Addis Ababa Times
እንኳን ደህና መጡ !
ለዜና ፣ወቅታዊ ጉዳዮች፣መዝናኛ ፍላጎት?
07/10/2025
" ' የመኪናና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ተሰርቆብኛል ' የሚል አካል ልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመምጣት ዕቃውን መለየትና መረከብ ይችላል " - ፖሊስ
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በአዲስ አበባ አስራ አንዱም ክ/ከተማ ተከታታይነት ያለው በወንጀለኞችና የተሠረቁ ዕቃዎችን በሚቀበሉ ግለሠቦች ላይ የጥናት፣ የክትትል፣ የምርመራና የኦፕሬሽን ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከነሐሴ 22 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክ/ከተማ ሦስት ወረዳዎች፤ በወረዳ 3፣ 7 እና 9 የተሠረቁ የመኪና ዕቃዎችንና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እየገዙ የሚሸጡ ግለሠቦችን እንደለየ አመልክቷል።
ልዩ ቦታው ፦
- ጌጃ ሰፈር፣
- ሱማሌ ተራ
- አብነት አካባቢዎች በተለያዩ መኖሪያ ቤቶችና ሱቆች ላይ የፍርድ ቤት የመበርበሪያና የመያዣ ትዕዛዝ በማውጣት በተደረገ ብርበራ የተለያዩ የመኪናና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከሌባ የሚገዙና የሚቀበሉ ግለሰቦችን ይዟል።
ፖሊስ አደረኩት ባለእ ኦፕሬሽን ፦
➡️ 209 የጎን መስታወት (ስፖኪዮ)፣
➡️ 84 ፍሬቻ፣
➡️ 6 የፊት መብራት፣
➡️ 56 ጌጅ፣
➡️ 32 የመኪና ጌጥ፣
➡️ 66 ቸርኬ፣
➡️ 11 የተሽከርካሪ ዓርማ፣
➡️ 7 የኤሌክትሪክ ቻርጀሮች፣
➡️ 34 የመኪና ሠሌዳዎች፣
➡️ 13 ላፕቶፕ ኮምፒውተር፣
➡️ 4 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር፣
➡️ 41 የሞባይል ቀፎዎች እንዲሁም የተለያዩ ሀሠተኛ ሠነዶችን ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሆነ አመልክቷል።
የመኪናና የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎች ተሰርቆብኛል የሚል አካል ልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመምጣት ዕቃውን መለየትና መረከብ እንደሚችልም ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበባ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa