Hanos Media and Promotion
we are informing and entertaining you
25/01/2026
❔ የምትደግፉት ክለብ ስንተኛ ደረጃ ነዉ ❔
Hanos Media and Promotion
Ethiopian Music
Black is Stronge
ፈጣን ስፖርት
24/01/2026
ደርብ ዘነበ
++++++++++++++++++
ደርብ ዘነበ በጎንደር የተወለደ ከሙዚቀኛ ቤተሰብ የተገኘ ድንቅ ችሎታ ያደለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው፡፡ደርብ አባቱ አኮርዲዎን ተጫዋች አጎቶቹም ሙዚቀኞች ናቸው። በልጅነቱ "ያዳመጠውን ሁሉ ከልብ ያስፈነደቀ፤ በመሰንቆ አገራረፉ ማንንም ያስደነቀ ፤ በግጥም አጣጣሉ ሴት ወንዱን ያሳቀ"ተብሎ ስለተሞገሰው አሰፋ አባተ ብዙ ሰምቷል። ሰምቶም ወዶታል፤ አድንቆታል። "በልጅነቴ ጀምሮ ስለአሰፋ አባተ ሰዎች ይነግሩኝ ነበር። ከሙዚቃውም ከሰውዬውም ፍቅር ነበረኝ" የሚለው ደርብ "አሰፋ አባተን እንዴት አድርጌ በሙዚቃ ላምጣው?" የሚል ሐሳብ እንደነበረው ይናገራል። ደርብ እንዳደነቀው አሰፋ አባተ ሁሉ መሰንቆ ይጫወታል። የወደደውን የማትበላ ወፍ የተሰኘ ሙዚቃ መልሶ ሲዘፍን ግን አላማው መዝፈን ብቻ አልነበረም። "ማሲንቆ በእኔ ትውልድ እንዲመለስ ፈልጌ ነበር። ማሲንቆን ማስተዋወቅ እፈልግ ነበር" ይላል ደርብ ለዲ ደቭሊው በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለ ምልልስ፡፡
"ባንቺው መጀን" በተባለው የወሎ ሙዚቃ ወሎን ከታች ከበረሃው እስከ ጦሳ ተራራና አምባሰል ተራራዎች ድረስ አስቃኝቶን በአንቺው መጀን እንል ዘንድ በሀሳብ ወሎ ወስዶ ያደርሰናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተጫወተው የአሰፋ አባተ "የማትበላ ወፍ" ተለይቶ የሚታወቀው ደርብ ዘነበ ከእነዚህ ስራዎች በኋላ ጠፍቶ ሰነባብቶ እንደገና በመመለስ
በሚኖርበት አውስትራሊያ Drums and Lions እና Dereb The Ambassador የተሰኙ ሁለት አልበሞች ሠርቷል።
በአልበሙ የተካተቱት "የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመናት" ተብለው በሚቆጠሩት 1960ዎቹ እና 70ዎቹ የተሠሩ ናቸው። አልበሙ ግን በኢትዮጵያ ገበያ አልተሸጠም። የጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ አለማየሁ እሸቴ እና ሙላቱ አስታጥቄ እና የደርብ የራሱ ባሕላዊ ሥራዎች ተካተውበታል። ደርብ ዘነበ እንደገና የሠራው የአሰፋ አባተ "የማትበላ ወፍ" የተባለ ሙዚቃ Drums And Lions በተሰኘ አልበሙ ውስጥ የተካተተ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.