Leniza
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Leniza, Digital creator, Addis Ababa.
የዐቢይ ምጽዋተኞች
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ(በረከታቸው ይደርብንና) በነበሩ ዘመን አንድ ሰው እሳቸውን ሰድቦ መጽሐፍ ያሳትማል፡፡ ቤተ ክህነቱ ይከሰዋል፡፡ እሱም ይታሠራል፡፡ በኋላ አቡነ ጳውሎስ ይሰማሉ፡፡
“ለምን ከሰሳችሁት” አሉ
“እርስዎን ሰድቦ፣ መጽሐፍ አሳትሞ እየሸጠ ነው” ብለው መጽሐፉን አምጥተው አሳዩዋቸው፡፡
“ለመሆኑ ልጁ ሥራ አለው” አሉ
“ኧረ የለውም፤ ይሄንኑ እየሸጠ ነው የሚበላው”
“ሊሸጥ የሚችል ስምስ አለው”
“ኧረ ስሙ መንገድ ላይ ወድቆ ቢገኝ ማንም አያነሣውም”
“በሉ ተውት፤ ከሚርበው ስሜን ሽጦ ይብላ፤ ለእኔም እንደ ምጽዋት ይቆጠርልኛል፤ እሱኮ የሚሠራው ሥራም፣ የሚሸጠው ስምም ስለሌለው ነው” አሉ ይባላል፡፡
አሁን አሁን የዐቢይን ስም ሽጠው የሚበሉ ምጽዋተኞች ብቅ ብቅ ብለዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁለት ነገር የላቸውም፡፡ አንድም ሥራ የላቸውም፤ አንድም የሚሸጥ ስም የላቸውም፡፡ ያላቸው አማራጭ የዐቢይን ስም ሸጠው መብላት ነው፡፡ ልጆቻቸውም በዚህ ሽያጭ ነው የሚያድጉት፤ ቢልም የሚከፍሉት ከዚሁ ሽያጭ ነው፡፡ ለዐቢይ በዋናነት የሚጸልዩት እነዚህ ሰዎች ናቸው፡፡ ስሙ እንጀራቸው ነዋ!
እነዚህ የዐቢይ ምጽዋተኞች ናቸው፡፡
ስሙ እንጀራቸው ነው፡፡
ስሙ ልብሳቸው ነው፤
ስሙ የታክሲ ሂሳባቸው ነው፡፡
ያሳደጋቸው የዐቢይ ስም መሆኑን ልጆቻቸውም ያውቃሉ፤ እናም ምኞታቸው አሳዳጊያቸውን ዐቢይን ማየት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ፡-
ለአንዳንዶች በታላላቅ ፕሮጀክቶች የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፤
ለአንዳንዶች የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ተመቻችቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በሪሞት የሚሠሩት ሥራ ተዘጋጅቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በኮሪደር ልማት የሥራ ዕድል አግኝተዋል፤
ለአንዳንዶች በሌማት ትሩፋት የገቢ ምንጭ ተፈጥሮላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በአረንጓዴ ዐሻራ የእንጀራ ገመድ ተዘርግቶላቸዋል፤
ለአንዳንዶች በስንዴና በሩዝ አብዮት ሀብት ተትረፍርፎላቸዋል፤
ለአንዳንዶች ቤት ተሠርቶላቸው ሱቅ ተሰጥቷቸዋል፤
ለነ እንቶኔ ደግሞ ስሙን ሸጠው የመተዳደር የሥራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፤
እናም፤ ምጽዋተኞችን ተዋቸው፤ እዘኑላቸው፤ አትፍረዱባቸው፡፡
ስም በመሸጥ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው “የዐቢይ ምጽዋተኞች” ናቸው፡፡
ፀሀፊ:ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
18/05/2026
ዘመን ተሻጋሪ እና ሀገርን በድል፣ በክብር ወደከፍታ አሻጋሪ የሆነው የክቡር ጠ/ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት መፅሀፍ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ በአቡዳቢ በድምቀት ተመረቀ።
*
*
*
*
*
Click here to claim your Sponsored Listing.