Berekah Tube

Berekah Tube

Share

የነቃ ትውልድ!

01/04/2026

አሜሪካዊው ራፐር LIL REESE እስልምናን መቀበሉን አስታወቀ!!

13/12/2025

⛔️የከባድ መኪና ሹፌሮች "የቸርች ማሰርያ ኩፖን" በግዳጅ እንዲገዙ እየተደረገ መሆኑ ተዘገበ
~~~~~~~~
የከባድ መኪና ሹፌሮች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ በደሎች እየደረሱባቸው መሆኑን በከፍተኛ ምሬት እየተናገሩ ቆይተዋል፡፡ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል አቤት ቢሉም መንግስት ምንም እንኳን የምችለዉን ማሻሻያ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ቢልም እስካሁን ድረስ መፍትሄዎችን እንዳላገኙና ለመስራትም እጅግ እየተቸገሩ መሆኑን ፣ይህንንም ተከትሎ በራሳቸዉና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ይገልጻሉ፡፡

እነዚህ የከባድ መኪና ሹፌሮች ከሚያነሷቸው ችግሮች መሃል የደህንነት ስጋቶች፣ የስራ ክብደት እና የደሞዝ አለመመጣጠን፤ የመሰረተ ልማት አለመሟላትና ያንንም ተከትሎ የጉዞ መስተጓጎል፣ አስተዳደራዊ በደሎች የሚጠቀሱ ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በየአርቴፊሻል ኬላው በአንድ ጉዞ ዉስጥ ብቻ በተደጋጋሚ በሚጠየቁት ገደብ አልባ ገንዘብ እጅግ መማረራቸዉን ሲገልጹ ይሰማሉ፡፡ ይህ በእንዲሁ እያለ እነሆ አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንቶችን ቸርች ማሰርያ እየተባሉ በግዳጅ ኩፖን እንዲገዙ እየተደረጉ መሆኑን የ የተሰኘውና ሹፌሮች የሚደርስባቸዉን በደሎች የሚያጋልጠው ገጽ ከእነማስረጃው ለጥፎት እንዲህ ይነበባል!👇
_____________
"ትናንት ከሰበታ እና ቱሉቦሎ መሀል ያለወ ወረዳ ላይ ማለትም ኢሉ ወረዳ ወይንም ተጂ ከተማ ላይ የጴ'''''ንጤ ቸርች ማሰሪያ እያሉ ትራፊኮችና መንገድ ትራንስፖርቶች የ500 ብር ኩፖን ካልገዛቹ ብለው እያስቆሙ የግድ እየተቀበሉን ነው የሚል መልዕክት ደርሶናል ብለን ስላጋራን ብዙዎች ጉዳዩ መፈፀሙ ሳታውቁ ስትዘልፉን ነበር። ለማንኛውም ኩፖኑ ይሄው ያኔ ያላጋራነው ጉዳዩን አይተው እንዲታረሙ ነበር ለማንኛውም ማንም በግዳጅ የሚያደርገውን ነገር የማውገዝ የማሳወቅ የማሳየት ግዴታ ስላለብን እንዲህ ያለውንም አናልፍም። ማውገዝ ካለባችሁ እኛን ችግሩን ያሳየነውን ሳይሆን ችግሩን የፈጠረውን አካል ነው። በግዴታ መሆኑን ነው ልክ አይደለም ያልን መዋጮውን አይደለም። እንመዝን"

18/11/2025

"በትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ የማራቅ ዘመቻ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል"

📎 የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትምህርት ሚኒስትር በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት የማራቅ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዳሉት ሙስሊም ተማሪዎች በአለባበሳቸው ምክንያት በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው በደል የሀገራችንን ተከባብሮ የመኖር እሴት የመናድ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ሂጃብም ሆነ ኒቃብ የሙስሊም ሴቶች መግለጫ መሆኑን በማንሳት አንዱን ፈቅዶ አንዱን መከልከል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

ሀገር ወዳድ የሆነው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ያለውን በደል በትግስት ማሳለፉን አንስተው የሚመለከተው የመንግስት አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

17 አባላት ያሉት ኮሚቴ የሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል እንዲያጠራ መቋቋሙንም ገልፀዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa