CFIC
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from CFIC, Media, current Place kera, Addis Ababa.
⚠️⚠️⚠️ልጄ ሆይ ተመለስ!⚠️⚠️⚠️
ልጄ ሆይ🤴 የዛሬ ምክሬ በቶሎ ተመለስ የሚል ነው።
👉ለምን መሰለህ እንዲህ የምልህ? ለረዥም አመት ❌ከተሳሳትክ❌ ለመመለስ አመቶች ያልቁብሃል! 🌕🌖🌗🌘🌑 ይመሽብሃል!
ዛሬ ግን ገና ወጣት ነህ 1 ብለህ ብትጀምር እንኳ ብዙ መቁጠር ትችላለህ። ደግሞ የምታውቃቸው ሰዎች የሉም? በወጣትነታቸው ተራ ነገር ላይ አተኩረው አሁን ሲነቁ ለመመለስ መሽቶባቸው በዚያው በጨለማ እየሄዱ ያሉ? አንተ ግን ለምን ይመሽብሃል? ለምንስ የተበላሸ የሰው ታሪክ ትደግማለህ? ለምንስ ጉልበትህን💪 ለከንቱ ነገር ትጨርሳለህ? አንተ እኮ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ልጅ👪፥ ጥሩ ወንድም👬፥ ጥሩ ጓደኛ👫፥ ጥሩ ባል💏 እና ጥሩ አባት👨👧👦 መሆን ትችላለህ!
🎯ይሄንንም ግን ለመሆን ዛሬ የምትወስነው ውሳኔ አለ!⚖
ምክንያቱም የትኛውም አቅም እና ጥንካሬ በጊዜው⏰ ብቻ ነው የሚሰራው! አለዚያማ ያልፍብሃል! ሁሌ ወጣት፥ ሁሌ ጎበዝ፥ አይኮንም!
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
📌ትልቁ አቅምህ ያለው ሰውነትክ🏋♀ እና እድሜክ ላይ ሳይሆን የዛሬው ምርጫህ እና ውሳኔክ🎯 ውስጥ ነው!
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
እነዚህ ቁልፎች ወይ ወደክብር ትገባባቸዋለህ አለዚያም ደግሞ እንደህፃን ልጅ እራስህ ላይ ትቆልፍባቸዋልህ፦
🔑ጓደኞችክ👋 እነማን ናቸው?
🔑ውሎክ የት ነው?
🔑ምንድን ነው የሚያስደስትህ?
አእምሮህን🧠 አሰራው እንጂ፤ ተራ እና የማይጠቅሙ ነገሮችን እያሰብክ አእምሮህን አታበላሽ፥ ደሞ ማወቅ ያለብህ የህክምና ማዕከል ሆስፒታል እንኳን ብትሄድ ሃኪም (Doctor)👨⚕👩⚕ ጭንቃላትህን (Brain) እንጂ አእምሮህን(Mind) አያክምልህም፤ ጤነኛ ያደርግሃል እንጂ ጤነኛ አስተሳሰብን አይሰጥህም፤ ምክንያቱም አንተ ነህ ምን ማሰብ እንዳለብህ የምትመርጠው! ደግሜ ልንገርህ ምን ማሰብ እንዳለብህ አስብ!
🕺አሪፍ ማለት ሳይመሽበት ❌ ከማይሆን መንገድ 🏃♂የሚመለስ ማለት ነው!🕺
👇ዛሬ የግድ 👋 "ቻው"👋 የምትላቸው አስተሳሰቦች🙇♂ እና ሰዎች መኖር አለባቸው!
አንተ ቻው ማለት ያለብህን ቻው የማለት አቅም ካጣህ ህልምህ እና ስኬትህ ያለጥርጥር ቻው ይሉሃል! 👋👋👋👋👋
👌ስለዚህ ዛሬ መንገድህን🛤🛣 ምረጥ እና አስተካከል🚧። መመለስ ካለብህ መንገድም🏃♂ ተመለስ! በመመለስህም ውስጥ አስተዋይነትህን ትገልጣለህ፤ አለዚያ ግን እድሜህ ቢጨምርም መቼም ትልቅ አትሆንም!
ልጄ ሆይ👨👦 ምክሬን ስለሰማህና ስለምታደርገውም አመሰግንሃለሁ!🙏 የህይወትህንም ስኬት🏹 አብሬህ አያለሁና አምላኬን አመሰግናለሁ!
ሁሌም እወድሃለሁ!
አባትህ
የክርስቶስ ሙላት አለም አቀፍ ቤ/ክ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
6318