Shop in ethio

Shop in ethio

Share

We are a professional shoe supplier, we will provide you with the best and most affordable shoes. Welcome to our website!

Photos from Shop in ethio's post 01/12/2021

Iphon6 5000birr only

16/01/2018

ተነግሮ የቱ ይተዋል
የጌታ ሥራ እጅጉን በዝቷል
ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ
በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ

ነግሮ ሊጨርስ ማነው የቻለ
ተዓምራቶቹን እያስተዋለ
የጌታን ክብር ታላቅነቱን
የፍቅሩን ብዛት ደግሞ ጥልቀቱን

ከመጣው (ም) ሁሉ ያለፈ
ከህሊናችን ሞልቶ የተረፈ
ነውና ታላቅ ሥራው ብዙ
ለዚህ ለጌታ ምሥጋናውን አብዙ

ይሄ ሁሉ ፍጥረት የሚያመሰግንህ
ይሄ ሁሉ ክብር ለአንተ የተገባ
ስለሆንክ ገዢ ብርቱና ገናና
አሁንም አሁንም ይብዛልህ ምሥጋና

ፍጥረታት በሙሉ በግዛትህ ናቸው
ስለዚህም በአንተ ብዙ ደስታ አላቸው
በራሳቸው ቋንቋ ይመሰክራሉ
የእግዚአብሔር ሥራ ፍጥረት ነን እያሉ ሃሌሉያ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ

በደማቅ ብርሃን እራስክን ሰውረህ
ከፍ ካሉት በላይ እጅግ ከፍ ብለህ
ድካምና ዝለት ሳያውቅህ እርጅና
ትናንትና ዛሬም ሁልጊዜ ገናና

ንጉሥ በንግሥናው አዋቂው በዕውቀቱ
ሊመስልህ ሲሞክር ሲጥር አይ ሰው ከንቱ
ነገር ግን ከአንተ ጋር ሁሉን ሲያስተያይ
ሁሉን ብሎ ያልፋል የለህም መሳይ ሃሌሉያ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር እንዲህ ይህን ይመስላል
ተብሎ በቃላት መች ይገለጻል
አንዲያ ልጁ በቀኙ ያለው
ተረከው እንጂ ሌላ ማን አየው

ሰማይ ተቀምጦ እግሮቹ ምድር
ታላቅነቱ እንዴት ይነገር
መግለጫ ቋንቋ ቢጠፋም ቃሉ
እንዲሁ ብቻ ተመሥገን በሉ

የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል
የጌታ ዝና እጅጉን በዝቷል
ከየት አንስቼ ስንቱን ላስታውስ
በየማለዳ ሁልጊዜ አዲስ

የለህም መሳይ (፫x) በምድር በሰማይ
የለህም እኩያ (፫x) ኦ ሃሌሉያ (፪x)

Want your business to be the top-listed Clothing Store in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa