Sello Media

Sello Media

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sello Media, Media/News Company, Addis Ababa.

20/05/2026

ፍርድ ቤት የሰጠው ምንም ዓይነት የቅጣት ውሳኔ በሌለበት ሁኔታ የፈጠራ ወሬዎችን እያቀነባበሩ ለሕዝብ ማቅረብ ራሱ የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ከባድ ስህተት ነው።

የፍትሕ መድረኩ የሕግ አዋቂዎችና የዳኞች መድረክ እንጂ የሶሻል ሚዲያ አክቲቪስቶች የውሸት ፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ አይደለም። በማኅበራዊ ሚዲያ የሀሰት ጩኸትና የፈጠራ ወሬ የሕግን ሂደት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት ከንቱ ሆኖ ይቀራል።

ኅብረተሰቡም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት እንዲህ ዓይነት የተደራጁ የሐሰት ወሬዎችን ውድቅ በማድረግ መረጃዎችን ከራሱ ከፍርድ ቤቱ ይፋዊ መዝገብ ብቻ እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን።

Photos from Sello Media's post 09/05/2026

በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ "ቃል መግባት" እንደ ባህል "ተግባር" ደግሞ እንደ ናፍቆት በነበረበት ዘመን ተወልደው ያደጉ እንደ ቡንካሾ ያሉ ግለሰቦች ዛሬ የሚታየው የተግባር ሩጫ ግራ ቢያጋባቸው አይገርምም።

ቡንካሾና መሰሎቹ "ያልሰራ በካርድ ይቀጣ" የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር እንደ ፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት ቢሞክሩም እውነታው ግን ከእነሱ የትችት አድማስ በላይ ርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ያልሰራን በካርድ ቅጡ" ሲሉ በባዶ ሜዳ ላይ ቆመው ሳይሆን በሰሩት ስራ ተማምነው ነው።

እንደ ቡንካሾ ያሉ ተቺዎች በጽሁፍና በንግግር ሲጠመዱ አመራሩ ግን የህዳሴውን ግድብ ውሃ ሞልቶ፣ ተራሮችን አልምቶና የከተሞችን ቆሻሻ ገፅታ በኮሪደር ልማት አጽድቶ በተግባር እየመለሰ ይገኛል።

ለቡንካሾዎች ፖለቲካ የቃላት ጨዋታ ነው ለአመራሩ ግን ፖለቲካ ማለት ህዝብን በስራ ማገልገል ነው።

ኢትዮጵያ ስንዴ ትልካለች ሲባል "የማይሆን ህልም" ነው ብለው ሲተቹ የነበሩ ወገኖች፣ ዛሬ ምርቱ መርከብ ላይ ሲጫን ለማየት አይናቸው ቢታወርም ታሪኩ ግን እየተጻፈ ነው። ቃልን በተግባር የመለወጥ ጥበብ ማለት እንዲህ ነው።

ቡንካሾ በፌስቡክ ገጹ "ቃል አልተጠበቀም" ብሎ ሲጽፍ በመሬት ላይ ግን ገበሬው በመስኖ ስንዴ ህይወቱን እየቀየረ ነው። ታዲያ ማነው መቀጣት ያለበት ? ቃልን በተግባር የገነባው መሪ ወይስ ሀቁን የካደው ተቺ?

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የደረሰችበት የዲፕሎማሲ ከፍታና የብሪክስ (BRICS) አባልነት እንዲሁም እንደ ዓድዋ መታሰቢያ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የንግግር ውጤቶች አይደሉም። እነዚህ ስራዎች የ"ቃል-ተግባር" ትርክትን በደም እና በአጥንት ያጸኑ ናቸው።

"በካርድ ቅጡ" የሚለው ንግግር ለቡንካሾዎች ማስፈራሪያ ሳይሆን ለሰራው አመራር የልበ ሙሉነት መግለጫ ነው።

በመጪው ጊዜ ህዝቡ ካርዱን በእጁ ሲይዝ የሚፈርደው በፌስቡክ ትረካ ሳይሆን በአይኑ ባየው ልማት ነው። የቡንካሾ ጽሁፎች በአየር ላይ እንደሚበን ጢስ ሲጠፉ፣ የአመራሩ የልማት አሻራዎች ግን ለትውልድ የሚሻገሩ ሀውልቶች ሆነው ይቆማሉ።

ስለዚህ ህዝቡ ካርዱን የሚጠቀመው ቃልን ወደ ተግባር ለቀየረ ኢትዮጵያን ከአፈር ወደ ብርሃን ላወጣ አመራር እውቅና ለመስጠት መሆኑ አያጠራጥርም።

ቡንኬ ከፌስቡክ ትችት ውጪ ዕቅድ እና ራዕይ የሌለ ሰው ነች !

05/05/2026

ፍርድ ቤት የያዘውን ጉዳይ በሚዲያ ጋጋታ ለማሸነፍ ለምን ታሰበ?
የስዩም ተሾመ ሚዛናዊነት የጎደለው ውንጀላ!

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1238/2013) ይህ አዋጅ በሚዲያና በፍትህ አካላት መካከል ያለውን ግንኙነት በዝርዝር ያስቀምጣል። መገናኛ ብዙሃን በፍትህ ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ሲዘግቡ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊና የሕግ የበላይነትን ያከበሩ መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማል።

ፍርድ ቤቶች የዜጎች የመጨረሻ የመብት ማስከበሪያ ናቸው። ፍርድ ቤቶች በሕግ አውጭው አካል አስቀድመው የወጡ ሕጎችን የመተረጎም ሥልጣን የተሰጣቸው በየትኛውም አካል ተፅዕኖ ውስጥ ሳይወድቁ ነፃና ገለልተኛ ሆነው የፍህት ስርዓቱን የሚያሳልጡ ተቋማትም ናቸው። መገናኛ ብዙሃን ፍርድ ቤት በያዘው ጉዳይ ላይ ሚዛናዊ ያልሆኑ ዘገባዎችን ማሰራጨት እንደማይችሉ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ይደነግጋል።

የዳኝነት ነፃነት ( በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥ አንቀጽ 79)፦ ፍርድ ቤቶች በማንኛውም ደረጃ የዳኝነት ስልጣናቸውን ሲጠቀሙ ከማንኛውም የተፅዕኖ ፈጣሪ አካል (ሚዲያን ጨምሮ) ነፃ መሆናቸውን ያመላክታል።

ምንም እንኳን አዋጁ ይህንን ቢያስቀምጥም አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ አንቀሳቃሾች ይህንን ድንጋጌ ወደ ጎን በመተው ፍርድ ቤት በያዛቸው ጉዳዮች ላይ ሚዛናዊነት የጎደላቸውን ዘገባዎችን የመስራት እና የፍርድ ቤት የዳኝነት ስርዓት ላይ ተፅዕኖ የመፍጠር ስራዎችን ሲሰሩ ይስተዋላል።

ለአብነትም ከሰሞኑን ጦማሪ ስዩም ተሾመ ነፃ ውይይት በተሰኘው የዩቲዩብ ዝግጅቱ ላይ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተያዘውን የአቶ ብርሃነ መስቀል ክንፈ የማራማይንስ ማዕድን ምርመራ እና ማዕድን ማምረት ስራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ጉዳይን ሚዛናዊነት በጎደለው መልኩ በዘፈቀድ በሚዲያ ሲያራግብ ተስተውሏል።

ጉዳዩን የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በከባድ ሙስና ክሥ የእርሡን እና የግብር አበሩን እያየ የሚገኝ ሲሆን፤
የፌደራል የመጀመሪ ደረጃ ፍ/ቤት እና የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ግራ ቀኙን በፍታብሔር ችሎቶች እያከራከሩ ለመጨረሻ ውሣኔ ተቀጥሮ ሣለ ለምን አሁን ሚዲያ ላይ ማሥጮህ ተፈለገ?

ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ በያዘው ጉዳይ ላይ የሕግ የበላይነትን ባለከበረ መልኩ በአክቲቪስት ስዩም ተሾመ አማካኝነት ለአንድ ወገን ያደላ ሃሰተኛ መረጃ መሰራጨቱ በብዙዎች ዘንድ ቅሬታን ፈጥሯል።

ሚዲያ እውነተኛ መረጃን ከሁለት ወገን አጣርቶ ገለልተኛ በሆነ መልኩ መረጃን ለሕዝብ የማድረስ ኃላፊነት ያለው ቢሆንም ስዩም ተሾመ ያልተረጋገጡ መረጃዎችን የማሰራጨት እና ፍርድ ቤት የያዘውን ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሲሰጥበት ተስተውሏል።

ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ከጫፍ በደረሰው ጉዳይ ላይ
ስዩም ተሾመ ከአንድ ወገን ተላከልኝ ያለውን መረጃ ይዞ ወደ ሚዲያ መውጣት ለምን አሰፈለገ። ይህ ከሚዲያ ስነምግባር ያፈነገጠና ሚዛናዊነት የጎደለው ውንጀላ በፍርድ ቤት ላይ ተገቢነት የሌለው የሚዲያ ጫና በማሳደር የፍህት ስርዓቱን ለማደናቀፍ ያለመ ሴራ መሆኑን ሕዝብ ሊረዳ ይገባል።

ጉዳዩን በተመለከተ ፍርድ ቤት በራሱ አሰራር ተገቢውን ብይን የመስጠት ሙሉ ስልጣን ያለው ቢሆንም በሚዲያ ጋጋታ ይህን ዕውነታ ለመደበቅ እና የፍህ ስርዓቱ ላይ ጫና ለማሳደር በግልጽ ዘመቻ መከፈቱን መረዳት ይቻላል።

ስዩም ተሾመ የሰራው ሚዛናዊነት የጎደለው ዘገባ የፍርድ ቤትን ነፃነት የሚነካ፤ ለአንድ ወገን ያዳላ፤ በእውነተኛ መረጃ ላይ መሠረት ያላደረገ፤ በፍርድ ቤት አሰራር ላይ ጣልቃ ለመግባት ያለመና በሕግ የተያዘ ጉዳይን በሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ለማሸነፍ ያለመ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።

ሕዝብን በአሉባታ ልታደናግር ትችል ይሆናል እንጂ ውሸት ስለደጋገም እውነት አይሆንም፤ የለቅሦ ቦታ እየቀያየረሩ አብዝቶ ሰለተለቀሠ ሐቀኝነት አይረጋገጥም፤ ሌላኛው ወገን እውነትን ይዞ ሕግን አክብሮ ጉዳዩ በሀላፊነት ስሜት ስለመራ ሀቅ የለውም ማለት አይደለም፤ ከዚህ በኋላ ዱቡሻ ሚዲያ ኔትዎርክ እውነታውን በሚዛናዊነት ለሕዝባችን በተከታታይ የሚያቀርብ ይሆናል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Addis Ababa