Excellency Today Media
To day Excellency information
04/03/2021
17/02/2021
ከህዝብ እይታ ተሰውረው የነበሩት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ባለቤት ከአመት በኋላ መታየታቸውን የአገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል።
በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ በባለቤታቸው አባትና የቀድሞ መሪ የልደት መታሰቢያን በማስመልከት በተዘጋጀ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ታይተዋል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ትልልቅ ዝግጅቶች ላይ መሪው ባለቤታቸውን አጅበው የሚገኙት ቀዳማዊት እመቤት ሪ ሶ ል ጁ ለየት ባለ ሁኔታ ለአንድ አመት ያህል ከህዝብ እይታ ጠፍተው ነበር።
ለዚህም መጥፋታቸው አንዳንድ መላምቶች የተሰጡ ሲሆን ከጤና እክል ጋር በተያያዘ እንዲሁም ነፍሰ ጡር ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ ነበር።
የሰሜን ኮሪያ ብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት በበኩሉ በትናነትናው ዕለት ለምክር ቤቱ እንዳሳወቀው ሪ ሶ ልጁ ከህዝብ እይታ የጠፉት ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ጋር በተያያዘና እንዲሁም ከልጆቻቸው ጋር አብረው ለማሳለፍ በመምረጣቸው ነው ብሏል።
እስካሁን ባለው መረጃ ሰሜን ኮሪያ አንድም በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው አላገኘሁም ትላለች። አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ይህንን ሃሳብ አይቀበሉትም።
ሮዶንግ ሲንመን ዘገባ መሰረት በትናንትናው እለት ባለትዳሮቹ ማንሱዴ አርት ቲያትር ሲገቡ በርካቶች በጭብጨባ እንደተቀበሏቸው ነው።
ከቦታው የወጡ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ሲጫወቱና ሲስቁ ሲሆን፤ ጭምብል አላጠለቁም እንዲሁም አካላዊ ርቀታቸውን አልጠበቁም ተብሏል።
ሪ ሶል ጁ ማን ናቸው?
ቀዳማዊት እመቤት ሪ ሶል ጁ አባቷ በሙያቸው ፕሮፌሰር ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የህክምና ዶክተር ናቸው።
አስተዳደጋቸው ከላይኛው መደብ የሚመደቡና፤ ሃብታም ናቸው።
የ31 አመቷ ሪ ሶል ጁ ከዚህ ቀደም ኡንሃሱ በሚባል ኦርኬስትራ ውስጥ ዘፋኝ ነበሩ።
ከመሪው ኪም ጋር የተጋቡት በአውሮፓውያኑ 2009 ሲሆን ይህም የቀድሞው መሪና የኪም አባት በጠና ታመው እያለ በአጣዳፊ ያቀዱት ነው ተብሏል።
ምንም እንኳን ከተጋቡ አመታትን ቢያስቆጥሩም የኪም ባለቤት መሆናቸው የታወቀው የአገሪቱ ሚዲያዎች ይፋዊ በሆነ መንገድ ባለቤት ብለው መጥራት ከጀመሩ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ነው።
የደቡብ ኮሪያ ደህንነት በበኩሉ ባለትዳሮቹ ሶስት ልጆች እንዳላቸው ይፋ አድርጓል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa