Man City Addis

Man City Addis

Share

This is the official page of Man City Addis, the official Supporters Club for Manchester City FC.

11/05/2026

ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ኤፍኤ ካፕ እና ካራባኦ ካፕ ያለውን አክብሮት በሚመለከት :-

​"ከአስር አመት በፊት ከረዳቶቼ ጋር እዚህ ክለብ ከመጣሁ ጀምሮ፣ ክለቡ ገና ከቅድመ-ውድድር (pre-season) የመጀመሪያ ጨዋታ አንስቶ ‘ማሸነፍ አለብን፣ ለማሸነፍ መጣር አለብን’ ብሎ እንዲያስብ ለማድረግ ሞክሬያለሁ። እኛ ውድድሮችን አንመርጥም። ጨዋታዎችንም አንመርጥም። የስራ ስነ-ምግባራችን እና ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነው።

​ሁላችንም ሊቀመንበሩ፣ ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ የስፖርት ዳይሬክተሩ፣ እኔ ራሴ እና ተጫዋቾቹ በውስጣችን ‘በእያንዳንዱ ጨዋታ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን’ የሚለውን ስሜት አትመናል። ይህም ለህዝባችን ካለን አክብሮት እና ለስራችን ካለን ክብር የተነሳ ነው። ሁላችንም እጅግ በጣም ከፍተኛ ክፍያ ይከፈለናል። ይህንን ማድረግ አለብን። ስራህን ትወዳለህ? ለዛ ነው! ስራችንን መወጣት አለብን።

​ከውድድር ስንወጣ እና ውጤቱም ተገቢ ሲሆን በፀጋ እቀበላለሁ። እንደ አሰልጣኝነቴ ከሊግ ዋን ቡድኖች ጋር ስንጫወት ለተጫዋቾቼ ‘ከእነሱ በላይ ጠንክራችሁ ስሩ’ እላቸዋለሁ። ተጫዋቾቹም ይህንን ያውቁታል። ‘ተጠንቀቁ ፣ በብቃታቹ ልክ ካልሆናችሁ ችግር ውስጥ እንወድቃለን’ እላቸዋለሁ። ክለቡም ሆነ ተጫዋቾቹ ይህ ይሰማቸዋል።

በቻምፒዮንስ ሊግ ከማድሪድ ጋር ወይም በሜዳችን ከአርሰናል ጋር ለሚደረግ ጨዋታ መነሳሳት ቀላል ነው። ቡድኑም ሆነ ደጋፊው በዛ ሰዓት ክለቡን ለማገዝ ዝግጁ ናቸው።

​ክለቡን የሚገልጸው ግን ይሄ ነው። ባለፉት አስር አመታት በሁሉም ውድድሮች ያሳየነው ወጥነት። ይህ በእውነት፣ በእውነት አስደናቂ ነው፣ እጅግ በጣም አስደናቂ!"

09/05/2026

በዛሬው ጨዋታ አንድ የአርሰናል ደጋፊ ከብሬንትፎርድ ደጋፊዎችጋ ተመሳስሎ ገብቶ ታይቷል።

አልተሳካም 😁

09/05/2026

ዶኩ በዚህ ሲዝን 😁

09/05/2026

የፕሪምየር ሊጉ ቴብል ይሄን ይመስላል

Want your organization to be the top-listed Non Profit Organization in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address

Addis Ababa