Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Disaster Safety Inclusion &Competence Assurance Directorat, Public Figure, Addis Ababa.
12/10/2025
በአፋር ክልል በደረሰ የመሬት ወንቀጥቀጥ አደጋ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተገለጸ ።
በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ ትናንት ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ።
የሰሜናዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ አስሓብ የመሬት መንቀጥቀጡ በዞኑ ባራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች መከሰቱን ተናግረዋል።
በአደጋው የ12 ዓመት የሆነ ታዳጊ ህይወት ሲያልፍ 6 ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የስረዱት ኃላፊው 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙንና ያለመጠለያ መቅረታቸውን ጠቁመዋል።
በሁለቱ ወረዳዎች መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ለተጎጂዎች ከክልሉ መንግስት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚደረግ አመላክተዋል።
የባራሕሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን በበኩላቸው÷ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንተ ኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳወቁ.....
በነሀሴ ወር ከባድ ዝናብ ይኖራል ተባለ.......
በነሀሴ ወር በረዶ የቀላቀለና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።
ኢኒስቲትዩቱ እ.ኤ.አ ከኦገስት 1 እስከ 31/2025 የሚኖረውን የአየር ጠባይ ሁኔታ አስታውቋል።
በነሃሴ ወር ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጋር ተያይዞ በተለይም በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ የሃገሪቱ ቦታዎች ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በፀሐይ ሀይል ታግዘዉ ከሚፈጠሩ የደመና ክምችቶች በመነሳትም በረዶ የቀላቀለ እና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተመላክቷል።
በሌላ በኩል በአንዳንድ ቦታዎች ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ የእርጥበት መብዛት ጋር ተያይዞ በረባዳማ አካባቢዎች የውሃ በሰብል ላይ መተኛት፣ የመሬት አቀማመጡ ከፍታ ባላቸውና ተዳፋታማ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የመሬት መንሸራተትና በጎርፍ መጠቃት ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል።
እርጥበት በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሰብል በሽታ እና የአረም መስፋፋት ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሮችና የሚመለከታቸው አካላት ሰብሎች በጎርፍ እንዳይጠቁ እና በማሳ ላይ ውሃ እንዳይተኛ የጎርፍ መቀልበሻዎችንና ከማሳ ውሰጥ ውሃን ማስወገጃ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ደግሞ አልፎ አልፎ በሚኖረው ተደጋጋሚ ከባድ ዝናብ ቅጽበታዊ ጎርፍ የማስከተል እድል ይኖረዋል ተብሏል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው።
በክረምቱ አልፎ አልፎ የሚኖር ከባድ ዝናብ ሊያስከትል ከሚችለው ቅጽበታዊ ጎርፍ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል-የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
****
(ሐምሌ 15/2017ዓ.ም) በመጪዎቹ አስር ቀናት አልፎ አልፎ የሚኖረው ከባድ ዝናብ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለፀ።
ኢንስቲትዩቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በመጪዎቹ አስር ቀናት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በደቡብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት እንደሚኖራቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልጿል።
የሚጠበቀው እርጥበት ለወቅቱ የግብርና ስራ እንቅሥቃሴ በአመዛኙ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ትንበያው ያሳያል።
ስጋቶችን ለመቀነስና የሚኖሩትን መልካም አጋጣሚዎች በላቀ ሁኔታ ለመጠቀም የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች በተገቢው ሁኔታ መተግበር እንደሚያስፈልግ አመላክቷል።
በሚኖረው እርጥበት ዘር መዝራት፣ ትርፍ ውሃን ከማሳ በማጠንፈፍ ማስወገድ፣ የአፈር መሸርሸር ስጋትን ለመቀነስ የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ጠቁሟል።
ረባዳማ በሆኑ ማሳዎች የውሃ ማንጣፈፍ ስራዎች መስራትና የደረሱ የበልግ ሰብሎችን በሚኖሩ ደረቅ ቀናቶች መሰብሰብ እንዲሁም የሚገኘውን እርጥበት በመጠቀም የመኸር ዘር መዝራት እንደሚገባም አብራርቷል።
በቀጣዮቹ አስር ቀናት በሚኖረው ዝናብ በአብዛኛው ተፋሰሶች ላይ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖርም መግለጫው ያመላክታል።
አልፎ አልፎ ከሚኖረው ተደጋጋሚ የሆነ ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ በተለይም ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ተፋሰሶች ላይ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊያስከትል እንደሚችል አስረድቷል።
ስለሆነም በወንዝ ዳርቻ እንዲሁም ረግረጋማ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውና የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት አደጋን በመቀነስ መልካም እድሎችን እንዲጠቀሙም አስገንዝቧል።
የጎርፍ መቀልበሻ ቦዮችን ማዘጋጀት፣ወራጅ ውሃን በእግርም ሆነ በቀላል ተሽከርካሪ ለማቋረጥ አለመሞከር፣ የጎርፍ የፍሳሽ መውረጃ ቦዮችን ማፅዳት፣ የዝናብ ውሃ ማሰባሰብና ማጠራቀም እንደሚገባ ማመላከቱን ኢዜአ ዘግቧል።
23/06/2025
ሰኔ 15/2017ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ማዕከልና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተወጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በአደጋ ስጋት ቅነሳ ላይ ያተኮረ ውይይትና ሥልጠና ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ ሲካሄድ የነበረው ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
በውይይቱ ከቀረቡት ሰነዶች መካከል የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ምንነትና አስፈላጊነት፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ ዕሳቤዎች፣ ማስፈንጠሪያዎችና መለኪያዎች፣ የቤተሰብ ኃላፊነትና የማህበረሰብ አጋርነት፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ሮድ ማፕ፣ የአደጋ ስጋት ፕሮፋይል ጥናትና ውጤቶች እና የአደጋ ስጋት ዕቅድ ማካተት ዙሪያ ሰፋፊ ርዕሰ ጉዳዮች በጥልቀት በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች ከዩኒቨርሲቲ በተጋበዙ ምሁራን አማካኝነት ተሰጥተዋል፡፡
ከቀረቡት ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል፤ የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለማሳካት ተግዳሮቶቹ ምን እንደሆኑ እና ምን መፍትሔ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፖሊሲን በአዲስ አበባ በሚሰሩ ቢሮዎች የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራን በልማት ዕቅዶቻቸው እንዲያካትቱ ምን እየተደረገ እንደሆነ፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል መሰራት ያለበት ወሳኝ ነገሮች እና እንዴት የተሻለ የቤተሰብ ሀላፊነትንና የማህበረሰብ አጋርነትን ማሳደግ እንደሚቻል በሚሉ የመወያያ ነጥቦች የቡድን ውይይት ተደርጎ የቡድኑ አቅራቢዎች ከልምዳቸው በመነሳት ተግዳሮት ይሆናሉ ያሏቸውን ነጥቦችን እስከ መፍትሄዎቻቸው ያቀረቡት ሲሆን ለወደፊት የአደጋ ስጋት ቅነሳ ተግባርና ለአደጋ የማይበገር ማህበረሰብና ሀገር ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ ትልቅ ግብኣት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
በመረሀግብሩ ማጠቃለያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሀመድ ፖሊሲውን ከማስፈፀምና ከመፈፀም አንፃር፣ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ምላሽ በመሥጠትና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራን በስልጠናው ባገኘነው ጥልቅ ዕውቀትና የልምድ ተሞክሮ በመነሳት በቁርጠኝነት፣ በቅንጅት እና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ውጤታማ ስራ ልንሰራ ይገባል የሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ አመራሮችንና ስልጠናውን የሰጡትን አካላት አመስግነው ኮሚሽኑ ቀጣይነት ያለው ቅንጅታዊ ስራ ከመሥራት አኳያ ከአዲስ አበባ እሳትና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሥራት እንደሀገር የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራን ማሳካት እንደሚቻል ያላቸውን ቁርጠኝነት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ሜኒስትሪሚንግ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ነጋ ጋረደው በመድረኩ እንደተናገሩት ከሌሎች ክልሎች ጋር በቅንጅት እንደምንሰራው ሁሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋርም በአቅም ግንባታ፣ ልምድ ልውውጥ፣ ውጤታማ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራ በቅንጅት ለመሥራት ትብብራችንና ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ሥራንና ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ምላሽ መስጠት እንዲቻል በዕውቀትና በክህሎት የዳበረ አመራርና ባለሙያ ለማፍራት የሚረዳ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና የመድረክ ውይይቶች እንዲደረጉ በማመቻቸቱ ምስጋናቸውን ገልፀው ባገኙት እውቀት፣ ልምድምና ተሞክሮ ወደ ውጤታማ ተግባር እንደሚቀይሩም ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ስለምትከታተሉን ምስጋናችን ከልብ ነው።
Click here to claim your Sponsored Listing.