Sbahe Tube

Sbahe Tube

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sbahe Tube, Digital creator, Addis Ababa.

02/01/2026

❝ ❞
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
◉.እንደ ሆሣዕናው ሕጻናት አመስጋኝ ሕጻን፣እንደ ሃያ አራቱ አመስጋኝ ሽማግሌዎች አመስጋኝ ሽማግሌ፡ እንደ አሥራ ሁለቱ መምህራን ሐዋርያት ሐዋርያ ወመምህር ፣እንደ መናኙ እንጦንስ መናኝ መነኮስ የሆኑ አባት እንኳንም ተወለዱልን!!!!

◉.ሀገር ለሚያተራምሰው፣የሥላሴ ሕንጻ እያፈረሰ ለሚውለው ለሚያድረው፣ ለአባት ለእናቱ ስጋት፣ለሀገር ለወገን ስጋት የሆኑትን ፈጣሪያቸውን ሳይፈሩ ማኅደረ እግዚአብሔር የተሰኘው ሰውነታቸውን ለሰይጣን አከራይተው የሚኖሩትን እንኳ እንኳን ተወለዳችሁ እንላቸው የለ!! የእግዚአብሔር ማደሪያ ለሆኑት፣በእርሳቸው የተነሳ የእግዚአብሔር ስሙ በአኅዛብ ዘንድ እንዲመሰገን ምክንያት የሆኑትን ቅዱስ፤ መብራት ሆነው ተወልደው ለጨለማው ዓለም መብራት ለሆኑ አባትማ እንዴት እንኳንም ተወለዱልን አንል።

◉.ከሕጻንነት እስከ እውቀት የጣመውን የላመውን እየተመገቡ ፈጣሪያቸውን በማመስገን ፈንታ ለሚያማርሩት እንኳ እንኳን ተወለዳችሁ እንላቸው የለ!!!
ከውልደት እስከ ሕልፈት አንደበታቸው ከምስጋና እግራቸውና እጃቸው ከአንሳሕስሆ ዘበከንቱ ገትተው ስለእኛ ስለ ኃጥአኑ ያለ እረፍት ለሚለምኑ አባትማ እንዴት እንኳን ተወለዱ አንልም!! ደግመው ደግመው ይወለዱልን እንጂ በኮልታፋ አንደበታቸው ያመሰገኑትን ምስጋና ደግመን እንሰማው ዘንድ።

‟አባ አቡነ አባ መምህርነ፡መምህርነ አባ ተክለሃይማኖት።
እምአእላፍ/፪/ኅሩይ እምአእላፍ ኅሩይ።

◉.የቅዱስ አባታችን ምልጃና በረከት አይለየን!!!

24/12/2025

እግዚአብሔር ትላንት በልጁ ተናገረን፣ዛሬም በሥነ ፍጥረቱ፣በመዓቱ መገለጫዎች በሆኑ ነገሮች ሁሉ ይናገራል፡ነገም በሁሉ ፊት ይናገራልና ታድያ ዛሬ ላይ እርሱን መስማት አይሻም ጆሮአችን ለሁሉ ከመስጠት።

06/12/2025

"አቀምዎ ውስተ ዓውድ ለዘይቀዉሙ ሎቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት በፍርኃት"

"መላእክትና የመላእክት አለቆች በፍርኃት በመንቀጥቀጥ በፊቱ የሚቆሙለት ጌታ ኃጥአት ሳይኖርበት፣የበደለው ነገር ሳይኖር እንደ ወንጀለኛ በፍርድ አደባባይ አቁመው የሞት ፍርድ ፈረዱበት።
◉.መምጣቱ ለዓላማ ሰውን ለማዳን ነውና በቁጣና በመዓት ሲጎትቱት፣ሲያንገላቱት እሱ ግን በይቅርታና በፍቅር ይከተላቸዋል ነበር።

መድኃኔዓለም በያላችሁበት ይጠብቃችሁ!!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address

Addis Ababa