Islamic History
Spreading the Light through clarification
1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
ነገር ግን በክርስትና (በባይብል) ሙስሊምን መጠየቅ ሀጢያት ነው።
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
(2ኛ ዮሐንስ 1:9–11)
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
የእኛ እስልምና ይህ ነው።
¶
2ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ ለሚወጣ ሁሉ በክርስቶስም ትምህርት ለማይኖር ሰው አምላክ የለውም፤ በክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉት።
¹⁰ ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት ሰላምም አትበሉት፤
¹¹ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና።
06/11/2022
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
ወንድማችን አሊ መሐመድ (ቢራ) ወደ አኼራ ሄዷል
ከነበረበት ህይወት ወደ አላህ ተመልሶ መስጂዶችን በማስገንባት ላይ የነበረው ወንድማችን አሊ መሐመድ ባጋጠመው ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ወደ አኼራ አልፏል::
አላህ ምህረቱን ይለግሰው፣ ተውበቱን ይቀበለው፣ ማረፊያውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግለት
ለቤተሰቦቹም አላህ መፅናናቱን ይወፍቃቸው
19/10/2022
ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላን ማን ይተካቸው ይሆን???
ሀገራችን በሞት ያጣቻቸው ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላ የሀገራችን ትልቅ የኢልም ዋርካ ነበሩ:: ብቻቸውን ትልቅ የኢልም ተቋም ነበሩ::
የምድር ኮከብ የሆኑት ኡለሞች በሞት እየረገፉ መሄዳቸው ቀጣዩ ትውልድ ላይ ትልቅ አደጋ መደቀኑን የሚያመላክት ነው::
እድሜያቸውን ሁሉ ለኢስላም የሰጡ፣ ጭንቀታቸው እና ልፋታቸው ሁሉ ለአኼራቸው የሆኑ አሊሞቻች ሲያልፉ አሻራቸው በትውልዱ ላይ የሚታይ ነው የሚሆነው::
የዛሬው የሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላ ስርዓተ ቀብር ላይ የተገኘው ህዝብ እሳቸው ምን ያህል ህዝቡ ልብ ውስጥ የነበሩ ፣ትልቅ አሻራ በህዝቡ ላይ አሳርፈው ያለፉ መሆናቸውን የሚያመላክት ነው::
ኡለሞች ሲያልፉ ብቻ ሳይሆን በህይወት እያሉም ማክበር የኡማው ባህሪ ሊሆን ይገባል::
እንቁ የሆኑ ኡለሞቻችንን በሞት እያጣን መገኘታችን እና እነዚህን ታላላቅ መሻይሆች ለመተካት ቀጣዩ ትውልድ ቆም ብሎ ካላሰበ ቀጣዩ ጊዜ አሳሳቢ ይሆናል::
ትውልዱ ከእውቀት እየራቀ በአለማዊ ህይወት እየተጠመደ ባለበት ወቅት የነብያት ወራሽ የሆኑት አሊሞችን በሞት ማጣት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆነብን ነው::
ህይወታቸውን ለኡማው የሰጡ ኡለሞች ሲያልፉ እነሱን የሚተኩ ኡለሞች እየተመናመኑ መሄዳቸው እና ተተኪዎችን ለማፍራት የሚሰራ ጠንካራ አካል አለመኖሩ ትልቅ ፈተና ውስጥ መኖራችንን ያሳያል::
በተለይ ባለሃብቱ እና የንግዱ ማህበረሰብ እጅግ የተረሱትን የሀገራችን ኡለሞችን በህይወት እያሉ ማክበር እና መንከባከብ ተተኪ እንዲያፈሩም በደንብ ሊረዷቸው እና ሊያግዙ ይገባል:
የዱንያ ቆይታቸውን ሙሉ ኡማውን በመጥቀም፣ በማስተማር እና በማገልገል ያለፉ አሊሞች ምንኛ ታደሉ?? እነዚህንስ ማን ይሆን የሚተካቸው??
ሙፍቲ ሼይኽ አደም ቱላን አላህ በፊርዶስ ያሳርፋቸው
16/10/2022
ጊዜ እንዲህ ነው!
አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሙስሊሙ ተቋም ይስተካከልልን የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኡስታዝ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ ይሰቃዩ ነበሩ::
ዛሬ ቀኑ ተቀይሮ እሳቸው የታሰሩበት ተቋም መሪ ሆነው ከቀድሞ የአሳሪዎቻቸው ተምሳሌታዊ መሪ ጋር ተገናኝተው እንዲህ በክብር አናግሯቸዋል !
Click here to claim your Sponsored Listing.