End Time Warning/ETw/ Ministry
ወንጌል መመስከር፤ ድሆችን መርዳት!!! የዳኑ ነገር ግን በጌታ ቤት ጸንተዉ ያልቆሙ ወገኖችን ማገልገል
ላልዳኑ ወንጌልን መመስከር
የወንጌል አርበኞችን መጎብኘትና መደገፍ
አቅመ ደካሞችን፤ወላጅ አጥ ህፃናትን መርዳት፤ማስተማር እና ሥራ መፍጠር
04/04/2025
በዚህ የዘመን ፍጻሜ እኛ ሁላችን መሄድ ባንችል ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ እንድሄድ እግር እና እጅ በመሆን ድርሻችንን መወጣት እንችላለን:: ይህ ህብረት ሌላ ተጨማሪ የማገልገል ዕድል ለሁላችን ይዞልን በመምጣት ለወንጌል ተልዕኮ አገልግሎት በልዩነት የተጠሩትን ለመላክ፣ ለመሄድ እና የተላኩትን ለመደገፍ የተነሳ እና ከሌሎች ጋር የእግዚአብሔር መንግሥት አብሮ ሰራተኛ የሆነ አገልግሎት ነውና ከታች ያለውን Link በመንካት ህብረቱን ይቀላቀሉ ፣ አብረውን በፀሎት ይትጉ፣ ቃሉን ያጥኑ፣ ካሎት ነገር ጥቂት አካፍለው በእግዚአብሔር መንግስት ብዙ ያትርፉ እናም ለዚህ ለከበረ ጥሪ በደስታ ምላሽ ይስጡ!! ❗️❗️ ህብረቱን ስቀላቀሉ ሸክም እና የወንጌል ዕዳ እንዳለቦት እርግጠኛ ይሁኑ❗️❗️
መከራ፣ ስደት፣ ማጣት፣ በሽታ፣መጠላት እና ወዘተ የዚህ ምድር መገለጫ ነው ፡፡ ነገር ግን የዚህ ምድር ክፋት እንዲሁም የዲያብሎስ ውግያ ያጠፋናል ብለን የማንሰጋበት ምክንያት አባታችን እግዚአብሔር ስለሆነ በብዙ ወይም በጥቂት ማዳን ስለማያስቸግረው በእርሱ ተዘልለን እንኖራለን እንጂ በአንዳች አንናወጥም ፤ ለምንም አንፈራም፡፡ ክብር ለስሙ ይሁን፡፡ 1ኛ ሳሙ 14÷6! መልካም ቀን!
03/01/2024
Click here to claim your Sponsored Listing.