ZD trading
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ZD trading, Public & Government Service, Addis Ababa.
17/01/2026
06/01/2026
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ የገናን በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ
እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ ።
የገና በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አንዱ ነው ። በዓሉ በሃይማኖት ተቋማቱ ሃይማኖታዊ ስርዓትና ትውፊት መሰረት ይከበራል ።
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በሚከናወኑ የዝማሬና የመንፈሳዊ ፀሎት መርሐ ግብሮች አማካኝነት በልዩ ሁኔታ ይከበራል ። ይኸንን በጉጉት የሚከበር በዓል ለማክበር እንኳንም በሰላም አደረሳችሁ ።
በባለፈት ወራት የዞናችንን ህዝብ ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ሰፋፊ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ። የአርሶ አደራችንን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል በተደረገው ተከታታይ ስራ ውሃ ፣ መሬት ና ጉልበትን አጣምሮ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ያለ አርሶ አደር እየተፈጠረ ነው ። በበጋ ወራት ስንዴ ማምረት አፈፃፀሙ እያደገ መጥቷል ። ግብርናውን ለማዘመን እየተደረጋ ያለው ጥረትም አበረታች ውጤት እየታየበት ነው ። በቀጣይ በትኩረት ይዘን የምንሰራው ተግባርም ይሆናል ።
በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለአልሚ ባለሃብቶች ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት በዘርፉ ውጤታማ ስራ እየሰራን እንገኛለን ። የተመረጡና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን በመሳብ የተጀመረው ስራ እጅግ አበረታች ነው ። በተለይ አረርቲ ከተማ አስተዳደር ፣ ቡልጋ ከተማ አስተዳደር ፣ አንጎለላና ጠራ ወረዳ እና ለሚ ላይ ለአልሚ ባለሃብቶች በቂ መሬት አዘጋጅተን ባለ ሃብቶችን እያስገባን እንገኛለን ። ሌሎች አልሚ ባለሃብቶችም በዞናችን በሁሉም አካባቢ ያለውን ፀጋ ተጠቅማችሁ ለማልማት ብትመጡ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የምናስተናግዳችሁ መሆኑን አረጋግጣለሁ ።
በማዕድን ዘርፍ በዞናችን ያለንን እምቅ አቅም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አማካኝነት ተጠንቷል ። በርካታ አይነት ማዕድናት በዞናችን እንደሚገኙም ተረጋግጧል ። በዘርፉ ለመሰማራት ለምትፈልጉ ባለሃብቶቻችን ከዚህ በፊት እንደተለመደው በትብብር ለመስራት ቁርጠኝነታችን እናረጋግጣለን ።
በቱሪዝም ዘርፉም ዞናችን እምቅ አቅም ያለው ዞን ነው ። ሰው ሰራሽ ፣ ተፈጥሮ አዊ ና ታሪካዊ የመስህብ ሃብቶቻችን ሰፊ ናቸው ።
የህዝባችን ሰላም ወዳድነት እና በሁሉም ዘርፍ የተካሄዱ የኢንቨስትመንት ስራዎችን በመጠበቅ ያለው አርዕያነት የሚደነቅ ነው ። ህዝባችን ልማት ወዳድ ፣ አስተዋይና ሰላሙን አብዝቶ የሚሻ ድንቅ ህዝብ ነው ። አብሮነትን በተግባር ያሳየ ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ምሳሌ መሆኑን አሳይቷል ። ገጥሞን የነበረውንም የሰላም መታጣት ለመፍታት የሄደበት ብስለት በእጅጉ የሚያስመሰግን ነው ። በተሰራው ተከታታይ የህዝብ ወይይት ሁሉም ወደ ሰላማዊ ውይይት ብቻ መምጣት እንዳለበት አቋም ወስዷል ።
በቀጣይ ወራትም በልማት ና ሰላም ፣ የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ጋር የተያያዙ ተግባራት በቁርጠኝነት የምንተገብር ይሆናል ።
በመጨረሻም በዓሉን ስናከብር ጧሪና ተንከባባቢ የሌላቸው ምስኪን ወገኖቻችንን በመርዳትና በማገዝ መሆን አለበት ።
መልካም የገና በዓል
Click here to claim your Sponsored Listing.