Tesfa Microfinance Institution S.C.
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ትርፋማ ሆኖ የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ማሳካት::
10/11/2024
ለሁለት ቀን የቆየው የተስፋ የ7ቱም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆችና የደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎች ስልጠና እና የሩብ ዐመት ግምገማ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። ስለነበራችሁ መልካም ተሳትፎ ሁሉ እናመሰግናለን፤ ክብረት ይስጥልን። 🙏🏾🤩
መርሃግብሩን የተስፋ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብቴና የኦፕሬሽን ኃላፊ አቶ አረጋ በጥሩ ሁኔታ ከዋና የተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን ስለመራችሁት እናመሰግናለን።👏🙌
ወገባችሁን ለበለጠ ስራ የታጠቃችሁበት እንደነበር፣ በብዙ የምትሻሻሉበት እንደሆነ ያሰማችሁትን ንግግር በተግባር እንደሚገለጥ ሙሉ እምነት አለን፤ የሚቀጥለውን ወር ሪፖርት በጥሩ ሁኔታ ሰምተን በሩብ ዓመቱም ውጤታችሁን ተሻሽሎ መሸማቀቅ በሌለበት ልበ ሙሉነት በደስታ እንደምናከብረው እምነታችን ጽኑ ነው።
ከእናንተ ጋር አብረን ሠራተኞች ስለሆንን ደስ ይለናል።
በሰላም ግቡልን፣ ውዶቻችን 🤗🥰
ድኅረ-ገጽ፦ https://www.tesfamfisc.com
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.co/profile.php?id=100095256369462
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/?_t=8fbDC2y0qXu&_r=1
ዋትሳፕ፦ https://wa.me/251970202070
ተስፋ ጋ ተስፋ አለ!
02/11/2024
እንኳን ደስ አላችሁ ውድ የተስፋ ማይክሮ ፋይናንስ ባለአክሲዮኖችና ደንበኞቻችን!👏🏼🥳🤩
ተስፋ የመጀመሪያውን የአዲስ ባለአክሲዮኖች የሚቀበልበትና የተለያዩ አጀንዳዎችን የያዘ ጠቅላላ ጉባኤውን ቅዳሜ ሕዳር 7፣ 2017 ዓ.ም. ጠዋት 2፡00 ሰዓት ስብሰባውን ያካሂዳል፤ ስለሆነም፣ ውድ ባለአክሲዮኖች ለእዚህ ቀን እርስዎ ወይም ሕጋዊ ወኪሎ እንዲገኙ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ሙሉውን መረጃ ከተያያዘው ማስታወቂያ ላይ ወይም 👉🏼 https://tesfamfisc.com/ ተጭነው ይመልከቱ፡፡
📌ማሳሰቢያ
በዚህ አጋጣሚ የመጀመሪያው ዙር የተስፋ የአክሲዮን ሽያጭ ሕዳር 28፣ 2017 ዓ.ም. የሚያበቃ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡ በብሔራዊ ባንክ ተመዝግቦ በሙሉ ብቃት በ7ቱም ቅርንጫፎቹ እየሰራ ያለ ተቋም ባለቤት በመሆን ለእርስዎም ለሌሎችም መሰረት ያለው ስራ ላይ በመሳተፍ ትርፋማነትዎን ያረጋግጡ። በዚህ የተስፋ ባለቤቶች ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ለግለሰብ ከ5 አክሲዮን (5 ሺህ ብር) ጀምሮ እስከ 100 አክሲዮን (100ሺህ ብር) በመግዛት፣ ተቋማት እና አብያተክርስቲያናት ደግሞ ከ25 አክሲዮን (25 ሺህ ብር) ጀምሮ እስከ 1,000 አክሲዮን (1ሚሊዮን ብር) በመግዛት አንዱ ባለቤትና ውሳኔ ሰጪ መሆን እንደሚችሉ ስንገልጽሎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ
https://tesfamfisc.com/
ስልክ/ቴሌግራም/ዋትስአፕ፡ +2519 70 20 20 70
የቢሮ ስልክ ቁጥር፡ +251 115 52 62 05
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:00 |
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |
| Saturday | 08:30 - 12:00 |