Post Now

Post Now

Share

Describe Your Style and Services.

13/06/2025

አትሙት ያላት ነብስ

በትላንትናው ዕለት በህንድ የአውሮፕላን አደጋ ብቸኛው የተረፈው ሰው ኩማር ራሜሽ ሲሆን፣ ያጋጠመውን እንዲህ ሲል ገልጿል፦

"ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ነበር። በሕይወት ያለሁም አልመሰለኝም። ብድግ ስል ብዙ አስክሬኖች እዚያና እዚያ ተበታትነው አይቼ በጣም ደነገጥኩኝ። ወዲያውኑ መሮጥ ጀመርኩ።

'ወንድሜ የት ነህ? ወንድሜ የት ነው?' እያልኩኝ በከፍተኛ ድምፅ እጮህ ነበር። ወንድሜ ከእኔ ትንሽ ራቅ ብሎ ከነበረው ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምን እንደሆነ ባላውቅም፣ በዛን ወቅት አንድ ኃይል ሰውነቴን እንደወረረኝ ይሰማኛል። በሕይወት እንድተርፍ የረዳኝ ነገር እንዳለም ይሰማኛል።ሲል ተናግሯል::

ቀና ካልደረሰህ እንዲህ ነው::

Photos from Post Now's post 13/04/2025

ፎቶ ፦ የ2017 ዓ.ም በዓለ ሆሣዕና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከብሯል።

ቅድስት ቤተክርስቲያን ፥ " የሆሣዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፣ ሆሣዕና በአርያም በማለት ጌታችንን በክብር መቀበላቸው የሚታወስበት በዓል ነው " ብላለች።

Want your business to be the top-listed Food & Beverage Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Addis Ababa
GOFA