RODAS Agency
RODAS EMPLOYMENT AGENCY 0921314899
13/04/2023
29/03/2023
#እንድታውቁት
" #አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም በ11ዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው “ አስቸኳይ ” የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳውቋል።
አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ ?
አገልግሎቱ የተቋረጠው የባለ ጉዳይ ፍሰት ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ መጠነ ሰፊ በመስተዋላቸው ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ተገልጋዮች ሊገለገሉ ሌሊት ላይ በሚመጡበት ወቅት በተለያዩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የሚደርስባቸው እንግልትና ጉዳት በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋዩ ላይ ተግዳሮት በመፍጠሩ ነው።
ስለሆነም የማስተናገድ አቅም እና ሌሎች ክፍተቶች እስከሚስተካከሉ ድረስ ይሰጥ የነበረው የ “ አስቸኳይ ” ፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል።
አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው በምን ይስተናገዳሉ ?
ቀድሞ ይሰራበት በነበረው አሰራር መሰረት ያላቸው አገልግሎት ጠያቂዎች ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው ቤት ብቻ ከመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይስተናገዳሉ።
ማሳሰቢያ ፦ ተገልጋዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከህገወጥ ደላሎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።
የመደበኛ ፓስፖርትን በተመለከተስ ?
የመደበኛ ፓስፖርት ተገልጋዮች ቀድሞ በነበረው ሂደት መስተናገድ #ይቀጥላሉ።
ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
25/01/2023
ያልተመዘገባችሁ ተመዝገቡ!!
****
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለ4ኛ ዙር ሠልጣኞች የምዝገባ ቀናትን አራዘመ
********************
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ለ4ኛ ዙር ላዘጋጀው ሥልጠና የሚያካሄደውን የምዝገባ ጊዜ ማራዘሙን አስተውቋል።
ለሥልጠናው ፍላጎት ያሳዩ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ፣ በየቅርንጫፎቹ የታየው የተመዝጋቢዎች መጉላላትን ለማስቀረት፣ ተጨማሪ ተመዝጋቢዎችንም ለማካተት እና በሚፈለገው መልኩ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ፣ ምዝገባውን በእርጋታ ለማካሄድ ይቻል ዘንድ እስከ መጪው እሑድ ጥር 21 ቀን 2015 ድረስ ምዝገባው ለ4 ተከታታይ ቀናት ማራዘሙን የባንኩ ማኔጅመንት ገልጿል።
በመሆኑም ተመዝጋቢዎች በቀሪዎቹ ቀናት ተረጋግተው ምዝገባቸውን እንዲያካሂዱ ባንኩ አሳስቧል።
ይህንኑ በማስፈጸም ላይ ላሉ የባንኩ ቅርንጫፎችም መመሪያ መተላላፉ ታውቋል።
04/01/2023
Click here to claim your Sponsored Listing.