Mohe
لا إله إلا الله محمد رسول الله 🤍
الحمد لله على كل حال 🤲
توكلت على الله 🌙
የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስትር ኻዋጃ ሙሐመድ አሲፍ እስራኤልን “የሰው ልጅ ክፉ ዕጣ ፈንታ እና እርግማን” ሲሉ በመግለጽ ጠንከር ያለ ትችት ሰነዘሩ። ኻዋጅ ሙሐመድ በመግለጫቸው "እስራኤል የሰው ልጅ ክፉ ዕጣ ፈንታ እና እርግማን ናት። በመጀመሪያ በጋዛ፣ በመቀጠል በኢራን፣ አሁን ደግሞ በሊባኖስ ንጹሐን ዜጎችን እየገደለች ትገኛለች። አውሮፓውያን አይሁዶችን ለመገላገል በፍልስጤም መሬት ላይ ይህችን ካንሰር የሆነች ሀገር የመሠረቱት በገሃነም እሳት እንዲቃጠሉ እጸልያለሁ" ብለዋል። ይህም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ወዲህ ከፓኪስታን በኩል ከተሰነዘሩት እጅግ በጣም ጠንካራ መግለጫዎች አንዱ ተደርጎ ተወስዷል።
ለዚህ መግለጫ ምላሽ የሰጡት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር "እስራኤል 'ለሰላም አደራዳሪ ነኝ' ከሚል መንግሥት የሚወጡ እንዲህ ያሉ ፀረ-ሴማዊ እና ደም አፋሳሽ ስም ማጥፋቶችን ጉዳዩን በጥብቅ ትመለከተዋለች። የአይሁድ መንግሥትን 'ካንሰር' ብሎ መጥራት ማለት በተግባር ሀገሪቱ እንድትጠፋ እንደመጥራት ይቆጠራል" ብለዋል።
Nejmudin Awel
እምገርም ነው!
(በእውቀቱ ስዩም)
በሰሞኑን ሶስቱ ሀያላን ክፉኛ ተከሳክሰዋል፤ አለ የተባለ ከበባድ መሳርያ ተኳኩሰዋል ፤ አገር አቁዋራጭ ሚሳይል ተለዋውጠዋል፤ ግን ከሶስቱ አገሮች የሞተው ሰው ፤ አንድ ሺህ እንኩዋ አይሞላም፤
በርግጥ ፋርሲ አውራዎቿን አጥታለች፤ ግን አንዱ ሲወድቅ ፥ ቤንች ላይ የተቀመጠው ወደ ሜዳው እየሮጠ ይገባና ጨዋታውን ያስቀጥለዋል፤
ባንጻሩ እኔና አናንተ የመናውቃት አገር ውስጥ ጦርነት ሲከሰት ፥ የሚከተለውን አስቡት ፤ በጥቂት ወራት ውስጥ ግማሽ ሚሊዮን እምሽክ ይላል፤ ከመአት የሚሰውር መደበቂያ የለ፤ ሼልተር የለ፤ ሚሳኤሉን ወደ ርችት የሚቀይር አይርን ዶም የለ፤ የተተኮሰው ሁሉ አይስትም፤ የሚባክን ህይወት እንጂ የሚባክን ጥይት የለም፤
ጦርነቱን አልጄዚራ ሳይዘግበው ፤ ቢቢሲ ሳይመዘግበው ለአለም ዜና ሳይበቃ ይካሄዳል፤ አልፎአልፎ አምባሳደሮች ብቅ ብለው We are deeply concerned የምትል የሻገተች ቃል ጣል አርገው ይሰወራሉ፤
ሀብታም አገሮች በኢምባሲያቸው በኩል “ ዜጎቻችን በዚህ ስፍራ ላይ እነ አጅሬ እየተፈሳፈሱ ስለሆነ ተባራሪና ፍንጣሪ እንዳያገኛችሁ ተጠንቅቃችሁ ፈታ በሉ “ እያሉ ያውጃሉ፤
አገር በቀል ዩቲበሮች ብቻ “ በዛሬው ውጊያ እንትን ሸለቆ ላይ፥ ተቆርጦ የቀረ ሰባት ሺህ ተዋጊ ተደመመሰሰ” እያሉ ደም ያቀለመው ፍራንካ ይለቅማሉ፤
ቤት ባፈራው ጦርነታችን ሳቢያ የሚቆም መርከብ የለ፤ የአለም ኢኮኖሚ አይበርደው አይሞቀው፤ የቡና ዋጋ ንሮ፥ አለምም በአራራ ተማርሮ ጦርነቱን ለማብረድ ሳይጥር ጦርነቱ በራሱ ጊዜ ይጠናቀቃል፤ የሚዋጋው ሲያልቅ ውጊያውም ያልቃል፤
ብቻ እምገርም ነው !
የተረፈ ካለ በአለምነህ ዋሴ “ አዋዜ “ ላይ ቀርቤ እተነትነዋለሁ፤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
MOH