Amaizing GRACE

Amaizing GRACE

Share

ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው የሞተውና የተነሳው እኛ በእርሱ በማመን በፀጋ ብቻ የዘላለም ህይወት እንድናገኝ ነው።

26/10/2025

“የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤”
— ቆላስይስ 3፥16

1. የእግዚአብሔር ቃል (ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ) በሙላት
ይኑርባችሁ፦
👉የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም አገልግሎት እና ህይወት መሰረት ነው። ከቃሉ የተቀዳ መዝሙር፣ ስብከት፣ ትምህርት፣ ጸሎት....ሲሆን ውጤታማና ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ይሆናል።

2. በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገስጹ፦
👉የእግዚአብሔርን ቃል እና ተግሳጽ በጥበብ ማስተላሉፍ ውጤታማ ያደርጋል። ማስተማሩና መገሰጹ ላይ ብቻ ሳይሆን በጥበብ ከማድረጋችሁ ላይም አተኩሩ። ብዙዎች ይገስጻሉ ግን ያለ ጥበብ ስለሚያደርጉት ማቅናት አይችሉም። ውጤታማ አይሆኑም። ስንማማርና ስንገሳሰጽ በጥበብ ይሁን።

3. በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊ ቅኔ...ለእግዚአብሔር ዘምሩ
👉መዝሙር ለማንም ሳይሆን ለእግዚአብሔር ብቻ ነው ለእርሱ የምንዘምረውም በልባችን (ከልብ የመነጨ) ነው። መንፈሳዊ ቅኔ የሚለው Sensitive መሆንን ጭምር የሚያመለክት ነው።

ከቻላችሁ መልዕክቱን ካነበባችሁ በኋላ ከ3-5 ደቂቃ በማስተዋል በአንድ መዝሙር ከልባችሁ ለብቻችሁ ለእግዚአብሔር ተቀኙ።
ስለታዘዛችሁ ተባረኩ።

22/08/2025

#የተነሳው እና #ያረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ

ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አማኞች የስጋ ትንሳኤ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሲያስተምር ቀጥሎ ያለውን ሃሳብ ተናገረ። ሙሉ ምዕራፉ የሚያወራው ስለ ስጋ ትንሳኤ እንደሆነ ባለመርሳት ቀጥሎ ያለውን አንብቡ።

“ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥23

👉በማይሞትና በማይበሰብስ አካል በክብር የተነሳውና ወደ ሰማይ ያረገው በኩሩ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ካስረዳ በኋላ በመምጣቱ (ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ) ግን ለእርሱ የሆኑት (ማርያምን ጨምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑት በሙሉ) በማይሞትና በማይበሰብስ የትንሳኤ አካል በመነሳት ባለ ተራ ይሆናሉ ይለናል። ስለዚህ እርሱ ከመምጣቱ በፊት በትንሳኤ አካል ከሙታን የተነሳና እንደ እርሱ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ማንም የለም። ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ማርያምም ከሙታን ተነስታ አርጋለች ብሎ ማስተማር የእግዚአብሔርን ቃል መካድ ነውና ወደ ቃሉ እንድትመለሱ እመክራችኋለሁ። ቀጥሎ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በማስተዋል ተመልከቱት።
“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ #ማንም #የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።”
— ዮሐንስ 3፥13
👉ማንም የሚለው ቃል ማርያምንም ይጨምራል። እርሷም ከሌሎች በክርስቶስ ከሆኑ ወንድሞቿና እህቶቿ ጋር በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ መምጣት ጊዜ የሚጠብቃትን የስጋ ትንሳኤ ገና ትጠብቃለች። መድሃኒቴ ያለችው ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች አማኞች ብቻ ሳይሆን ለእርሷም አዳኟ ነውና።

29/07/2025

ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥያቄ የሆነባችሁ ሃሳብ ካለ ኮሜንት ላይ አስቀምጡ።

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa