Wondeye lightning Sarcasm

Wondeye lightning Sarcasm

Share

ዘና ፈታ እያሉ ቁምነገር የሚማሩበት ምርጥዬ ፔጅ ነው!!!It's the best page to learn while relaxing !!!È la pagina migliore per imparare rilassandosi !!!

22/11/2024

የዛሬዋን ቀን # ትረግማታለህ !
አዎ! ዛሬ ቁጭ ብለህ በፌስቡክ ላይ ፃፍ፣ ተሳደብ፣ ቀስቅስ፣ ሰዎችን አጋጭ፣ በሆነው ባልሆነው፤ በረባው ባልረባው ተባላ ...
ነገ ሀገር ሲተራመስ -- ኔትዎርኩ ሲዘጋ፤ መብራቱ ሲጠፋ፤ ውሀው ሲቋረጥ፤ የምትበላው ስታጣ፤ ገንዘብ በኪስህ ሞልቶ ለሻይ እንኳን ከቤትህ ለመውጣት ሲያቅትህ የት እንደምትገባ ግራ ይገባሀል።
ዛሬ ያቀለልካት ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር እንጂ...የቤትህ አናት ላይ ሲተኮስ፤ የቦንብ ናዳው ሲውርድ፤ ሰው ወጥቶ ሲቀር ስትሰማ፤ ህፃናት ሲረግፉ ስታይ፤ ህዝብ እየተሰደደ የበረሀ ሲሳይ ሲሆን፥ ባህር ውስጥ ሰጥሞ ሲቀር ስታይ...የዛሬዋን ቀን # ትረግማታለህ ።
ምነው ጌታ ባልፈጠርከኝ ትላለህ።
ብቻህን ያለወንድም፤ ያለእናት አባት፤ ያለዘመድ ስትቀር መፈጠርህን ትጠላለህ። ዛሬ ያቀለልካትን ሰላም ደም እምባ ብታለቅስ መልሰህ አታገኛትም።
ዛሬማ ሰላም ነው ፎክር...አቅራራ...ህዝብ ቀስቅስ...ተነሳ በለው፣ ግደለው በል!
የለኮስከው እሳት አመድ ሲያደርግህ የሰላምን ዋጋ ያን ጊዜ ትረዳዋለህ!
Share በማርግ ላልሰማው እናስም🙏

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address

Addis Ababa