DeritaTech Solution
DeritaTech Solution is a Technology page providing IT tips, Tricks and How to videos.Follow us.
21/05/2026
አዲሱ BYD ያስተዋወቀው ክሪክ ለምኔ ያለው እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪ!
የቻይናው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ BYD ሰሞኑን ዓለምን እያነጋገረ ያለ አዲስ ነገር ይዞ ተከስቷል ፤ ይሄውም ኩባንያው ሰሞኑን ባስተዋወቀው የBYD leopard Bao 8 የተሰኘ ተሽከርካሪው አዲስ ስሪት ላይ ይፋ ያደረገው Ultra fully active hydraulic suspension ቴክኖሎጂ ፤ ይህ ተሽከርካሪ እያንዳንዱን ጉማዎቹን በየተራ ክፍ በማደግ ክሪክ ሳያስፈልገው በራሱ አየር ላይ በመቆም ጎማ መቀየር እንድንችል ወይም በሶስት ጎማዎች ብቻ ሚዛኑን ጠብቆ መሄድ እንዲችል ያስችላል።
ይህ ግንቦት 13,2026 የተዋወቀው BYD Leopard 8 Flash Charging Edition የሚጠቀመው አዲሱ ultra fully active hydraulic suspension ቴክኖሎጂ ተሽከርካሪው በገደላማ ና እጅግ አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ያለ ችግር ጎማዎቹን በየተራ እስከ 300ሚሊ ሜትር ወይም 30ሴንቲ ሜትር ድረስ በማንሳት እንዲጓዝ የሚያደርግ ሲሆን አሽከርካሪው የፈለገውን ጎማ መርጦ እንዲነሳ ማዘዝ ይችላል።
ይህ ቴክኖሎጂ Yangwang U9 Supercar በተሰኘው እጅግ ቅንጡ በሚባሉ የቢዋይዲ ተሽከርካሪዎች ምድብ በሚካተተው ተሽከርካሪ ላይም እንዳለ ተነግሯል ፤ ይህ ሱፕር ካር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ የመዝለል አቅም እንዳለውም ታውቋል።
BYD የመጀመርያውን Leopard bao 8 በይፋ ያስተዋወቀው April 8,2024 እንደነበር ይወሳል።
13/05/2026
አሁን ላይ በብዙዎቻችን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ለእያንዳንዷ ነገር እንደ ግል አማካሪ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ChatGPT እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር November 2022 ላይ ድንገት ተከስቶ የጉግልን ሰርች ዶሚናንስ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል ፤ ቻት ጂፒቲን ወይም ሌሎች ኤአይ ቻት ቦቶችን ሰዎች ከጎግል በበለጠ እንዲመርጧቸው የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ፤ Google Search ትንሽ አድካሚ ና ጥረት የሚጠይቅ ነው ፤ ጉግል ላይ ሰርች ላደረግናቸው ነገሮች ለኛ ተስማሚ የሆነውን ና ለፍለጋችን በጣም ቅርብ የሆነውን የፍለጋ ውጤት ጉግል ከሚሰጠን በሺዎች የሚቆጠሩ ውጤቶች መካከል መምረጥ ይጠበቅብናል ፤ ቻት ጂፒቲ ላይ ስንሄድ ያለ ምንም ልፋት ለፍለጋችን ቀጥተኛ ምላሽ ከማግኘታችንም ባሻገር ልክ ሰዎችን እንደምንጠይቀው በውይይት ቃና የምንፈልገውን ነገር መጠየቅ ስለሚያስችለን ነው።
ChatGPT ከ ጉግል አንጻር ሲታይ ምን ልዩነት አለው? ምን አይነት ጥያቄዎችስ መጠየቅ የለብንም? ጉግልን ሊተኩ የሚችሉ አንዳንዴም የተሻሉ አማራጭ search engines የትኞቹ ናቸው ? እነዚህ እና ሌሎች መሰል መረጃዎችን የያዘውን ቪዲዮ ይመልከቱ!
ChatGPTን በፍጹም መጠየቅ የሌለብን ጥያቄዎች! Google vs ChatGPT |ChatGPTን መቼ እንጠቀም? |Google Alternatives |OpenAI | | | |EthioComputer School| Useful Videos : Exce...
07/05/2026
Keylogger ምንድን ነው?
Keylogger ወይም Key Stroke logger ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ የምንጽፋቸውን ሁሉንም key strokes ማለትም ከኪቦርድ ታይፕ የምናደርጋቸውን characters/Text ሁሉ ፓስወርዳችንን ሳይቀር ከትቦ የሚይዝ በHardware ወይም በSoftware መልክ የተዘጋጀ tool/መሳሪያ ነው። ሶፍትዌር ኪይሎገር ለስልክም ለኮምፒውተራችንም በቀላሉ online ልናገኝ እንችላለን።
Keylogger ብዙ ግዜ እና በአብዛኛው የሚታወቀው በሃገሮች ወይም በሳይበር ጥቃት አድራሾች የሰዎችን ወይም የተቋማትን መረጃ ለመስረቅ ወይም ለስለላ (Espionage) ተግባር በመዋል ሲሆን ከዚህ ባለፈም ለበጎ አላማ ጥቅም ላይ እንደሚውል ይነገራል።
Keylogger ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው በጎ አላማዎች / Legitimate uses የተወሰኑትን ስንመለከት ፡
1. Employee Monitoring ፡ ቀጣሪዎች በሰራተኞቻቸው ኮምፒውተር ላይ Keylogger ጭነው የመረጃ ስርቆትን ፣ የሰራተኛውን ምርታማነት እንዲሁም ለፖሊሲዎች ተገዢ መሆነቸውን ለመከታተል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
2. Parental Control : ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት ኪይ ሎገር ያለው የሞኒትሪንግ ሶፍትዌር ሊጠቀሙ ይችላሉ።
3. IT Support & Troubleshooting : የአይቲ ባለሞያዎች የሶፍትዌር ወይም የሃርድዌር ችግሮችን ለማወቅ ና ለመፍታት እንዲረዳቸው keylogger ጭነው የተጠቃሚዎችን input ሊከታተሉ ይችላሉ።
4. Software Debugging & Testing ፡ **ሶፍትዌር አልሚዎች ለቴስቲንግ ና logical errorsን ለመለለየት ይጠቀሙበታል።
5. CyberSecurity Research : የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎች እና ethical hackers ለpenetration testing ይጠቀሙበታል።
6. Law Enforcement : የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ምርመራ ወቅት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ለሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።
ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ keylogger ይኖራል ብለን ከጠረጠርን ምን እናድርግ?
Software Keylogger ይኖራል ብለን ከፈራን ፤ ኮምፒውተራችን Task manager ላይ ሄደን ለየት ያሉ ና የማናውቃቸው እንግዳ ፕሮሰሶች ካሉ ምንነታቸውን አጣርተን ማስቆም ፣ ከኛ እውቅና ውጪ በራሳቸው የሚነሱ Startup ፕሮግራሞች ካሉ እነሱን ማስቆም ፤ ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ የተጫኑ የማናውቃቸው ሶፍትዌሮች ካሉ ምንነታቸውን አጣርቶ እርምጃ መውሰድ እኒዱም ኮምፒውተራችንን full virus እስካን ማድረግ።
Hardware Keylogger ይኖራል ብለን ከጠረጠርን በኪይቦርድ ና በኮምፒውተሩ USB port መካከል የተሰካ የማናውቀው ነገር ካለ መጠርጠር ወይም ነቅሎ ሌላ ኪይቦርድ መጠቀም።
Click here to claim your Sponsored Listing.