Vision Properties
Real Estate Sales Advisor
24/05/2026
ፍፁም ዘመናዊ የሆነ አፓርትመንት እና ዘመናዊ መንደር እንዲያገኙ መርዳት ዋና ስራችን ነው
በዲኤምሲ ሪል እስቴት ደንበኞቻችን ዘመናዊ መኖሪያ ቤታቸውን አግኝተው ዘመናዊ ኑሮ እንዲኖሩ በማድረጋች እና ከህልማቸው ጋር በማዛመዳችን እንኮራለን። የህልማቸውን ቤት ከእኛ ጋር ሲያገኙ የሚሰማቸው የደንበኞቻችን እርካታ ሀሴታችን ነው! DMC Real Estate የቤት ፈላጊዎችን ፍላጎት እና የእርስዎን ህልም ለመረዳት እና በሂደቱ ውስጥ እርስዎን ለመርዳት እና ህልምዎን ለማሳካት ሁሌም ቁርጠኛ ነው።
ህልምዎ የሆነውን ቤትዎን ለማዬት እና ዘመናዊ መንደርዎን ለመጎብኘት ወይም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ቢሮአችንን ይጎብኙ!
ወይም
09-47-29-58-10
07-26-29-58-10
ይደውሉ።
ደስታዎ ከዚህ ይጀምራል
DMC Real Estate
join us
https://t.me/vgtcservice
Celebrating my 6th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉
18/05/2026
በሪል እስቴት አቅርቦት የሚያስደንቅ እና ፍፁም የቅንጦት እና የምቾት መንደራችን በHill Side Recidence ቅንጡ አፓርትመንት ቤቶችን እና የንግድ ሱቆችን በተለያየ የካሬ አማራጭ፣ 60% የባንክ ብድር እስከ 25 አመት በሚደርስ የመክፈያ ጊዜ ፣ እስከ 35% በሚደርስ ቅናሽ እና በ10% ቅድመ ክፍያ አቅርበናል።
ይህ መንደር እያንዳንዱን ፍላጎቶትዎን የሚያሟሉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ይዟል።
፦የመዋኛ ገንዳ
፦ስታንድ ባይ ጀነሬተር
፦የከርሰ ምድር ውሀ
፦የልጆች መጫወቻ
፦ላይብራሪ
፦የስብሰባ አዳራሾች
፦በቂ ሊፍቶች
፦በቂ መኪና ማቋሚሚ
፦ጅምናዝየም
፦ማራኪ እይታ
ለበለጠ መረጃ
09-47-29-58-10
07-26-29-58-10
DMC Real Estate
ደስታዎ ከዚህ ይጀራል!
03/05/2025
የአእምሮ ህመም ህክምና ምንነትና መለያ ባህሪያት
ክፍል አንድ
የአእምሮ ጤንነት የሰው ልጅ ትርጉም ያለው ሕይወት እና ጤናማ ግንኙነቶች እንዲኖሩት የሚያስችሉት መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡ የአእምሮ ህመም አንድ ፍቺ እንደሌለው፤ የሚደረስበት አንድ ግብ ያለው ሳይሆን እንደሂደት ሊቆጠር እንደሚችልም ይጠቀሳል፡፡
በዛሬው ዓምድ ባነሳነው የአእምሮ ህመምና ህክምና ርእስ ዙሪያ፤ ስለአእምሮ ህክምና ምንነት፣ ህመሙን እንዴት መለየት እንደሚቻል እና ተያያዥ ጉዳዩችን እንዳስሳለን፡፡
በዚህ ጉዳይ መረጃውን በማጋራት የተባበሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ትምህርት ከፍል ሐላፊ ዶ/ር ባርኮት ሚልኪያስ ናቸው፡፡
የአዕምሮ ህክምና ትምህርት ክፍል አመሰራረት
የአዕምሮ ህክምና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ50ዎቹ መጨረሻ (እአአ 1966) በውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ሥር እንደአንድ አነስተኛ ዘርፍ ሆኖ ነበር የተመሰረተው፡፡ የመሰረቱትም ከደች የመጡ ፕሮፌሰር ሮበርት ጊል የተባሉ የአእምሮ ሃኪም ናቸው፡፡
ከውስጥ ደዌ ህክምና ክፍል ወጥቶ ራሱን ችሎ የአዕምሮ ህክምና ክፍል የሆነው እአአ በ1973 ነው፡፡ እንደክፍል ሆኖ አገልግሎት ቢሰጥም፤ በስሩ የትምህርት መርሃ ግብሮች በተለይም የአእምሮ ህክምና ስፔሻላይዜሽን አልነበሩትም፡፡ በአእምሮ ህክምና ትምህርት ስፔሻላይዝድ ያደረጉ ባለሙያዎች ትምህርት መውሰድ ከጀመሩ ደግሞ 21 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡
ትምህርት ክፍሉ አገልግሎት የሚሰጥበት የራሱ ቦታ አልነበረውም፡፡ ነገር ግን በአዲስ አበባ ካሉ የተለያዩ ሆስፒታሎች ጋር የአእምሮ ህክምና አገልግሎትን ማስጀመርና አገልግሎቱን እንዲጠናከር ማድረግ ችሏል፡፡ በጳውሎስ ሆስፒታል እና በየካቲት 12 ሆስፒታል አገልግሎቱን በማስጀመርም ሰርቷል፡፡
እስካሁን ድረስ የቀጠለው ደግሞ በዘውዲቱ ሆስፒታል እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም አማኑኤል፣ የካ ኮተቤም የአእምሮ ህክምና አገልግሎትን ሰጥቷል፡፡ የትምህርት ክፍሉ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዜሽን ሆስፒታል ውስጥም የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የትምህርት ክፍል እንደመሆኑ በክፍሉ መማር ማስተማር ይከናወናል፣ ሳይንሳዊ ጥናቶች ይሰራሉ፣ የሕክምና አገልግሎትም አለው፣ ማህበረሰብ አገልግሎትም አንድ አካል ሆኖ ይተገበራል፡፡
እንደሆስፒታል ሲታይ የመጀመሪያ እና ለረጅም ጊዜም አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁንም ስፔሻላይዝድ የሆነ የአእምሮ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ አማኑኤል ሆስፒታል ብቻ ነው፡፡
ሆኖም የጥቁር አንበሳ ስፔሻይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አማኑኤል ሆስፒታል ላይ ከምስረታው ጀምሮ ያለውን ህክምና በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
የአእምሮ ህክምና ምንድን ነው ?
የአእምሮ ህክምና በጣም ሰፊ ነገር ነው፡፡ ሰዎች በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ጤናማ ሆነው ለመኖር ከሚያሥፈልጋቸው አንዱ ነገር ውስጥ ጤነኛ አእምሮ እንደመሆኑ ትኩረቱም እዚሁ ላይ ነው፡፡ ይህ ማለት የሰዎችን አመለካከት፣ ስሜታቸውን፣ ባህሪያቸውን ወይም ድርጊታቸውን በአጠቃላይ ጤናማ በሆነ መንገድ ህይወታቸውን መምራት እንዲችሉ ማብቃት ወይም ማገዝ ነው፡፡
