BOLE MEDIA network

BOLE MEDIA network

Share

Digital media creater.Based on visa process.

16/05/2024

With Melat Nigussie – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

06/07/2023

#ሁለት ሚሊዮን ገደማ ሰራተኞችን ከኢትዮጵያ #ለመቅጠር በውጭ ሀገራት ጥያቄ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ

ከኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ሰራተኞችን ለመቅጠር የውጭ ሀገራት ለስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ባለፉት 11 ወራት፤ “ህጋዊ በሆነ” የውጭ ስምሪት 100 ሺህ ገደማ ሰዎች ስራ ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ይህንን ያስታወቁት ዛሬ በተካሄደ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ የተገኙት፤ ከተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት ነበር። የስራ አጥነትን ጉዳይ ያነሱት ዶ/ር አሰለፈች ኮቼ የተባሉ የፓርላማ አባል፤ ችግሩ “አሁንም በጣም አሳሳቢ” መሆኑን ተናግረዋል።

በየዓመቱ ከዩኒቨርስቲዎች የሚመረቁ ወጣቶች እና “ሌሎች” ስራ ፈላጊዎች ቁጥር “በርካታ መሆኑን” በመጥቀስም፤ መንግስት የስራ አጥነትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ምን ሊሰራ እንዳሰበ የፓርላማ አባሏ ጠይቀዋል። ከኢትዮጵያ ሄደው በውጭ ሀገራት የሚቀጠሩ ስራተኞች ለማግኘት በርካታ ፍላጎት መኖሩን በማብራሪያቸው የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ለስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በአሁኑ ወቅት “ሁለት ሚሊዮን ገደማ የሰራተኛ ጥያቄ” እንደቀረበለት አብራርተዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችን ለማቅረብ ከተለያዩ ሀገራት ጋር “እየተፈራረመ” መሆኑም ለፓርላማ አባላቱ አስታውቀዋል።
👇👇👇👇👇

https://t.me/bolemedianetETH

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa