Ethio Doctors
This is a site created by Ethiopian Doctors to provide the best lifestyle and health tips. Like and follow us to be updated with recent medical advices.
29/11/2021
ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?
1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡
2) በአንጎል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ለእንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነጭ፤መደበትና እና የባህርይ ለዉጥን ያስከትላል፡፡
3) በከንፈር ላይ የሚወጡ አንዳንድ ቁስለቶች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
4) ለደም ግፊት መጨመር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ ለልብ ሕመምም ይዳርጋል፡፡
5) በሳንባ ላይ የሚያስከትለው ችግር የአስም ሕመምተኞች ላይ የአዕምሮ ጭንቀት ሕመማቸው እንዲነሳባቸው ያደርጋል፡፡
6) በጡንቻዎች ላይ ሕመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ለወገብ ሕመም ያጋላጣል፡፡
7) ጭንቀት የጨጓራ ሕመምን ከማስከተል ባለፈ ለአንጀት ቁስለትም ሊዳረግ ይችላል፡፡
8) ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት የወር አበባ ዑደትን ያዛባል፡፡ ወንዶችን ለስንፈተ ወሲብ ስለሚዳርግ የትዳር እና የፍቅር ግንኙነት እንዲሻክር ያደርጋል፡፡
ስለዚህ ጭንቀትን በማስወገድ ጤንነትዎን ይጠብቁ የዛሬዉ መልዕክቴ ነዉ፡፡
እባክዎን ለወዳጅዎ ያካፍሉ
ጤና ይስጥልኝ
15/11/2021
✅🌀 በኩላሊት ጠጠር ለሚሰቃዩ ሰዎች የጤና መረጃ
✅🌀 የኩላሊት ጠጠርን በ10 ቀናት ውስጥ ለማስወገድ
-----------••••••••••••••••••------------------
በአሁኑ ሰዓት የኩላሊት ጠጠር በጣም በብዙዎች ዘንድ የሚከሰት ችግር ሆኗል፡፡ ጠጠሩ የሚፈጠረው በሚኒራሎች እና በአሲዳማ ጨው በኩላሊት ውስጥ ሲሆን የሚከማቸው በኩላሊት ውስጥ ወይም በላይኛው የሺንት ቧንቧ አልያም በሽንት ፊኛ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡፡
የሚፈጠሩት ጠጠሮች በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ሊወገዱ ይችላሉ፡፡ የተወሰኑት ግን እዚያው ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ እዚያው የሚቆዩ ጠጠሮች ካልተወገዱ፣ አንድ ላይ ትልቅ ጠጠር መፍጠራቸው አይቀርም፡፡
ምናልባት የጎልፍ ኳስ ያክል መጠን ሊደርስም ይችላል፡፡ ይህም የሽንት ቧንቧን ሊዘጋ፣ በምንሸናበት ሰዓት ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል፣ ማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም ማስታዎክ ያስከትላል እነዚህ ችግሮች ጠጠሩ አስካልተወገደ ድረስ ቀጣይነት ይኖራቸዋል እንጂ አይተውንም፡፡
🚺🚹 የኩላሊት ጠጠርን ለማስወገድ የሚሆኑ ዘዴዎች
የኩላሊት ጠጠር ከሰውነታችን በተለያዩ መንገዶች ሊወገድ ይችላል፡፡ ይህም በጠጠሩ መጠን እና አይነት ይወሰናል፡፡ የኩላሊት ጠጠር በውስጣችን እንዳለ ካወቅን ስለሁኔታው የጤና ባለሙያ ማማከር የመጀመርያ ስራችን መሆን አለበት!!!
ዋናው ነገር ግን አስቀድሞ መከላከል ነው፡፡ ይሄም በቀላሉ ከቤት በምናዘጋጃቸው ነገሮች (home remedies) የኩላሊት ጠጠርን መጠን መቀነስ እና በሽንት አማካኝነት እንዲወገዱ ማድረግ ይቻላል፡፡
🚺🚹 ከነዚህ home remedies መካከል በጣም የሚታወቀው የሚከተሉትን ነገሮች በመቀላቀል የሚገኝ ነው።
🟢 #እነርሱም፦
👉 1 ብርጭቆ ንጽህ ሙቅ “ውሃ”
👉 2 የሾርባ ማንኪያ “የአፕል ጭማቂ”
👉 1 ወይም 2 የሾርባ ማንኪያ “ማር”
👉 ግማሽ የሻይ ማንኪያ “ቀረፋ” ናቸው፡፡
🟢 #አወሳሰድ
👉 “ለሁለት ሳምንታት” “ማታ” ከመተኛታችን በፊት መጠጣት፡፡
👉 እንደ ጠጠሩ መጠን በአስር ቀን ውስጥ ጥሩ ውጤት ማግኘት እንችላለን፡፡
ሌሎችም ያንብቡት ሼርርርር አርጉት
ጤናዎ ይብዛለዎት!!!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000