Dr. Solomon werku

Dr. Solomon werku

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Solomon werku, Doctor, Addis abeba, Addis Ababa.

23/02/2020

/INSOMNIA



ይህ ማለት ለመተኛት መቸገር፡በቂ ለሆነ ጊዜ በእንቅልፍ አለመቆየት ወይም ተኝተን ስንነሳ ምንም አይነት እረፍት የማይሰጥ ከሆነ የዚህ እክል ምልክት ነው ማለት እንችላለን።በአጠቃላይ የዚህ ችግር ተጠቂ የኖኑ ግለሰቦች ጥቂት ሰአታት የሚተኙ ወይም የተመቻቸ ቦታ ኖሮ መተኛት ሚቸገሩ ናቸው።ይህም እንቅልፍ ማጣት በቀን ተቀን እለታዊ ክንዉናችን ላይ ተጽኖ ይፈጥራል።ይህ ችግር በተወሰነ የሰአት ገደብ ከፍለን ከዚ በታች የሚተኙ ይህ እክል አለባቸው ለማለት እንቸገራለን ምክንያቱም የተለያዩ ግለሰቦች የተለያየ የእንቅልፍ ጊዜ ስለሚኖራቸው ነው።አብኛዉን ጊዜ ይህ ችግር ብቻዉን የሚመጣ ሳይሆን ከተለያዩ የጤና ችግር እና እለት ተእለት ከሚገጥሙን ስንክሳር ጋር የሚያያዝ ነው #ለምሳሌ ህመም፡ጭንቀት እና የተላያዩ የጤና ሁከቶች ጋር ይዛመዳል እነዚህ ተዛማጅ ባሉበት ወቅት ይህን እክል ለማስወገድ እና ለማከም ቀለል ይላል ምክንያቱም እነዙህ ምክንያቶች ከታወቁ እነሱን ማከም ያንን እክል ለማስወገድ ይረዳል።በአጋጣሚ ግን ምንም አይነት ተጓዳኝ ችግር ሳይኖር የእንቅልፍ ማጣት ችግር እራሱ ዋነኛ ችግር ሆኖ ሊመጣ ይችላል በዚህ ወቅት እራሱን እንቅልፍ ማጣትን ማከም ይኖርብናል ማለት ነው።በህክምና የተለያዩ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ መንገዶች ሲኖሩ ለዛሬ ከነዚህ መካከል በቀላሉ ቤት ወስጥ መተግበር የምንችላቸዉን መንገድ እናያለን እሱም ፦ጤናማ የእንቅልፍ መርህ ፡ የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ ፡ እራስን መቆጣጠር ነው
በህክምናው ወደ ተወሳሰቡ የህክምና መንገድ ከመሄዳችን በፊት ይህን ህክምና ማድረግ ይመከራል

1 ጤናማ የእንቅልፍ መርሆች መከተል
👇👇👇
#እረፈት እስኪሰማን ብቻ መተኛት ከዛም ከአልጋል ላይ መነሳት
#ቋሚ የሆነ የእንቅልፍ ጊዜ ማበጀት ለምሳሌ ሁሌ 3 ሰአት ወደ መኝታ ማምራት
#እንቅልፍ ሳይመጣ ወደ አልጋ በማምራት ለመተኛት መሞከርን ማወገድ
#ከምሳ በኋላ የሚወሰዱ አነቃቂ መጠጦችን ማስወገድ ለምሳሌ ቡና
#የመተኛ ጊዜያችን ሲደርስ ምንም አይነት አልኮል አለመዉሰድ
#አለማጨስ በተለያ ማታ ላይ
#ለመተኛት በምንሰናዳበት ወቅት የተለያዩ ሀሳቦች ሚያስጨንቁን እና ሚረብሹን ከሆነ የምናስበዉን ነገር በወረቀት ላይ መጻፍ እና ሲነጋ ለዛ ነገር መፍትሄ መፈለግ
#መተኛት ሲያቅተን የተለያዩ መጻፍት ወይም አልጋ ላይ ሆኖ ቲቪ መመልከትን ማስወገድ
#አልጋ ላይ ሆኖ ምግብ መመገብን ማስወገድ
#አልጋ ላይ ሆኖ ስልክ ማናገርን ማስወገድ
#በቀን ላይ ለአጭር ጊዜ የሚወሰዱትን ናፕ ማስቀረት
#እንቅልፍ አልወስደን በሚል ወቅት በተደጋጋሚ ሰአታችንን በማየት መጨነቃችን ማስወገድ ይኖርብናል
#እየራበን ወደ መኝታ አለማምራት
#የመተኛ ክፍላችንን በተቻለ መጠን አመቺ እና ለእንቅልፍ እንዲጋብዝ አድርጎ ማዘጋጀት ለምሳሌ መብራት ፡ጫጫታን ማወገድ
#ቋሚ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ማድረገ

2 የሰዉነታችን ጡንቻዎች የማዝናናት/ሪፍሬሽ ማድረግ
👇👇👇
ይህን ለመከወን በመጀመርያ የፊታችን ላይ ያሉትን ጡንቻ ለቀቅ ለማድረግ እና ለማዝናናት ለ5-6 ሰኮንድ ለሚያህል ጊዜ ጥርስትን ነክሶ/ጡንቻን በመወጠር/ መቆየት በመቀጠልም ለ20-30 ሰኮንድ ለቀቅ ማድረግ።ይህን መጀመርያ ከፊታችን ጡንቻዎች ጀምረን እስከ እግራችን ድረስ ይህንን መንገድ መከወን። ይህን በተደጋጋሚ መሞከር ይህም መንገድ ዉስጣዊ ስሜታችን ረጋ ሲለሚያደርገው ቶሎ እንቅልፍ እንዲወስደን ይረደናል።
3 እራስን መቆጣጠር፦ይህ ሀሳብ እንደ አንድ የህክም

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
DOCTOR