Bitaniya Tube

Bitaniya Tube

Share

የሚጠብቀኝ አይተኛም

12/08/2025

ሱባኤ ለምን እንገባለን ?

ከቅዱሳን በረከት ለማግኘት
ቅዱሳን የተጋደሉትን ተጋድሎ በማዘከር ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ገዳማትና አድባራት የሚገባ ሱባዔ ከቅዱሳኑ በረከት ተካፋይ ያደርጋል፡፡ ቅዱሳን በሚጋደሉበት ቦታ ቅዱስ ነውና፤ ከአራቱ ዐበይት ነቢያት አንዱ ኢሳይያስ ከቅዱሳን የሚገኘውን በረከት ሲናገር «ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋ የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ» በማለት እግዚአብሔር ለቅዱሳን ቃል ኪዳን ስለ ገባላቸው ሱባዔ በመግባት በረከታቸውን መሳተፍ ይቻላል /ኢሳ.56፥6/፡፡ በጾመ ነቢያት የነቢያትን በረከት ለመሳተፍ፣ በጾመ ሐዋርያት የሐዋርያትን፣ በጾመ ፍልሰታ የእመቤታችንን በረከት ለመሳተፍ ሱባዔ መግባት የነበረና ወደ ፊትም የሚኖር የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ነው፡፡

ዛሬ ይህን ሥርዓት በመከተል ከቅዱሳንን በረከት ለመቀበልና የቅዱሳን አጽም ካረፈበት ገዳም በጾም፣ በጸሎት፣ በጉልበትም ገዳማትን በማገልገል የቅዱሳንን በረከት ለማግኘት ደጅ የሚጠኑ መናንያንና ምእመናን በየገዳማቱ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡

ነቢዩ ኤልሳዕ መምህሩን ኤልያስን በማገልገል የኤልያስ በረከት በእጥፍ በኤልሳዕ ላይ አድሮበታል፡፡ ‹‹ኤልያስ ኤልሳዕን ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው፤ ኤልሳዕም መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ›› /2ኛ ነገ. 2፥9/፡፡ ይህን አብነት በማድረግ በትሕርምት የሚኖሩ መናንያንን ያገለገሉበትን ገዳም በረከት በእጥፍ እየተቀበሉ ለሌሎችም የሚያቀብሉ አባቶች በየገዳማቱ በርካቶች ናቸው፡፡ ይህን ትውፊት ለማጥፋትና ምእመናን ለመናንያን ክብር እንዳይሰጡ በስመ ገዳማዊ የምእመናንን ገንዘብ የሚዘርፉና የእውነተኛ መነኮሳትንና መናንያንን የተቀደሰ ሕይወት የሚያጐድፉ መኖራቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

ምሥጢር እንዲገለጥልን!

በዘመነ ብሉይ እግዚአብሔር ነገሥታትን ራእይ በማሳየት ምሥጢሩን ይሰውርባቸው ነበር፡፡ የግብጹን ፈርዖን ሕልም ዮሴፍ ፈቶለታል /ዘፍ.41፥14-36/፡፡

የባቢሎኑን ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የልጁ ብልጣሶርን ራእይ ደግሞ ነብዩ ዳንኤል ተርጉሞላቸዋል /ዳን.4፥9፤ ዳን.5፥4/፡፡እነዚህ ነገሥታት በዘመናቸው የሚሆነውንና ወደፊት ሊፈጸም የሚችለውን ራእይ ቢያዩም ራእዩን በትክክል ተረድተው «ትርጓሜው እንዲህ ነው!» የማለት ብቃት አልነበራቸውም፡፡
ስለዚህ በዘመናቸው ይኖር የነበሩትን ነቢያት ሱባዔ ገብተው የሕልማቸውን ትርጉም እንዲነግሩአቸው ይማጸኑ ነበር፡፡ ነቢያትም ሱባዔ በመግባት ነገሥታቱ ያዩትን ሕልም ሲተረጉሙ ‹‹ማኔ ቴቄል ፋሬስ ይላል፡፡ የነገሩም ፍቺ ይህ ነው፤ ማኔ ማለት እግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረው ፈጸመው ማለት ነው፡፡

ቴቄል ማለት በሚዛን ተመዝነህ ቀልለህም ተገኘህ ማለት ነው፡፡ ፋሬስ ማለት መንግሥትህ ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ ማለት ነው›› እያሉ በግልጽ የመንግሥታቸውን አወዳዳቅ ይነግሯቸው ነበር /ዳን.5፥28/፡፡

ቅዱሳን አባቶቻችን በየራሳቸው ያዩት ራእይ ምሥጢርና ትርጉም እንዲገለጥላቸው ሱባዔ ይገባሉ፡፡ እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፡፡ ነቢዩ ዕዝራ የመጻሕፍትን ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ቢገባ የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ዳግም መልሶ ለመጻፍ ችሏል /1ኛ ዕዝራ.13፥43-49/፡፡

በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሐዋርያት ከነሐሴ 1-14 የገቡት ሱባዔ ነው፡፡ ይህ ሱባዔ ተሰውሮባቸው የነበረውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ትንሣኤ ተረድተው በረከቷን ለመሳተፍ አብቅቷቸዋል፡፡

እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም. ነው፡፡ ሐዋርያት ሊቀብሯት ወደ ጌቴ ሰማኔ ይዘዋት ሲሔዱ አይሁድ በታተኗቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት የእመቤታችንን ሥጋዋን ወስደው በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አኑረውታል፡፡ በዚህ ጊዜ እነርሱ ተደናግጠው ስለተበታተኑ የእመቤታችን የዕረፍቷ ነገር ያስጨንቃቸው ነበር፡፡

Photos from Bitaniya Tube's post 12/08/2025

🎉 Just completed level 3 and am so excited to continue growing as a creator on Facebook!

12/08/2025
13/08/2024

እምነቴ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa