Yetages kera
11/06/2026
በቀናት ውስጥ ወደ ጦርነት…!
ህወሓት በቀናት ውስጥ በፌደራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መወሰኑን፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ አልጀዚራ ላይ በጋራ ባስነበቡት ጽሑፍ አስጠንቅቀዋል፡፡
ሬድዋን እና ጌታቸው በጋራ ባስነበቡት ጽሑፍ፣ “ጽምዶ” በሚል ቅንጅት የፈጠሩ ኃይሎች ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ጎትተው ለማስገባት እየተንቀሳሱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በአስመራ፣ በመቀሌ እና በሱዳን በድብቅና ግልጽ በሆኑ ስብሰባዎች የተፈጠረው የጽምዶ ጥምረት፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ጌታቸው እና ሬድዋን አክራሪና ርዝራዝ ቡድን ነው ያሉት ህወሓት፣ በአስመራ ድጋፍና አጋዥነት፣ በሚቀጥሉት ቀናት ጥቃት ለመሰንሰር መወሰኑን አረጋግጠዋል፡፡ ህወሓት ትቃት የሚፈጽመው በፌደራል መንግስቱ ላይ መሆኑን የገለጹት ሁለቱ ባለሥልጣናት፣ በጦርነት ዝግጅቱ የኤርትራ መንግሥት በግልጽ እየተሳተፈ ነው ብለዋል፡፡
እነ ጌታቸው “ርዝራዝ” በሚል ያኮሰሱት ህወሓት፣ የፕሪቶሪያውን ስምምነት በግልጽ መጣሱን እና በፌዴራል መንግሥቱ ላይ ጥቃት ለመሰንዝር ራሱን መዘጋጀቱን ጠቁመዋል። ባለሥልጠናቱ ዳግም ኢትዮጵያ ወደ ጦርነት ተስባ መግባት የለባትም በሚል ባስነበቡት ጽሑፍ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡
በህወሓት እና በአስመራ ደጋፊዎቹ ላይ ተጽዕኖ ወይም አቅም ያለው ማንኛውም አካል፣ ወደ ሌላ ግጭት ውስጥ እንዳይገባ ከፍተኛ ግፊት ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ለኢትዮጵያ ዳግም ወደ ግጭት መመለስ አደገኛ ከመሆኑም በላይ አስከፊ ቀጠናዊ መዘዞችን ያስከትላል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ህወሓትና የጦርነት አጀንዳውን በግልጽ ውድቅ ቢያደርግም፣ ቡድኑ የግጭት መቀስቀስ አባዜውን አልተወም ብለዋል፡፡ ህወሓት ከኤርትራ መንግስት በቀጥታ በሚያገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተዋጊ ኃይል መመልመል፣ ማሰልጠን እና ማስታጠቅ ቀጥሏልም ሲሉም አክለዋል።
#ኢትዮጵያ #ትግራይ
#አንድአፍታ
11/06/2026
ኦባሳንጆ መቀሌ ገብተዋል
የፕሪቶሪያ ስምምነት አደራዳሪ ከነበሩት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ የአውስትራሊያና የኢንግሊዝ ተወካዮች ያካተቱ የልኡካን ቡድን ከትግራይ ክልላዊ መንግስት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ለመወያየት መቐለ ከተማ ገብተዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.