የአእምሮ ጤና ሲባል የሚደረስበት አንድ ግብ ሳይሆን እንደሂደት ልንቆጥረው የምንችለው ነው፡፡ በመኪና ምሳሌ አድርገን ብንመለከት የሚደረስበት ቦታ ሳይሆን መኪናው የሚሽከረከርበት መንገድ አድርገን ልንመለከተው እንችላለን፡፡
አንድን ሰው በአእምሮ ጤነኛ ለማድረግ ሳይሆን ህይወቱን በተስተካከለ ሁኔታ እንዲመራ ለማድረግ ነው፡፡ ለምሳሌ የአለም ጤና ድርጅት የአእምሮ ጤናን ፍቺ፤ አካላዊ ጤና፣ የአእምሮ ጤና፣ ማህበረሰባዊ ጤና እና መንፈሳዊ ጤንነትም አለ ሲል ያስቀምጧል፡፡
ስለዚህ አእምሮ የሚባለው ክፍል ሰው ሕይወትን ሲመራ ስሜቱን፣ ድርጊቱን፣ ግንዛቤውን፣ ማመዛዘን መቻሉን ሁሉ በተገቢው ሁኔታ እየመራ ትርጉም ያለው ሕይወት እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ጤናማና መስተጋብር ኖሮት እንዲኖር የማድረግ ሂደት ነው፡፡ እርሱ ላይ የሚደረግ የትኛውም አይነት እገዛ እና ድጋፍ የአእምሮ ጤና ህክምና እንለዋለን፡፡
ህክምናው አሁን ማህበረሰቡ ውስጥ እንደሚታሰበው አይነት የአማኑኤል ተብላ የምትታሰበውን መድሃኒት መስጠት አይደለም፡፡ ግለሰቡን/ቧን ከመረዳት ጀምሮ ያለውም ህክምና ነው፡፡ ግለሰቧን/ቡን ማነጋገርም ሆነ መድሃኒት ማዘዝም ህክምና ነው፡፡
የንግግር ሕክምና አንዱ ሲሆን ከዛም አልፎ በአካባቢው ካሉ ሰዎች ጋር የተሻለ እገዛ እንዲያገኝ ማመቻቸት በራሱ እንደአእምሮ ጤና ህክምና እገዛ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ እነዚህን ሁሉ ባካተተ መልኩ የሚደረጉ እገዛዎች በሙሉ የአእምሮ ጤና ህክምና እንላቸዋለን፡፡
ዘርፉ በራሱ አወዛጋቢ ነገር አለው፡፡ ለምሳሌ የልብ ህክምና ሲባል አልፎ አልፎ የሚመጣ ነው ወይም ከመንፈሳዊ ነገር ጋር ይገናኛል ሲባል አይሰማም፡፡ የአእምሮ ህክምና ሳይንሱ በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደገ መምጣቱ በራሱ ሙያውን ልዩ ያደርገዋል፡፡
በተለይ የአእምሮ ህመም ተፈጥሯዊ ወይም አካላዊ ምክንያቶች ለአእምሮ ህመም የሚያጋልጡ አንጎል ውስጥ ግኝቶች አሉ፡፡ ህክምናውም ይበልጥ መድሃኒቶች ወይንም ደግሞ ከኤሌክትሪክ ንዝረት ጋር የተገናኙ ህክምናዎች የዘረመል ጥናቶቹን ጨምሮ የዘረመል ህክምና ለማድረግ ጉዳት የነበረበትን በማከም ረገድ ሳይንሱ በጣም አድጓል፡፡
ከቀደመው በበለጠ ተፈጥሯዊ የሆነ ፍች ያለው ማስረጃዎች ተገኝተዋል፡፡ ሳይንሱ ይበልጥ በምርመራ እና በጥናት ትኩረት እያገኘ በፍጥነት እያደገ ነው፡፡
አወዛጋቢ ነው የሚባለው ደግሞ አንጎል ውስጥ ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ የማናየው፣ የማንዳስሰው፣ በላቦራቶሪ ምርመራ የማናረጋግጠው ነው፡፡ ሁሉም ህብረተሰብ ስለአእምሮ ህመም የራሱ አመለካከት አለው፡፡
ስለሌላ ህመም ሳይንስ ከሚለው ውጭ ሌላ ሰው ብዙ ሊል አይችልም፡፡ ስለአእምሮ ህመም ግን ሁሉም ሰው የራሱ ለየት ያለ አመለካከት አለው፡፡ ዘርፉ ለተለያየ ህዝባዊና ግላዊ አመለካከቶች ወይም አስተያየቶች ክፍት ነው፡፡
