70 Derja
Welcome to 70derja❤
If you want to promote, talk to us inbox.
26/04/2026
▣ በ90ቹ መጨረሻ LOVE & PEACE የሚሉ በቴዲ አፍሮ ፎቶዎች የደመቁ ደብተሮች በብዛት ለገበያ ቀርበው ነበር። ብዙ ጊዜ የቴዲን ፎቶ ለማየት ወይም ለማሳየት ሲባል በዘመኑ ደብተሮቹ በሌላ ነገር አይታሸጉም ነበር። በእነዚህ ደብተሮች የተማረ አለሁ ይበል?
▣ ፍቅር እና ሰላም! Love & Peace! ንጉሣችን ከብላቴናነቱ የጀመረው ይሄን ስብከት በጉልምስና ዘመኑም አስቀጥሎታል። መልዕክቱ ሁሉ ፍቅር ነው፣ ጩኸቱም ለሀገር እና ሕዝብ ሰላም ነው።
▣ ፍቅር ሲል እውነተኛ ፍቅርን ነው። አሸናፊ የሆነ ፍቅር - ፍቅር ያሸንፋል እንዲል። ሰላም ሲልም የአፍ ሰላም ሳይሆን በይቅርታ የሚፀና ነብስን የሚያሳርፍ ምልዑ ሰላም ነው።
▣ ፍቅርና ሰላም ለሁላችን ይሁን!
Teddy Afro
Amleset Muchie
❤
24/04/2026
የቴዲ አፍሮ ስቱዲዮ መዘረፉ
የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ስቱዲዮ መዘረፉን የአርቲስቱ የቅርብ ሰው ለዶቼ ቬለ አረጋገጡ። ትናንት ማምሻውን የወጡ መረጃዎች መሣሪያ የታጠቁ እና በተሽከርካሪ የመጡ አካላት ጠባቂዎችን በመደብደብ አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ ሲኤምሲ በሚባለው አካባቢ ከሚገኘው የአርቲስቱ ስቱዲዮ ንብረቶች መዘረፋቸውን ገልጸዋል።
ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው እኝህ የመረጃ ምንጭ፦ በበኩላቸው ትናንት ምሽት ወደ ሦስት ሰዓት ገደማ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል። አክለውም ጠባቂዎችን በመደብደብ ስቱዲዮው ተሰብሮ አርቲስቱ ለሙዚቃ ሥራው የሚጠቀምባቸው ንብረቶች መዘረፋቸውንም አመልክተዋል።
አርቲስት ቴዎድሮስ በርካታ የሙዚቃ ሥራዎች እንዳሉት የገለጹልን የመረጃ ምንጩ፦ አብዛኞቹ እስካሁን አልወጡም ነው ያሉት። ቴዲ አፍሮ በየዕለቱ በሙዚቃ ሥራና ልምምድ፤ እንዲሁም የሙዚቃ ቅንብር ጊዜውን የማሳለፍ ልምድ አለው ያሉት የቅርብ መረጃ ምንጩ፤ በርካታ ግጥሞችና የሙዚቃ ሥራዎቹን ለሌሎች አርቲስቶች እንደሚሰጥም ገልጸውልናል።
ምንም እንኳን አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን «ኢቶሪካ» የተሰኘው የሙዚቃ አልበሙ ከመውጣቱ በፊት ጀምሮ የሥነልቡና ጫና ሊያደርሱ የሚችሉ ወከባዎች በአካባቢው እየተፈጸሙ ቢሆንም እንቅስቃሴው ተገትቶም ቢሆን እስካሁን በደኅና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል። በመንግስት በኩል ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የተባለ ነገር የለም።
ዶይቸ ቬለ
DW
❤
24/04/2026
በኢቶሪካ አልበም የተሳተፉ ባለሙያዎች‼️
🔷 ቴዲ አፍሮ የ18ቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ ደራሲ ከመሆኑ በተጨማሪ 'የአዞ እምባ አይደለም' በሚለው ዘፈን ላይ በአቀናባሪነት አግዟል
🔷 'ፅዮን ሙሽራዬ' በተሰኘው ሙዚቃ 23 ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፤ ይህም በአልበሙ ውስጥ ከሚገኙ ሙዚቃዎች መካከል ብዙ ሰው ያሳተፈ ሙዚቃ አድርጎታል
🔷 በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያላቸው ባለሙያዎች በዚህ አልበም አሻራቸውን አሳርፈዋል፤ አንጋፋው የሊድ ጊታር ተጫዋች ሰላም ስዩም 'ዝ ፀዳል' እና 'ተወዳጅ' በተሰኙ ስራዎች ላይ ተጫውቷል፤ እውቁ የሳክስፎን ተጫዋች ያሬድ ተፈራ ደግሞ በስምንት ሙዚቃዎች ላይ ድንቅ ጥበቡን አሳይቷል፤ አበጋዝ ክብረወርቅ በሁለት ሙዚቃዎች ላይ በድምፅ ቅጂና በማስተሪንግ አስተዋፅኦ አድርጓል፤ ክብረት ዘኪዎስ በድምፅ ቀረፃ ተሳትፏል
🔷 'ፅዮን ሙሽራዬ' በአቦጊዳ ባንድ የተቀናበረ ሲሆን ቀሪዎቹ 17 ስራዎች በ6 ባለሙያዎች ቅንብር፣ ሚክሲንግ፣ ኪቦርድና ማስተሪንግ ተሰርቶላቸዋል
🔷 ወጣቱ በረከት ተስፋዝጊ ስምንት ሙዚቃዎችን ሰርቷል፤ ታየኝ፣ መሬማ፣ ስምምነ፣ ዝ ፀዳል፣ በመስኮቱ፣ ብልጭታ፣ ሳምነው፣ የማዕረግ ጥግ የእሱ ውጤቶች ናቸው፤ በተጨማሪ ሊድ ጊታርም ተጫውቷል
🔷 የዳስ ጣል፣ ቲንታጎና ኢቶሪካ አቀናባሪ እንዲሁም የመሬማ፣ ታየኝ፣ ስምምነ፣ በመስኮቱ፣ ተወዳጅና የማዕረግ ጥግ ማስተሪንግ ቀማሚ ደግሞ ማሩ አለማየሁ ነው
🔷 አቤል ጳውሎስ የአዞ እምባ አይደለምና ተወዳጅ፥ ሀይፐር ዜማ መርከብና ስማ እራሴ፥ በፍቃዱ ግርማ ጀምበር እንዲሁም ሮቤል ዳኜ ሺ ቢባል ዜማዎችን አቀናብረውና ሚክስ አድርገው ለአልበሙ ስኬታማነት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል
🔷 ታመነ መኮንን ክራር፥ ቻላቸው አረጋና ወንድሜነህ ክፍሌ ማሲንቆ እንዲሁም ጣሰው ወንድምና ኤርሚያስ ናደው ዋሽንት በመጫወት የሀገራችንን ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪዎች ከዘመናዊው ጋር አቀናጅተው ለአልበሙ ተጨማሪ ጣዕም አበርክተዋል
🔷 ስድስት የውጭ ሀገር ዜጎችም ተሳትፈዋል፤ ጀምስ ክሮምዌል እና ኮይሲ ክሮምዌል ትራምፔት፥ ስቲቭ ብራድሊና ፎስተር ሞቲ ትራምቦን፥ ግሬግ ጃንግ ሳክስፎን፥ ዴስትኒ ፒቮንካ አልቶ ሳክስፎን ተጫውተዋል
🔷 ድምፃዊ አስገኘው አሽኮ(አስጌ ዴንዳሾ) በቲንታጎ ዘፈን በግጥምና በፊውቸሪንግ ተሳትፏል፤ ተዋናይ መኮንን ላዕከ ደግሞ በስማ እራሴ በድምፅ ግብአት ያልተጠበቀ ክስተት ሆኖ ተደምጧል፤ የወሎ እናቶች ምርቃት(ፀሎት)፣ የፀሀዬ ደመቀችና የኢትዮጵያ ትቅደም ዜማዎች እንዲሁም የአፄ ሀይለስላሴ ንግግር በጀምበር ሙዚቃ በድምፅ ግብአት ገብተዋል
🔷 ድምፃዊያኑ ሚኪያስ ቸርነት፣ ልዑል ሲሳይ፣ አዲስ ጉርሜሳ፣ ምኞት ሀይሉ(ዲጄ ዊሽ)፣ አለማየሁ ደሊልና በሀይሉ ዳንኤል አጃቢ ተቀባዮች ሆነው አልበሙን አድምቀዋል
በአጠቃላይ 50 የሚጠጉ ባለሙያዎች በኢቶሪካ አልበም ተሳትፈው ለስኬታማነቱ የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል፤ ለሁሉም ምስጋና ይገባቸዋል!
(ታምሩ ዓለሙ)
❤
24/04/2026
ቃሉ ፑቱክስ (Kalu Putiks) ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን በስፋት እያገኘ ነው! 🚀🌟
በፈጠራው እና በይዘቱ ሁላችንም የምናደንቀው ተወዳጁ ቲክቶከር ቃሉ ፑቱክ በይፋዊ የኢንስታግራም (Instagram) ገጽ ላይ እንዲተዋወቅ ትልቅ ግብዣ ቀርቦለታል። የግዙፋ ኢንስታግራም ድርጅች ኦፊሻል ገፅ፤ ከ700 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት አለም አቀፋዊ ገጽ ሲሆን፣ ቃሉን "በልዩ ሁኔታ ልናስተዋውቅህ እንፈልጋለን" በማለት በይፋ ጋብዞታል።
ይህ ግብዣ ትላንት በኢንስታግራም አካውንቱ በለቀቀው ቪዲዮ ላይ በተጻፈለት አስተያየት (ኮሜንት) የተደረገ ሲሆን፣ "Hi! We'd love to feature you on our account next week..." በሚል መልእክት የተረጋገጠ ነው። ይህ ለቃሉ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ፈጣሪ ወጣቶች ትልቅ ሞራል እና ማሳያ ነው።
በእውነት የሚያስደስት ዜና ነው። እንኳን ደስ አለህ ቃሉ! 🎉
በውጤትህ ሁላችንንም አኩርተኸናል። ኢትዮጵያ ትኮራብሃለች!
24/04/2026
ሙዚቃን ማሰር አይቻልም!
የተከበራችሁ የጥበብ ወዳጆች እና የነፃነት አፍቃሪዎች፤
ይሄንን መልዕክት የምናስተላልፈው በአንድ ድምፃዊ ላይ ስለደረሰ ጥቃት ብቻ ለመናገር አይደለም። ይልቁንም፣ የሀገር ኩራት በሆነው፣ በሰላማዊው የኪነ-ጥበብ እና በነፃነት የመግለጽ መብታችን ላይ ስለታወጀው ዘመቻ ለመቃወም ነው።ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አዲስ አልበም ሰርቶ ለህዝብ ባቀረበበት በዚህ ወቅት፣ በሌሊትና በድብቅ ወደ ስቱዲዮ በመግባት የሙዚቃ መሳሪያዎቹን መውሰድና የቅርብ ሰዎቹን ማዋከብ፣ የፍርሃት እንጂ የጥንካሬ ምልክት አይደለም። ስቱዲዮ መዝጋት ይቻላል፣ መሳሪያዎችን መውሰድ ይቻላል፣ ሰዎችንም ማሰር ይቻላል፤ ነገር ግን በህዝብ ልብ ውስጥ የታተመውን ዜማ እና የነፃነትን መንፈስ በፍጹም ማሰር አይቻልም! ጥበብ የህዝብ መተንፈሻ ናት። ሙዚቃ ደግሞ የሀገር ቁስል የሚታከምበት፣ ፍቅርና አንድነት የሚሰበክበት መድረክ ነው።ይህንን መድረክ ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል። ስለሆነም፦በድምፃዊው ስቱዲዮ እና በስራ ባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመው ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም፤ የተወሰዱት የሙዚቃ መሳሪያዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ፤የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ስጋት የመፍጠር ነፃነታቸው እንዲከበርላቸው አለመግባባቶችም ደግሞ ካሉ በንግግር እና በንግግር ብቻ እንዲፈቱ የሚመለከተው አካል በዚህ ጉዳይ ላይ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ በጥብቅ እንጠይቃለን። " ስቱዲዮ ተገብቶ የሙዚቃ መሳሪያው ቢወሰድም፣ የቴዲ አፍሮ ዜማ ግን በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ እያስተጋባ ይኖራል። እውነት እና ጥበብ ሁልጊዜም ከሰንሰለት በላይ ናቸው!
ሙዚቃን ማሰር አይቻልም!
ጥበብ ለዘላለም ትኑር!
እዮብ
Teddy Afro
Amleset Muchie
18/04/2026
በሁለት ቀን 50 ሚሊየን እይታ👌
❤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |