Sinework Taye

Sinework Taye

Share

Public Figure

06/09/2025

ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ነች!

አንዳንድ ጊዜ ሕይወት እንደ አይሮፕላን በረራ ያደርጋታል፡፡ የአይሮፕላን በረራ አደገኛው፣ ለመከስከስ ተጋላጭ የሆነውና እጅግ ትልቅ ጥንቃቄ የሚስፈልገው ጊዜ ሁለት ነው፡፡

1) የመነሻው (የመጀመሪያ) ጊዜ፣

2) የማረፊያው (የመጨረሻው) ጊዜ፡፡

ማንኛውንም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ስትጀምሩ በጥንቃቄ አስባችሁበት ጀምሩ፡፡ በችኮላ፣ በመላ-ምትና በግድ የለሽነት የተጀመረ ነገር ለመከስከስ አደጋ የተጋለጠ ነው፡፡ ትክክለኛ ነገር እየጀመርን እንኳን በጥንቃቄ ካላደረግነው ከአደጋው አናመልጥም፡፡

ማንኛውም ግንኙነት፣ ንግድ፣ ስራ፣ ራእይ . . . ወደማብቂያው እንደደረሰ ሲገባንና “ማሳረፍ” ስንፈልግም ታላቅ ጥንቃቄ ይጠይቃል፡፡ በስሜታዊነትና በችኮላ ነገሮችን ከማቋረጥ መጠንቀቅንና ስናቋርጠው ደግሞ በጥበብ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ አሳርፉት እንጂ አትከስክሱት!

የተባረከ ምሽት ተመኘን🙏

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa