Manchester United - Gech

Manchester United - Gech

Share

ይህ በኢትዮጵያ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች የመረጃ መለዋወጫ ገጽ ነው Manchester United Fans' Page in Ethiopia. https://t.me/gechggmu

11/08/2025

ዶናሩማ ከፒኤስጂ እንደሚለቅ ተረጋግጧል...

ፓሪ ሰን ዠርማዎች ግብ ጠባቂውን ከአውሮፓ ሱፐር ካፕ ስብስባቸው ውጭ ማድረጋቸው ተዘግቧል

ማንቸስተር ዩናይትድ የግብ ጠባቂው ፈላጊ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፥ ተጫዋቹ ከፒኤስጂ ጋር እንደሚለያይ እርግጥ ሆኗል

ዶናሩማ ከዩናይትድ በተጨማሪ በቼልሲም የሚፈለግ ሲሆን መዳረሻው እንግሊዝ እንደሚሆን ፋብሪዚዮ ዘግቧል

13/07/2025

ሮናልዶ ሊውስ ኤንሪኬ የዩናይትድ አሰልጣኝ እንዲሆን ይፈልግ ነበር

ሲአር -7 በዩናይትድ ቤት በነበረበት ወቅት ኦሌጉናር ሶልሻየር ሲሰናበቱ ሊውስ ኤንሪኬ ክለቡን እንዲረከቡ ፍላጎት እንደነበረው ተነግሯል

ስፔናዊው አሰልጣኝ በተለይም በዚህ አመት ፒኤስጂን ታሪካዊውን የሻምፒየንስ ሊግ ክብር ጨምሮ አስደናቂ ጊዜን እንዲያሳልፍ አስችለዋል።

የፓሪሱ ክለብ በርካታ አሰልጣኞችን እያፈራረቀ እንዲሁም ከዋክብትን እያሰባሰበ ለዓመታት ማንሳት ያልቻለውን ዋንጫ በሊውስ ኤንሪኬ አማካኝነት ወደ ፓርክ ዴ ፕሪንስ አምጥቷል።

አሰልጣኙ ፒኤስጂን ከመረከባቸው በፊት ሮናልዶ የሶልሻየር ምትክ ሆነው ማንቸስተር ዩናይትድን እንዲረከቡ ቢመኝም፥ ዩናይትድ ራፍ ራግኒክን በጊዜያዊነት መሾሙ አይዘነጋም።

በወቅቱ ዚነዲን ዚዳንን የመሳሰሉ አሰልጣኞች ከክለቡ ጋር ስማቸው ቢነሳም ክርስቲያኖ ሮናልዶ ግን ኤንሪኬ ዩናይትድን እንዲረከብ ይፈልግ እንደነበር ነግሮኛል ሲል የስካይ ስፖርቱ ሮብ ዶርሴት ጽፏል።

Follow and Share Manchester United - Gech

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa