Eyerusalem Negash

Eyerusalem Negash

Share

“ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥2

25/06/2026

ህይወት ከንቱ ናት! ይላሉ። ይህን ሃሳብ የሚያቀነቅኑ ሰዎች አብዛኞቹ ከንቱነቷን ተረድተው ሊኖሩ በተፈቀደላቸው ጊዜ በቁም ነገር ከመኖር ይልቅ ራሳቸውን ለሚፈልጋቸውና ለሚፈልጉት ነገር ያለ ስስት ሰጥተው ከንቱ የሆነችባቸውን ህይወት ከድጥ ወደ ማጥ ይነዷታል።

ህይወት ከንቱ ናት! ያለ ሰው ጊዜያዊነቷን ተረድቶ በቁም ነገር ይኖራታል። ተስፋውን ዘላለማዊ አድርጎ በሰላም ይኖራታል። የአንዴ ክስተት ናትና ትርጉሟን በኑሮው ያጣጥማል።

ይህ ሁሉ ግን ያለ አዳኟ የሚከወን አይደለም። ሲዖል በሆነች ዓለም ሰላም፣ ደስታ፣ ስክነት፣ የመኖር ምክንያት፣ የህይወት ተስፋ ያለ ኢየሱስ አይታሰብም።

እናማ ምን ለማለት ነው? እኔ ኢየሩሳሌም ነጋሽ ኢየሱስ ጌታዬ ነው፣ ከሁሉ አስቀድሜ እከተለዋለሁ ስል በምክንያት ነው!

ሰላም ምሽት

23/06/2026
Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa