ሌሎችም ሊማሩበት የሚገባ ድንቅ ተግባር! 👏
20/03/2026
እናቱን ጡት በመቁረጥ😭😭
በገዛ እናቱና እህቱ ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነ
በሀዲያ ዞን ምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ፣ የገዛ ወላጅ እናቱን ጡት በመቁረጥ እና እህቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ።
እንደ ስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃ፣ ተከሳሹ ሰንበቱ መንገሻ የተባለ ግለሰብ ወንጀሉን የፈጸመው ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በገርቦ ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው። ግድያው የተፈጸመው አስቀድሞ በታቀደ እና እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ እንደነበር በችሎቱ ተገልጿል፦
ተከሳሹ የመኖሪያ ቤቱን በሮች በመቆለፍ እናቱን በሳንጃ አንገታቸውን፣ ሆዳቸውንና ጀርባታቸውን በመውጋት እንዲሁም ጡታቸውን በመቁረጥ ለህልፈት ዳርጓቸዋል።
ድርጊቱን አይታ የጮኸችውን እህቱን በተመሳሳይ ስለታም መሣሪያ ልቧንና ጀርባዋን በመውጋት ወዲያውኑ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርጓል።
የምዕራብ ባዳዋቾ ወረዳ ፖሊስ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ ጉዳዩ ለሕግ ቀርቧል። በችሎቱ ሂደት ላይ ዓቃቤ ሕግ የሐኪም የአስከሬን ምርመራ ውጤት እና ሌሎች ማስረጃዎች አቅርቧል።
ተከሳሹ ለፍርድ ቤት የሰጠው የእምነት ቃል ወንጀሉን መፈፀሙን አምነዋል ።
የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሾኔ ምድብ ችሎት በመጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፤ ተከሳሹ የፈጸመው ድርጊት እጅግ አሰቃቂ መሆኑን በማረጋገጥ በ1997 የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539(1-ሀ) መሠረት በሞት እንዲቀጣ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
መረጃው 👇
https://www.facebook.com/share/p/1bwEDsyZAn/
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Lagaharree
Dire Dawa