Afar forces

Afar forces

Share

🌎 አለም ከጉልበተኞችና ከአሸናፊዎች ጋር ናት..‼️

"ፈጣሪ ግን ምንግዜም ከተበዳዎች ጎን ነው 🇵🇸✅

09/05/2026

በነዳጅ የሚሰሩ እና ከ250 ሚልዮን ዶላር በላይ ግምት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ጅቡቲ ላይ ከጥቅም ውጪ እየሆኑ ነው ተባለ!!

በጠ/ሚሩ የተላለፈውን ክልከላ በመጣስ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና የፈቃድ ደብዳቤ ለማግኘት ለእያንዳንዱ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር የሚደርስ የጉቦ ክፍያ እየተጠየቀ መሆኑ ታወቀ።

(መሰረት ሚዲያ)

09/05/2026

አፋር ጊዜው አሁን ነው!

የአፋር ምድር የሰው ልጅ መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ የተፈጥሮ ድንቆችና ያልተገደቡ የኢኮኖሚ ዕድሎች መናኸሪያ ናት።

ዛሬ በአላሎባድ ፍልውሃ ላይ የታየው ዘመናዊ መሠረተ ልማት፣ ክልሉ የነበረውን "የተፈጥሮ ፀጋ" ወደ "ኢኮኖሚያዊ ስኬት" ለመቀየር የጀመረው ጉዞ ማሳያ ነው።

ይህ በአፋር ክልል በአላሎባድ ፍልውሃ ላይ የተጀመረው አዲስ የቱሪዝም ምዕራፍ፣ ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም አዲስ የኢኮኖሚ ሞተር የመሆን ትልቅ ተስፋ አለው።

G-24 News Media ለኢንቨስተሮች የሚሆን፣ የክልሉን ፀጋዎች የሚያስተዋውቅና ጥሪ የሚያስተላልፍ ልዩ ትንታኔ እና የኢንቨስትመንት ጥሪ እነሆ ብሏል፦

አላሎባድ ተፈጥሯዊ ትኩስ ፍልውሃዎቹ እና አስደናቂ ቀለማቱ ለዓይን ማራኪ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለጤናና ለፈውስ (Wellness Tourism) ትልቅ አቅም አላቸው።

ዘመናዊ መስተንግዶን ከተፈጥሮ ውበት ጋር አጣምሮ መያዙ፣ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለመሳብ የሚያስችል "ደረጃውን የጠበቀ መዳረሻ" ያደርገዋል።

# አፋር ለምን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ናት?
አፋር "ያልተነካው ምድር" (The Untouched Frontier) ተብላ የምትጠራው ያለምክንያት አይደለም፦

* ቱሪዝም፦ ከኤርታ አሌ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ እስከ ዳሎል አስደናቂ ቀለማት፣ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ እስከ አላሎባድ ፍልውሃዎች ድረስ ዓለምን ሊያስደንቁ የሚችሉ መዳረሻዎች ባለቤት ናት።

* ታዳሽ ኃይል፦ ክልሉ ለጂኦ-ተርማል (Geothermal) እና ለፀሐይ ኃይል ኢንቨስትመንት እጅግ ምቹ የሆነ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ አለው።

* ግብርና እና ማዕድን፦ ለሰፊ መስኖ ልማት የሚሆኑ ሰፋፊ መሬቶች እና የፖታሽ (Potash) ጨው ክምችት ለኢንዱስትሪ ባለቤቶች ትልቅ ዕድል ነው።

# "መቻል" የታየበት የአፋር ሕዝብ ፅናት!
የአፋር ሕዝብ በታሪክ ጠንካራ፣ እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳድ ነው።

አሁን ላይ የታየው የመሪዎችና የሕዝቡ ቅንጅት፣ ክልሉን ወደ ሰላምና ልማት ቀጠናነት እየቀየረው ይገኛል። ይህ "መቻል" ለኢንቨስተሮች አስተማማኝ ዋስትና ነው።

# ለኢንቨስተሮች የቀረበ ጥሪ፦
"አፋር ጊዜው አሁን ነው!"

ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስተሮች በሙሉ!
ያልተዋወቀው የአፋር ቱሪዝም፣ ያልታረሰው መሬት እና ያልተቀዳው የተፈጥሮ ሃብት የእናንተን ኢንቨስትመንት ይጠብቃል።
በአፋር ክልል ኢንቨስት ማድረግ ማለት፦

1.በአጭር ጊዜ ትርፋማ መሆን፦ ያልተነኩ ዘርፎች ላይ ቀዳሚ መሆን።

2.ታሪክ መስራት፦ የሰው ልጅ መገኛ የሆነችውን ምድር ወደ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም ማዕከልነት መቀየር።

3.የተመቻቸ ድጋፍ፦ የመንግሥትና የሕዝብ ትብብር ያለበት ምቹ ሁኔታ።

ኑ! በአፋር ምድር ላይ አሻራዎን ያኑሩ። አፋር ዛሬም ነገም ለስኬት ክፍት ናት።

# የ G-24 News Media መልዕክት!
እኛ በ G-24 News Media የአፋር ክልል እያሳየ ያለውን ይህን ፈጣን ለውጥ በታላቅ ኩራት እንዘግባለን።

ክልሉ ካለው ጂኦ-ፖለቲካዊ ጠቀሜታና ስትራቴጂካዊ ቦታ አንጻር፣ የአፋር መልማት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዋስትና ነው።

05/05/2026

ሰበር‼️
በህግ የተሰጠኝ የህዝብ አደራ በዘር የተደራጀው የህወሓት ቡድን የተከፈለ መስዋእትነት እከፍላለሁኝ እንጂ ማህተምና ቁልፍን አላስደፍርም። እኔ እንደ ጌታቸው ረደ መምህር ሳልሆን ወታደር ነኝ"።

ጀንራል ፕሬዚዳንት ታደሰ ወረደ

05/05/2026

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ!

ዛሬ በተካሄደው 6ኛው ዘመን 6ኛው መደበኛ የትግራይ ምክር ቤት ጉባኤ ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በአብዛኛው ድምፅ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተመርጠዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ወይዘሮ ኪሮስ ሐጎስ አፈ-ጉባኤ፣ ወይዘሮ ምህረት በርሄ ደግሞ ምክትል አፈ-ጉባኤ ሆነው ተሰይመዋል።

ምክር ቤቱ ስራውን በይፋ የጀመረው የፕሪቶሪያው ስምምነት በፌደራል መንግስቱ በኩል ተጥሷል በሚል ሲሆን፣ አዲሱ ፕሬዝዳንትም እስከ ቀጣዩ ስብሰባ ድረስ በአስፈፃሚው አካል ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያና ሹመት እንዲያደርጉ ሙሉ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።

ይህ እርምጃ በትግራይ ፖለቲካዊ መድረክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ወዴት ሊያመራው እንደሚችል የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።

02/05/2026

, ቃሉ በInstagram ገጹ 1m ተከታዮችን በማግኘቱ ደስታውን ለደጋፊዎቹ ጋር ለማክበር (Celebration) በዝግጅት ላይ ነበር።
​ነገር ግን ነገሮች ከሱ እቅድ በላይ ሆኑ! በአንድ ለሊት በለቀቃት አንዲት "Viral" የሆነች ቪድዮ ብቻ ተከታዩ ከ1m ተነስቶ 2.4m ላይ አልፏል።
​ይህንን ድንገተኛ ለውጥ የተመለከተው ቃሉ በገጹ ላይ
"ቀደማችሁኝ!"
ሲል በፈገግታ ስሜቱን አጋርቷል። እሱ ለ1m ሲዘጋጅ፣ አድናቂዎቹ ግን በድንቅ ጥበቡ ተማርከው ከ2 ሚሊዮን በላይ አደረሱት።

ይሄም የመጀመርያዉ ኢ/ያዊ በInstagram 2.5m በላይ ተከታይ ያለው ሁኖ ሪከርዱን ሰብሯል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa