Tesfa

Tesfa

Share

የሰው ልጆችን በእውነተኛ ተስፋቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለመርዳት የተከፈተ ገፅ ነው

31/05/2026

እግዚአብሔር የልጆቹን ጩኸት ይሰማል። አንዳንድ ጊዜ በችግር፣ በሀዘን ወይም በጭንቀት ውስጥ ልታልፍ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይሰማል፣ የምታልፍበትንም ያውቃል፤ ደርሶም በጊዜው ይረዳሀል።
እግዚአብሔር ቅርብ ነው፣ የሚሰማ እና የሚያድንም አምላክ ነው።
ዛሬ በጭንቀት ውስጥ ከሆንክ ተስፋ አትቁረጥ። እግዚአብሔር ጩኸትህን ይሰማል፤ በጊዜውም ይደርስልሀል።

“ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።”— መዝሙር 34፥17

27/05/2026

እግዚአብሔር በማንኛውም የሕይወት ሁኔታ ውስጥ ለልጆቹ ቅርብ ነው። ከአደጋ ምትሸበት እና የምትጠለልበት መጠጊያ ቦታ ነው። እግዚአብሔር በድካምህ ጊዜ የሚያበረታህ ኃይልህ ነው። አንዳንድ ጊዜ በሕይወትህ የምታልፍበት ነገር ከአቅምህ በላይ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያ ጊዜ ውስጥ እንኳ የሚያጸናህ እና እንድትቀጥል የሚያደርግ ኃይል ይሰጥሀል። እግዚአብሔር አምላክ በችግርህ ጊዜ ከአንተ ጋር ያለ፣ የሚረዳ፣ የሚያጽናና እና ተስፋ የሚሰጥ አባት ነው።

ዛሬ በሕይወትህ ውስጥ ድካም፣ ፍርሃት ወይም ጭንቀት ካለ፣ ብቻህን አይደለህም። እግዚአብሔር መጠጊያህ፣ ኃይልህ እና ረዳትህ ነው። ወደ እርሱ በጸሎት ብትቀርብ ሰላሙን ይሰጥሃል፣ ልብህንም ያበረታል።

መዝሙር 46:1 አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።

26/05/2026

በዚህ ቃል መሰረት ፈተና ወይም ፍርሃት ቢኖር እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን ይነግርሀል። ብቻህን አይደለህም፤ እርሱ ይመራህል፣ ያጽናናሀል፣ ኃይልም ይሰጥሀል።
በምታልፍበት ሁኔታ ሳይሆን በእግዚአብሔር ህልውና ታመን። እርሱ በምትሄድበት ሁሉ ከአንተ ይሆናል። ፍርሃትህን አስወግደህ፤ በእግዚአብሔር ብቻ ታምነህ ምትኖርበትን ህይወት ዛሬ ወስን!

"በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?” ኢያሱ 1፥9

14/05/2026

በጣም ከባድ ጊዜያቶችን በምታሳልፍበት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው። ዳዊት ብዙ ጦርነት፣ ፍርሃት እና አደጋ አጋጥሞት ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አብሮነት ላይ ሙሉ በሙሉ ይተማመን ነበር። ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ባለ ጊዜ እንኳ እንደማይተወው ስለሚያውቅ ነው።

ዛሬ ምንም አይነት ጭንቀት ቢገጥምህ፣ ብቻህን አይደለህም! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፣ እርሱም ሰላምን ይሰጥሃል።

መዝሙር 23:4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፡ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።

Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa