Shegger Insider

Shegger Insider

Share

Human Rights Fighter

14/06/2023

የወል እውነት እንዴት ማምጣት ይቻላል

የወል እውነትን እውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ ዋነኛ እርምጃዎች አንዱ እና ዋነኛው #እውነት እኛ ጋ ብቻ አለመሆኗን መረዳት መቻል ነው።

እውነት በሌላኛውም አቅጣጫ ያለች መሆኑን መረዳት ለጋራ ወይም ለወል እውነት በር ይከፍታል ትልቁን እውነታም እንድንረዳ ይረዳናል።

እውን ለማድረግ ከሁሉም ወገን ያሉ ትናንሽ እውነታዎችን በመረዳት ትልቁን እውነት በመረዳት የጋራ የሆነ እውነታን በመያዝ እና በማጠናከር እሱንም በማጎልበት #በጋራ ችግሮችን መፍታት ይቻላል።

ይሔን ሊያስፈፅሙ ከሚችሉ መንገዶች አንዱ ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ነው። ሁሉም ማህበረሰብ በጋራ ለጋራ ሀገር ያለውን እውነታ እና አስተዋፆ በማድረግ እና የሌላውን በመስማት ትልቁን እውነት በማጉላት ሀገርን ማፅናት ይቻላላ።

13/06/2023

በወል እውነት ሀገር መገንባት ወይስ በውሸት ሀገርን መናድ......

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ እያገጠጠ የመጣው #ፅንፈኝነት የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ወይም #የወል እውነትን እያደበዘዘ በተቃራኒው ደግሞ #ግለኝነትንን እና የሚል አስተሳሰብን እያገነነ መጥቷል።

ሁሉም በየቀየው ተገድቦ የራሱን እውነት ብቻ እያጮኸ የሌላውን እውነታ እየተጋፋ እና ወንድማማችነትን እየገፋ ይገኛል። እንደ ሀገር አንድ ጊዜ ቆም ብለን የምናስብበት ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል። ከተደጋገፍን እና ይዘን መጓዝ ከቻልን መመስረት እንችላለን ነገር ግን እየገፋን #በመንደር ማሰብ ከጀመርን ተያይዘን እንጠፋለን! ለቀጣዩ ትውልድ የሚናስረክበው ሀገርም አይኖረንም።

በመሆኑም አንድ ጊዜ ቆም ብለን እናስብ!

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Dhugaa Saba keenyaaf Ni falmanna!

Sabni keenya dhugaa akka galaanaa kan jaarraa hedduu qaba. Sirnootaa fi namoota dhuunfaan awwaalamee hafuun hin maluuf.

Category

Website

Address

Sheggar
Addis Ababa