Safe Drive in Addis
Welcome to Land of Origins.........
Stay safe and enjoy your time on Africa's capital Addis Ababa.
🚨🚨 ድምፅ ለሹፌሮች 🚨🚨
በአመት በዓሉ እንኳን ብታሳርፉን ምናለበት ደማችን ከማፍሰስ ኪሳችን ከመዳበስ ብትቆጠቡ :: ማንም የዘራውን ያጭዳል ሾፌር እየበደሉ እየገደሉ ምቾት ሆነ ድሎት አይኖርም ማንም ብትሆን ዋጋ ትከፍልበታለህ ::
የምር ነው የምንላችሁ እንዲህ እንቅልፉን አጦ ወገቡ ጎብጦ በሀሩር ቀልጦ ያመጣውን እየዘረፍክ እየገደልክ እኖራለው ብለህ እንዳታስብ ዋጋህን በምድር የላይኛው ይሰጥሀል ::
1 ብር ከካሜራ ጀርባ VS የጀሞ .........😂
Now in Addis 4 እንኳን አደረሳችሁ
Safe Drive in Addis
Now in Addis 1 እንኳን አደረሳችሁ
Safe Drive in Addis
17/01/2025
ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
የ2017 ዓ/ም የከተራና የጥምቀት በዓል ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር በጥምር የፀጥታ አካላቱ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል። በዓሉ በሚከበርባቸው ቦታዎች ሁሉ ከአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ የስምሪት አቅጣጫን በመከተል ፀጥታ የማስከበር ተግባሩ የሚከናወን ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በ11ዱም ክ/ከተሞች ጥምቀተ ባህር ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በ500 ሜትር ክልል ውስጥ ታቦታት ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም በሚሄዱባቸው መንገዶች ለአጭር ጊዜም ይሁን ለረዥም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
እንዲሁም ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ በጃን ሜዳ እና አቃቂ ቃሊቲ ታቦት ማደሪያ በሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ምክንያት በአካባቢው የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፦
👉 ከ6 ኪሎ አደባባይ - ምኒልክ ሆስፒታል
👉 ከምኒልክ ሆስፒታል - መከላከያ 3ኛ ሻለቃ አደባባይ
👉 ከ3ኛ ሻለቃ አደባባይ - 6 ኪሎ አደባባይ እንዲሁም አቃቂ ቃሊቲ አካባቢ
👉 ከዋልያ ቢራ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
👉 ከአቃቂ ዋናው መንገድ - ጥሩነሽ ቤይጂንግ ሆስፒታል
👉 ከ08 - አቃቂ ድልድይ ድረስ ከጥር 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ ለተሽከርካሪዎች ዝግ ስለሚሆን አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን እያስተላለፈ በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጻል።
*
ዘገባ፡- ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
አዲስ አበባ በእንግዶቿ እይታ.............
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
1000