Awulala Multimedia

Awulala Multimedia

Share

ነፃ ሀሳብ ፤ ሚዛናዊ መረጃ። Awulala Multimedia is Ethiopia's premier real estate multimedia platform.

21/11/2019

የኢህአዴግ ምክር ቤት የፖርቲውን ውህደት አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመራለትን የፖርቲውን ውህደት አፀደቀ።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት በዛሬው እለት ማካሄድ በጀመረው ስብሰባ ነው ውህደቱን ያፀደቀው።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በውህድ ፓርቲ ፕሮግራም (ማኒፌስቶ) ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክር በማካሄድ ረቂቁ ለኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲቀርብ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ ስራ አስፈፃሚው በተዋሃደው ፓርቲ ሕገ ደንብ ላይ ተወያይቶ እንዲጸድቅ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲመራ መወሰኑ ይታወሳል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ በዛሬው እለት የምክር ቤቱን ስብሰባ አስመልክተው ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ምክር ቤቱ ባካሄደው ስብሰባው በፖርቲው ውህደት ዙሪያ ተወያይቱ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቀዋል።

በዚህም ምክር ቤቱ በኢህአዴግ ውህደትን በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ነው አቶ ፍቃዱ የተናገሩት።
(ዘገባ የፋና)

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address

Algeria Street
Addis Ababa