Chora Media
we strive for change through information access!
01/02/2026
"አባዬ... ከሞት አድነህኛል አሁን ደሞ እኔ ልንከባከብህ።"
"እቺ ልጅ በእሳት ከሚቃጠል መኪና ውስጥ ሳወጣት 38 አመቴ ነበር።
ከስራ ወደ ቤት እየተመለስኩኝ ነበር፤ በእሳት የሚቃጠል መኪና ስመለከት ብስክሌቴን አቁሜ መኪናው ጋር በመድረስ፣ በሩን ፈጥኜ ከፍቼ፣ የደህነት ቀበቶዋን በመፍታት በእሳት ከሚቃጠለው መኪና ውስጥ አወጣዋት።
ደረቴ ላይ ልጥፍ ብላና ልብሴን ጥብቅ አድርጋ ይዛኝ አለቀሰች።በአምቡላንስ ሆስፒታል ወሰድኳት ፤ህፃኗ ብዙም ጉዳት አልደረሰባትም ነበር።
መኪና ውስጥ የነበሩትን ወላጆቿን ግን ማዳን አልተቻለም።
በቀጣዩ ቀን ላያት ሄድኩኝ ዝም ብላ ታየኝም ነበር፤ማንም ዘመድ ሊጠይቃትና ሊወስዳት የመጣ አልነበረም ።
ማንም ረዳትና ዘመድ ስላልነበራት ልጅቷን ለማሳደግ ወረቀቶችን ፈርሜ ወደ ቤቴ ወሰድኳት።
የሚያስፈልጋትን ሁሉ ነገር በማድረግና በእንክብካቤ አሳድጌ አስተማርኳት።
በአሜሪካን አቬሪ ከተማ የፖሊስ አካዳሚ ገብታና ተምራ የከተማውን ህዝብ የምታገለግል የፖሊስ መኮንን ለመሆን በቅታለች ።
ከ25 ዓመታት በኋላ ትኩር ብላ በፍቅር እየተመለከተችኝ "አባዬ... ከሞት አድነህኛል አሁን ደሞ እኔ ልንከባከብህ" አለችኝ።በቪዲዮ ለመመልከት https://www.youtube.com/ ዩቲዩብ ላይ ይመልከቱ።
ሙሉ ቪድዮው ኮሜንት ላይ ያገኛሉ።