ፍልስፍና፣ ስነአእምሮ፣ መንፈሳዊ ትምህርት፣ የማህበረሰብ ጥናት፣ ሜዲሲንም ሆነ እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ ብንመለከት ሁሉም የተለያየ አስተያየት ሊኖረው ይችላል፡፡
ዋናውና አስፈላጊ የሆነው ደግሞ የአእምሮ ህመም በባህል ጉዳይ በጣም ስሜታዊ የሆነ ጉዳይ መሆኑ ነው፡፡ አሜሪካ ወይም ወደምዕራባውያን ጋር የአእምሮ ህመም የሚታይበት መንገድ እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታይበት መንገድ ይለያያል፡፡
ምእራባውያን ጋር የአእምሮ ህመም የሚገለጥባቸው እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገለጥባቸው ምልክቶቹ ይለያያል፡፡ ከባህልና ከእምነት ጋር በጣም የተሳሰረ፣ የተቆራኘ እና ባህሉ ራሱ የሚገለጥበትን መንገድ ስለሚወስን ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ የማይታይ ባለመሆኑ ተግዳሮትም አለው፡፡ ባህሉም በጣም ይለያል ለግላዊ አስተያየትም የተጋለጠ ነው፡፡
የአእምሮ ህመም ሙያው አሁንም የሚያወዛግቡ፣ ብዙ ክርክር ያላቸው፣ ሳይንስ ግን ከቀደመው ጊዜ የበለጠ ትክክለኛ ህመም መሆኑን እያረጋገጠ መጥቷል፡፡
በዚህ ዘርፍ ያለው የተዛባ አመለካከት በሌሎቹ ላይ በዚህ መልኩ አይስተናገድም፡፡ በመሆኑም እንደባለሙያም፣ እንደአገልግሎቱ ተጠቃሚ ወይም እንደታማሚ በብዙ ጥያቄዎችና ማስረዳት የተሞላ ነው፡፡
የአእምሮ ሃኪሞች የሚጠየቁትን ያህል ወይም እንዳለው የተዛባ አመለካከት የልብ ወይም የቀዶ ጥገና ሃኪሞች ላይ አይስተናገድም፡፡ ስለዚህ እንደባለሙያም እንደዘርፍም፣ እንደአገልግሎቱ ተጠቃሚም ወይም እንደታማሚ በብዙ ጥያቄዎች፣ ማስረዳትና ማስተማር በየቀኑ የሚታለፍበት ዘርፍ ነው፡፡ ሰፊ በመሆኑም ማንም አንድ ፍቺ ሊያስቀምጥ አይችልም፡፡
የአእምሮ ህመምን እንዴት መለየት ይቻላል ?
የአእምሮ ጤንነት የሰው ልጅ ትርጉም ያለው ሕይወት እንዲኖር እና ጤናማ ግንኙነቶች እንዲኖሩት የሚያስችሉት እንዲሁም በዚህ ሂደት ውስጥ መሄድ መቻሉ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የተለያዩ እክሎች ሊገጥሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዶቹ አነስተኛ ሲሆኑ ሰው በራሱ ሊያልፈው ይችላል፡፡
የተለያየ መንገድ ተጠቅሞ ለምሳሌ ከሰው ጋር በመነጋገር፣ በራሱ ጊዜ ወስዶ በማመዛዘን፣ ወይም ሃይማኖታዊና እምነታዊ ዘዴዎችን ፈልጎ አልፎ አልፎ ከአእምሮ ጋር የሚፈጠሩ ተግዳሮቶችን ይሻገራል፡፡
ህመም ነው? ወይስ ህመም አይደለም? የሚለውን የሚለይበት መንገድ አለ፡፡ ሰው በጣም የተለመደው ህመም ላይ ሲመጣ ቸገረኝ ብሎ ከሚመጣበት ጭንቀትን እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ብዙ ሰው ጭንቀት የሚለውን ቃል ይጠቀመዋል፡፡ ማንም ፈተና ሲኖረው ልፈተን ስል ጨነቀኝ ይላል፡፡
