Abu Ruffa
☆━━━━━━━━ ʏᵃⁿⁱ ʙᵘᵘˡᵃ
ᴋᵃˢᵃˡ sᵃᵈᵘʰ
ᴀⁿ
ᴛᵃⁿⁱᵐ
ᴀᵇˡᵉ ʷᵃᵃ
ɴᵘᵐᵘᵏ ᴅᵉᵉˡᵘʰ ᴀⁿ ━━━━━━━☆ Afar state Afarlands daahuli
27/01/2024
👉 Ethiopian Federal police
ልዩ ልዩ ሐሰተኛ ሰነዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡-ልዩ ልዩ ሐሰተኛ ሰነዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ባለስልጣናት ስም እየተጠቀሙ ''እነ እከሌን እናውቃለን፤ ጉዳያችሁን እንጨርስላችኋለን'' እያሉ እያጭበረብሩና እያታለሉ ከህብረተሰቡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚቀበሉ በመሆናቸው ፖሊስ ከነ-ኤግዚብቱ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጿል።
ከዚህም ባለፈ ተጠርጣሪዎቹ ባለሃብት ሳይሆኑ ባለሃብትና ከፍተኛ ገንዘብ እንዳላቸው ለማስመሰል በርካታ የአሜሪካን ዶላር በሳምሶናይት ይዘው ፎቶግራፍ በመነሳት እራሳቸውን እያሳዩ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት አባል ሳይሆኑ አባልና ኮሎኔል ነን እያሉ እንዲሁም የብሔሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መሥሪያ ቤት የስራ ባልደረባ ሳይሆኑ ባልደረባና ደኅንነት ነን እያሉ በሐሰተኛ መታወቂያ ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩና ሲያታልሉ እንደ ቆዩ ፖሊስ አሰታውቋል።
ፖሊስ ምርመራውን በማስፋት ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ አውጥቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አካባቢ በሚገኘው የተጠርጣሪ ሞቱማ ደለሳ ቦሮቃ መኖሪያ ቤት ውስጥ ባደረገው ብርበራ ለወንጀል ተግባር ማስፈፀሚያ የሚገለገልበት 90 ሺህ ብር፣ አንድ ሽጉጥ TISASTOTLYE/ ከ24 መሠል ጥይቶች እና ከ2 ካዝና ጋር እንዲሁም አይፎንና ሳምሰንግ ሞባይል፣ አንድ አፒድ ላፕቶፕ እና ሦስት ፍላሾች መያዙን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል።
እራሱን ኮሎኔል እና ደኅንነት እንደሆነ በማስመሰል የሚያታልለው ፋህሚ አብዲ ዩሱፍ እንደሆነም ታውቋል።
ህብረተሰቡ በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ በማጠናከር በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችንና ቡድኖችን በማጋለጥ አሳልፎ ለፖሊስ እንዲሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።
በመጨረሻም በነዚህ ሰዎች ተታለልኩ ወይም ተጭበረበርኩ የሚል ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ አስታውቋል።
16/01/2024
Kudrak tan gaba taamah Baxsale innal magcag gurusen kokkobi wagiitay👁
የሚገርም እጅ ስራ የተሰራው ልዩ እና ድንቅ ዲዛይን የተሰራ ተሽከርካሪ ተመልከቱት👁
08/01/2024
😥ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ
**************
የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የሆነውና ሟቹ ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ስለሆነም መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማንኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።
በወንጀል የተጠረጠረ ግለሠብን መደበቅም ሆነ እንዲያመልጥ መተባበር የሕግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ በሼህ አብዱ ሞት የተሠማውን ሀዘን ገለጾ፤ ለቤተሰቦቻቸው እና ለእምነቱ ተከታዮች መፅናናትን ተመኝቷል።
07/01/2024
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Telephone
Website
Address
Addis Ababa