Broker

Broker

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Broker, Advertising/Marketing, Ashewa meda, Addis Ababa.

Photos from Broker's post 12/04/2026

ትርጉሙም በግርድፉ ሲታይ፦ "ምድርም ፋሲካን (ደስታን) ታደርጋለች" ማለት ነው።

​በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎት፣ በተለይም በትንሳኤ በዓል ወቅት፦

​ፍጥረት ሁሉ በጌታ ትንሳኤ መደሰቱን፣

​የሞት ስልጣን መሻሩን፣

​ጨለማው አልፎ ብርሃን መውጣቱን ለማብሰር ይዘመራል።

​የትንሳኤው ብርሃን ለሁላችንም ሰላምንና ደስታን ያምጣልን! መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልዎ።

10/10/2025

«ዮሐንስ» ማለት "እግዚአብሔር ጸጋ ነው" ማለት ነው። ትርጓሜ ወንጌልም ቅዱስ ዮሐንስን "ተድላና ደስታ" ይለዋል። ቤተሰቦቹ በእርሱ ተደስተዋልና።

ቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ካህኑ ዘካርያስ ሲሆን እናቱ ደግሞ ቅድስት ኤልሳቤጥ ናት።

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ገና በማህፀን ሳለ የተመረጠ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ በማህፀን ሳለ ለአምላኩ የሰገደ ታላቅ ጻድቅ ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መጥምቁ ዮሐንስ ሲናገር "ከሴቶች ከተወለዱት መካከል እንደ እርሱ ያለ አልተነሳም" ብሏል።

ቅዱስ ዮሐንስ በርካታ መዓርጋት አሉት።

ከእነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ፦

መጥምቅ /መጥምቀ መለኮት ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቁ

ነቢይ ፦ ከእኔ በፊት የነበረና ከእኔ የሚበልጥ ይመጣል ብሎ በመናገሩ

ካህን፦ሕዝቡን በማጥመቁ

ወንጌላዊ ፦ ስለ ጌታችን መወለድ መምጣትና በመካከላቸው መቆም ሕዝቡን በመስበኩ

ከክፋት፣ ከሀጢአት እንዲርቁና ንስሐ እንዲገቡ በማድረጉ

የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃና በረከት ይደርብን 🙏

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address

Ashewa Meda
Addis Ababa