በጣም ከባድ፣ የተቸገረበት ሥራን፣ ትዳርን ሁሉ መረበሸ የደረሰ የጭንቀት ህመም ያለበት ሰው ‹‹ጭንቀት›› የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡ ነገር ግን ጭንቀት ብቻ ስለሆነ በሽታ ነው ወይም ህመም ነው ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ ጭንቀቱ ህመም ደረጃ ደረሰ የምንለውና የአእምሮ ህመም ብለን የምንገልጸው ስሜቶቹ ወይም ድርጊቶቹ ከተለመደው በጣም ወጣ ያሉ ሲሆኑ ነው፡፡
ወጣ የሚሉት ለምሳሌ በየቀኑ ምን ያህል አዘውትረው ይመጣሉ፣ ምን ያህል በሰውዬው/ በሴትየዋ ቁጥጥር ውስጥ ናቸው፣ ምን ያህል አልፎ/ፋ መቆጣጠር ከሚችለው/ ከምትችለው በላይ ተጽእኖ እየፈጠሩበት/ሩባት ነው ? የሚለውን በመመልከት ነው ይህ ነገር የአእምሮ ህመም ነው ወይም አይደለም የምንለው፡፡
አንድ የሚወደውን ያጣ ሰው በጣም ተረብሾ ሊቆይ ይችላል፡፡ ከተወሰነ መጠን በላይ ሲሆንና ጫናው በጣም ለየት ያለ ሲሆን፤ ይሄ ነገር የአእምሮ ህመም ሊሆን ይችላል ብለን እንገምታለን፡፡ የምናያቸውን ነገሮች በባለሙያ አጢነን ከዛ በኃላ የአእምሮ ህመም መሆንና አለመሆኑን መለየት የምንችለው፡፡
በዚህ መንገድ ካየነው ሁሉም ከአእምሮ ጋር የተያያዘ ተግዳሮት/ ችግር ህክምና አያስፈልገውም፡፡ ህመም ነው ከተባለ ግን ሁሉም መታከም ይችላል፡፡ ስም የተሰጠው ህመም ከሆነ ባለሙያ አይቶ ያረጋገጠው ከሆነ መታከም ይችላል፡፡
ሊድን ይችላል ? ወይስ አይችልም ? የሚለውን ማየት የምንችለው አብዛኛው የአእምሮ ህመም (ክኖኒክ) የሚባል ነው፡፡ ማለትም አንዴ ሲከሰት ታካሚው ጋር ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው፡፡
በተለይ ካልታከመ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው፡፡ የአእምሮ ህመም ይጠፉና የማገርሸት ባህሪ ሊኖራቸው ስለሚችል አብዛኛውን ጊዜ ስናክማቸው ስኳር፣ ደም ግፊት ወይም አስም አይነት ለረጅም ጊዜ እየታከሙ ወይም እገዛ እያገኘ መቆየት ያለበት አይነት ህመም ነው፡፡
ከታከመ ግን ለውጥ ማምጣት የሚችል፣ የህመሙ ስሜቶችም አንዳንዴ ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ ሊቀረፉ የሚችሉ ናቸው፡፡ በተለይ አብዛኛው ከባድ ያልሆነ የአእምሮ ህመም ስሜቶቹን መቅረፍ እና ስሜቶቹን ማቅለል ይቻላል፡፡
አንዳንድ ህመሞች በተለይ በጊዜ ወደህክምና ያልመጡ ህመሞች ሲሆኑ በህክምናም ሙሉ ለሙሉ ለውጥ ለማምጣት ሊከብድ ይችላል፡፡ ነገር ግን በህክምና ከመጀመሪያውም ለውጥ በማምጣት የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ማድረግ ይቻላል፡፡
በቀጣይ ክፍል የአእምሮ ህመም ምልክቶች፣ የአእምሮ ህመም ደረጃዎቹ፣ የተዛቡ አመለካከቶች፣ የአእምሮ ህመም አጋላጭ ምክንያቶች እና ህክምና አሰጣጡን ጨምሮ ያሉ አጠቃላይ ጉዳዩችን አካትተን እናቀርባለን፡፡
Via College of Health Sciences Addis Ababa University
Click here to claim your Sponsored Listing.