Walabu Source
The daily news, facts and information
16/12/2023
Xiinxalaan siyaasaa Obbo johaar Mohammed waayee taayye dandayaafi mana keessaa baafamuu maatii isaatiin wal qabsiisee yaada toora media Hawaasaa isaarratti barreesseen Akkas jedhe "Siyaasa biyya keenyaa keessaa wanti fokkisaan tokko namoonni/ murnoonni gaafa waldhaban maatii walii kan miidhaniidha".
Itti dabaluunis Nuti warri qabsoo/siyaasa hojii godhannee filanne aarsaafi wareegama dhuunfaan dhufuu malu beekneeti itti seenne. Garuu ammoo haati, abbaan, adaadaan, haati warraa, obbolaanfi daa’imman keenya murtii kana keessatti hirmaannaa hin qaban. Badii uumamuufis wanti itti gaafatamaniif hin jiru. Taayyee Danda’aas tooraafi tooftaa siyaasaa filateen aarsaa itti dhufe kafalus, maatii isaa miidhuun garuu fafa. Yeroma mana itti kireeffatanis osoo hin kenniniif daa’imman isaa mana jireenyaa keessaa ari’uun cubbuudha.
Gochi akkanaa qaroowwan siyaasaa (political elites) jiddutti gadoo dhuunfaa hammeessuun, bor gaafa yeroon jijjiramte walitti fayyuu rakkisaa godha. Siyaasni haaloo ( revenge politics) ammoo biyya balleessa Jechuun Barreeffama isaa goolabeera.
https://t.me/walabu_source
https://vm.tiktok.com/ZM6MkfSpY/
https://youtube.com/?si=WMwrSWBruPoz550m
28/11/2023
ወይዘሮ ሮማነወርቅ ካሳሁን ከአባታቸው ከአቶ ካሣሁን እንግዳሸትና ከእናታቸው ከወይዘሮ አለሙሽ ዓለም በ1914 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተወለዱ፡፡ እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም ቅድሥት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ገብተው የቤተክርስቲያን ትምህርት ተማሩ፡፡ ከዚያም ስዊድን ሚሲዮን ትምህርት ቤት በመግባት በጊዜው ይሰጥ የነበረውን ዘመናዊ ትምህርት ተማሩ፡፡ በትምህርት ቤት ቆይታቸውም ጎበዝ ስለነበሩ አንደኛ ስለሚወጡ በአውሮፓውያን አስተማሪዎቻቸው ይሸለሙና ይመሰገኑ ነበር።
ወይዘሮ ሮማነወርቅ በተማሩበት ወቅት ሴቶች ላይ ከፍተኛ የባህል ተፅዕኖ ስለነበር ሮማነወርቅ ገና የ16 ዓመት ልጅ ሳሉ ለትዳር ታጩ፡፡ በለጋ እድሜያቸውም ወደ ትዳር ዓለም ተቀላቀሉና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ለመሆን በቁ፡፡ በስዊድን ሚሲዮን ትምህርት ቤት ይማሩ በነበረበት ወቅት ከአውሮፓውያን መምህራን ያገኙት ዘመናዊ ትምህርት እንዲሁም ከተፈጥሮ ችሎታቸው ጋር ተደምሮ በጥናትና ንባብ ያዳበሩትን እውቀታቸውን ወደ አደባባይ ማውጣት ስለፈለጉ በጥር ወር 1939 ዓ.ም በወቅቱ የማስታወቂያና ፕሮፖጋንዳ ሚኒስቴር ተብሎ ይጠራ በነበረው መስሪያ ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ በመሆን ተቀጠሩ፡፡ ወይዘሮ ሮማነወርቅ የሴት ልጅ ስራ "ከማዕድ ቤት ነው" የሚለውን የወቅቱን የኅብረተሰቡን አመለካከት በመጋፈጥ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ በተሰጣቸው በሬዲዮ ጋዜጠኝነት ስራቸው የተለያዩ ጽሑፎችንና ዜናዎችን በማዘጋጀት በማራኪ አንደበታቸው ሲያንቆረቁሩት በዜና አቀራረባቸውና በፕሮግራም ዝግጅታቸው በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትንና አድናቆትን ለማግኘት ብዙም ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር፡፡
በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ባገለገሉባቸው ጊዜያት በሬዲዮ ዜና አጠናቃሪነት፣ በዜና አንባቢነት፣ በሴቶች ፕሮግራም አዘጋጅነት ሰርተዋል፡፡ በዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ አንድም ቀን ሰለቸኝ ሳይሉ በየጊዜው ለአድማጭ አዲስ ነገር ይዞ በመቅረብ ለ25 ዓመታት ያህል ለሙያቸው በመታመን ያገለገሉት ጋዜጠኛ ሮማነወርቅ፣ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለወንዶችም በተለይ ለጋዜጠኞች አርዓያ መሆን ችለዋል፡፡ ይህም ከፍተኛ የሆነ ተወዳጅነትንና አድናቆትን አስገኝቶላቸዋል፡፡
ወይዘሮ ሮማነወርቅ ካሣሁን የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ ብቻ አልነበሩም፡፡ ሴቶች ከወንዶች እኩል ተሰልፈው መስራትና ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለኢትዮጵያውን ሴቶች ምሳሌና አርዓያ በመሆን ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደቡ ሰው ነበሩ፡፡ በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ጽሑፎችንም ያዘጋጁ ነበር፡፡ አብዛኞቹ ጽሑፎቻቸውም የሴቶችን ማኅበራዊ ኑሮ ማሻሻል ላይ ያተኮሩ ነበሩ፡፡
ወይዘሮ ሮማንወርቅ ካሣሁን የመጀመሪያ መጽሐፋቸውን (ትዳር በዘዴ) በ1942 ዓ.ም ለእትመት አብቅተዋል። ከአንድ ዓመት በኋላ በ1943 ዓ.ም ሁለተኛ መጽሐፋቸውን (ማህቶተ ጥበብ) ለሕትመት አበቁ፡፡ በ1948 ዓ.ም ሦስተኛ መጽሐፋቸውን ለሕትመት አበቁ፡፡ የመጽሐፉም ርዕስ "የሕይወት ጓደኛ" የሚል ነበር፡፡ ወይዘሮ ሮማነወርቅ የጤና እክል አጋጥሟቸው በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥር 23 ቀን 1964 ዓ.ም አረፉ፡፡ ስርዓተ ቀብራቸውም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡
28/11/2023
#ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት አንዲት ወጣት ተገደለች
የ32 ዓመቷ ወጣት በፖሊስ ጥይት ከጀርባዋ ተመታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን ፖሊስ የድርጊቱ ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ይገኛል ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ነዋሪ የሆነች የ32 አመት ወጣት ከፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ተመታ ህይወቷ አልፏል።
በፖሊስ አባል ጥቃት የደረሰባት ኢየሩሳሌም አስራት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ስትሆን ጥቃቱ ካጋጠማት በኋላ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና እና ሕክምና ክትትል ሲደረግላት የነበረ ቢሆንም ህይወቷ ሊተርፍ አልቻለም።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ቀበሌ 25 ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰአት አካባቢ በወጣቷ ጓደኞች እና በሌሎች ሰዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በቦታዉ የደረሰዉ የፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ እንዳለፈ ተገልጿል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደስ ፤ ወንጀሉን የፈፀመዉ የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ዉሎ " ለምን እና በምን ሁኔታ ዉስጥ ሊተኩስ ቻለ ? " የሚለዉ ጉዳይ እየተጣራ ነው ብለዋል።
ወደፊትም እንደ አስፈላጊነቱ የፍርድ ሂደቱ በመከታተል ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።
27/11/2023
Click here to claim your Sponsored Listing.