Transforming Development Consultancy Company tdc
With Your Self Confidence, You Have Won Before You Have Started.
28/05/2026
የትምህርት ሥርዓት ትኩረት ይጠይቃል!!!
*********************************
የንግድ ሥርዓት ቢዛነፍ የኢኮኖሚ መዋዤቅ ሊያጋጥመን ይችል ይሆናል:: የጤና ሥርዓት ቢዛነፍ ጥቅት ሕሙማን ይጎዱ ይሆናል:: የግብርና ሥርዓት ብዛነፍ ምርታማነት ይቀንስ ይሆናል::
የትምህርት ሥርዓት ብልሽት ግን መተኪያ የማይገኝለትን የትዉልድ ብልሽት ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ከቤተሰብ እስከ አደባባይ ትኩርት የሚጠይቅ የጋራ ኃላፊነት ይሆናል::
ትምህርት የለዉጥ መሠረት ነዉ::
24/05/2026
ለመድፈኞቹ !!!
እንኳን ደስ ያላችሁ:: ደስም አለን !!!
****************************
"መድፈኞቹ" ዛሬ የተጎናፀፉት ወርቃማዉ ድል የረጅም ዓመታት ያልተቋጠ ትግል: አስገራሚ ፅናት: የማይወድቅ የሞራል ልዕልና እና የአስደናቂ ትዕግሥት ዉጤት ነዉ::
ባልተቋረጠ መራራ ትግል "ፈታኝ ሁኔታዎችን በአሸናፍነት አልፋችሁ" ለዚህ ታላቅ ድል በመብቃታችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ:: ደስም አለን:: ዓለም አብሮን እየተደሰተ ነዉ::
የመድፈኞቹ ወርቃማዉ ድል "ሃገራችን ኢትዮጵያ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሄደዉ ለ7ኛዉ ሃገራዊ ምርጫ እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት በመሆኑ እና "አብዛኛዉ የመድፈኞቹ አባላት የፓርቲያችን ብልፅግና አባላት በመሆናቸዉ ድሉን ድርብ ወርቅ ያደርገዋል::
"መድፈኞቹ" በአብዛኛዉ ወጣቶች በመሆናችሁ ለወርቃማዉ ድል የሰጠነዉን ልዩ ትኩረት: ትዕግሥት: ፅናት እና የሞራል ልዕልችንን በዋናዉ ጤላታችን በድህነት ላይ በማሳረፍ የቤተሰቦቻችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ "ዓለም ከእኛ ጋር የእኛን ድል እንዲያከብር በተሠማራንበት መስክ ሁሉ በትጋት እንደሚንሠራ ተስፋ አደርጋለሁ!!!
በድጋሚ እንኳን ደስስስ ያላችሁ:: አለን::
ለሕዝባችን ሁለንተናዊ ብልፅግና እንተጋለን !!!
ብልፅግናን ይምረጡ !!!
የምርጫ ምልክታችን የጠንካራ ሃገራዊ አንድነታችን ምልክት የሆነዉ የስንዴ ነዶ ነዉ!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa