Liyu Mereja
አደደዲስ እና ዎክታዊ እንዲሁም አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ መረጀዎችን እናቀርብላቿኋላን።
ፔጁን like & share በማድራግ አበል ይሁኑ።
01/07/2026
መብረቅ ለመታው ሰው ስለሚደረጉ እና ስለማይደረጉ ነገሮች :-
አይበለው እና ከእኛ ጋር ያለ ሰው የመብረቅ አደጋ ቢደርስበት ከአፈር ለመቅበር ወደ ጉድጓድ ቁፈራ ነው የምንሄደው ወይስ ምን እናድርግ፤ ብንነካው ቻርጁ ወደ እኛ ይተላለፋል ወይስ አይተላለፍም? የሚሉትና እና ሌሎች ጠቃሚ ሳይንሳዊ ምክሮችን እነኆ ።
፩. የባህላዊ ልማዶች ፍተሻ፦ የታሰበው እና ሳይንሳዊ እውነታው
ማንኛውም ሰው መጀመሪያ እርዳታ ከመጀመሩ በፊት የሚከተሉትን ጎጂ ልማዶች ማወቅ እና ማስወገድ አለበት፦
ሀ. መሬት ውስጥ መቅበር (እስከ አንገት/እስከ ደረት)
የሚታሰበው ፦ አፈሩ በሰውነት ውስጥ የተከማቸውን ኤሌክትሪክ ወደ መሬት ይስበዋል ተብሎ ይታመናል።
ሳይንሳዊ እውነታው፦ መብረቅ ሰውን መትቶ የሚያልፈው በሚሊሰከንዶች ውስጥ ስለሆነ ሰውነት ውስጥ የሚቀር የኤሌክትሪክ ክምችት የለም። አፈር መቆፈር እና ሰውን መቅበር ሌሎች ሕይወት አድን የሆኑ ስራወችን ለመሥራት የምንጠቀምበትን ወሳኝ የሆነውን ሰዓት (ወርቃማ ጊዜ) ያባክናል። በተጨማሪም አፈሩ ደረት ላይ የሚፈጥረው ጫና መተንፈስ ይከለክላል ፤ የሰውነት ሙቀትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል ፤እንዲሁም በአደጋው ጊዜ በቃጠሎ ምክንያት የተፈጠሩ ቁስሎችን ለከፋ ኢንፌክሽን ያጋልጣል።
ሲጠቃለል መቅረቅ የመታውን ሰው ከአፈር መቅበር ምንም ዓይነት ጥቅም የለውም ።
ለ. ሌሎች የማይጠቅሙ እና ጎጂ ልማዶች :-
🎆ውሃ፣ ወተት ወይም ባህላዊ መድኃኒት በአፍ ማጠጣት፦ ራሱን የሳተ ሰው የመዋጥ አቅም ስለሌለው ፈሳሹ በቀጥታ ወደ ሳንባ በመሄድ ወዲያውኑ ሊያንቀው ወይም ሊገድለው ይችላል። ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ንቁ ያልሆነ ሰው (ራሱን የሳተ) ምንም አይነት ፈሳሽ ለማጠጣት መሞከር አይመከርም።
🎆በቃጠሎ የተፈጠ ቁስል ላይ ቅቤ፣ ዘይት ወይም ሌላ ነገር መቀባት፦ የመብረቅ ቃጠሎ ከፍተኛ ውስጣዊ ሙቀት አለው። ቅቤ ወይም ዘይት መቀባት ሙቀቱ ወደ ውጭ እንዳይወጣ አፍኖ በመያዝ ቃጠሎውን ያባብሰዋል፤ ከባድ ባክቴሪያም ወደ ውስጥ ያስገባል።
🎆 አደጋው በደረሰበት ቦታ ላይ መቆየት፦ መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ፣ እዚያው ቦታ ላይ እርዳታ ለመስጠት መሞከር ረዳቱንም ጭምር ለአደጋ ያጋልጣል።
፪. መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች :-
የመጀመሪያ እርዳታ ሰጪው ሕክምና ባለሙያ ባይሆንም የሚከተሉትን እርምጃዎች ደረጃ በደረጃ መተግበር አለበት፦
ደረጃ 1 ፦ የቦታውን ደህንነት ማረጋገጥ
መብረቅ የደረሰበትን ሰው ወዲያውኑ በእጅ መንካት ምንም አይነት ችግር አያመጣም።
ነገር ግን ከላይ እንደጠቀስነው መብረቅ በአንድ በዝናብ ማዕበል ወቅት በአንድ ቦታ ላይ ከአንድ ጊዜ በላይ የመምታት ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለሆነም ተጎጂውን በአስቸኳይ ይዞ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ ለምሳሌ ቤት ውስጥ ካልተቻለም በአካባቢው ካለው አንጻራዊ ዝቅተኛ ቦታ ላይ መውሰድ ያስፈልጋል።
ደረጃ 2፦ ተጎጂውን ሁኔታ መገምገም እና እንደ ሁኔታው እርዳታ መስጠት
እዚህ ጋር ተጎጂው ያለበትን ሁኔታ አይቶ እርዳታውን እንደሚከተለው ማድረግ ተገቢ ነው ።
ሁኔታ ሀ፦ ራሱን ለሳተ እና መተንፈስ ለማይችል ሰው
ይህ ሁኔታ ተጎጂው የልብ ምት መቆም አጋጥሞታል ማለት ስለሆነ እጅግ አስቸኳይ እርዳታ ይፈልጋል።
ለእርዳታ ሌላ ሰው መጥራት ከተቻለ አምቡላስ መጥራት ጎን ለጎን የሚሰሩ ሆነው አብሮ ያለ ሰው ወዲያውኑ ተጎጅውን በጀርባው በማስተኛት በሁለቱ ጡቶች መካከል ላይ የእጅዎን መዳፍ በማድረግ፤ ሁለተኛውን እጅ በላዩ ላይ በማጣመር ክንድዎን ሳያጥፉ፣ የሰውነትዎን ክብደት በመጠቀም ደረቱን ወደ ታች ከ5-6 ሳንቲም ሜትር ጥልቀት በፍጥነት እና በኃይል መጫን ነው ።
ፍጥነት፦ በደቂቃ ከ100 እስከ 120 ጊዜ መጫን ። ይኼንንም እየተጋገዙ የሰውየው መተንፈስ እስኪመለስ ድረስ ወይም እስከ 30 ደቂቃ ድረስ መደጋገም ያስፈልጋል።
ይህን በትክክል ካደረግን ከ100 ሃያ ሰዎችን ወይም ከዚያ በላይ ማትረፍ ይቻላል።
እንደ አጋጣሚ ከመካከል ስልጠና የወሰደ ካለ ግን ደረትን ከመጫን በተጨማሪ ትንፋሽም መስጠት ያስፈልጋል (ለሰለጠኑ) ።
ሁኔታ ለ፦ ራሱን ለሳተ ነገር ግን በትክክል ለሚተነፍስ ሰው
ሰውየው ልቡ እየመታ እና እየተነፈሰ ከሆነ ነገር ግን ካልነቃ የሚከተሉትን ያድርጉ፦
A. ተጎጂውን በግራ ጎኑ ማስተኛት፣ የላይኛውን እግሩን አጥፎ ወደ ፊት ማድረግ እና እጁን ከጉንጩ ስር ማስደገፍ። ይህ አቀማመጥ ምላሱ ጉሮሮውን እንዳይዘጋው እና ቢተፋ እንኳ ትውከቱ ወደ ሳንባው ሳይሄድ ወደ ውጭ እንዲፈስ ያደርጋል።
B. የአየር መተላለፊያውን መከታተል፦ አፉ ውስጥ አፈር፣ ሳር ወይም ትውከት ካለ በንጹህ ጨርቅ በጥንቃቄ ማጽዳት::
C. ትንፋሹን መቆጣጠር፦ በየደቂቃው ደረቱ መነሳቱንና መውረዱን ማየት። ትንፋሹ ከቆመ ወዲያውኑ ከላይ ያየነውን ሁኔታ 'ሀ' ማድረግ ።
ሁኔታ ሐ :- የቃጠሎ ቁስሎችን በአደጋው የተፈጠረ የአጥንት ስብራት ካለ የሚደረጉ እርዳታወችን የሚተነትን ነው ይታወቃሉ።
የመጨረሻ ማሳሰቢያው መብረቅ የደረሰበት ሰው ምንም ጉዳት የሌለበት ቢመስልም፣ አልፎ ተርፎም ተነጋግሮ በገዛ እግሩ ቢሄድም እንኳ፣ በግዴታ ወደ ሆስፒታል መወሰድ አለበት።
30/06/2026
Olive Oil and Onion for P***s Enlargement - How To Use Oil for P***s Growth & Testosterone Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Click here to claim your Sponsored Listing.